# ሸገር ብሎግ > የጡመራ ድረገጽ ## Posts - [ነግሬህ ነበረ](https://shegerblogs.com/%e1%8a%90%e1%8c%8d%e1%88%ac%e1%88%85-%e1%8a%90%e1%89%a0%e1%88%a8/): በድንገት ከኋላዬ መጥተህ አትንካኝ ብዬህ ነበር፡፡ ያጠብኳቸውን ብርጭቆዎች አንድ በአንድ እያደረቅኩ ከጀርባዬ መጥተህ ስትጎነትለኝ ጩኸቴን ለቀቅኩት፡፡ በድንጋጤ የወረወርኩት ብርጭቆ ወለሉ ላይ አርፎ ሲበተን አንዱ ስባሪ እግሬ ላይ ተሰካ፡፡ - [መልካም ጋብቻ](https://shegerblogs.com/%e1%88%98%e1%88%8d%e1%8a%ab%e1%88%9d-%e1%8c%8b%e1%89%a5%e1%89%bb-2/): (ከማታ ማታ መጽሐፌ (2012 ዓ.ም.) ከጓደኞቼ ማኅደርና እስከዳር ጋር፣ ዘናጭ ካፌ ቁጭ ብለን ውድ ማኪያቶ እየጠጣን ነበር፡፡ ማኪያቶው አሪፍ፣ ጨዋታው ደማቅ ነበር፡፡ መርዶዬን እስኪነግሩኝ… “ናሆምና ማርታ ሊጋቡ ነው” እስኪሉኝ፡፡ እንደሰማሁ በድንጋጤ ምራቄ ከአፌ አለቀ፡፡ በማኪያቶ የሞቀ ሰውነቴ በአንድ ጊዜ ቀዘቀዘ፡፡ ሰበባ’ ሰበብ ድርድሬ፣ራሴን አመመኝ ራይድ ጥሩልኝ ብዬ ካሰብኩት በጣም ቀድሜ ተለየኋቸውና ቤቴ ገባሁ፡፡ ናሆም ሊያገባ ነው? የኔ ናሆም ሊያገባ ነው? ያውም ያቺን አብረን እንፎግራት የነበረች ዝንጅብል ቅርጽ ማርታ? ሶፋዬ ላይ ቁጭ ብዬ ጥፍሬንም ነገርም ሳኝክ፤ ቅናት ሳመነዥክ፣ ልጆቼ ከባለቤቴ ጋር ከትምህርት ቤት መጡ፡፡ “እንዴት ዋልሽ…? ፊትሽ ጠቋቆረ ምነው?” አለኝ ባሌ፡፡ ጉንጮቼን በእጆቹ እየዳበሰ፡፡ መልካሙ የአሥር ዓመት ባሌ፣ እንኳን ፊቴ በሐዘንማንበብ ይቀጥሉ... - [ቀኑ እንዴት ይመሻል ያንን ሳናነሳ](https://shegerblogs.com/%e1%89%80%e1%8a%91-%e1%8a%a5%e1%8a%95%e1%8b%b4%e1%89%b5-%e1%8b%ad%e1%88%98%e1%88%bb%e1%88%8d-%e1%8b%ab%e1%8a%95%e1%8a%95-%e1%88%b3%e1%8a%93%e1%8a%90%e1%88%b3/): አዝማሪ ወርቄ (ሻምበል ወረቀት) እንዲህ ይል ነበር፤ “ቢናገሩ አፈኛ፤ ዝም ቢሉ ሞኝ ቢወፍሩ ዝሆን፥ ቢቀጥኑ ትንኝ ‘ አወይ ሰው! አወይ ሰው! ሰው አስቸገረኝ” ካዝማሪው የተረፈውን እነዲህ መዘርዘር ይቻላል- ብትጋብዝ “ አባካኝ “ ትባላለህ- ብትቆጥብ “ ቁዋጣሪ” – ብታሞግስ “ አሽቃባጭ፥- ብትተች” አቃቂረኛ- ብትቀመቅም “ሰካራም” ባትቀመቅም “ አብሿም”- ሴቶች ቢቀርቡህ “አተራማሽ -የሴት ድሮን” ‘ – ሌጣህን ብትሆን “ስልብ “ ወይም “ ጌ” ሸሸግ ብትይ “ ምነው ጠፋሽ “ – ብቅብቅ ብትይ” ምነው እዩኝ እዩኝ አበዛሽ “ – ባያምርብሽ “አመዳም “ -ቢያምርብሽ “ፊልተራም” ወይም “ዱቄታም” -ብትጨምቺ “ አንገት ደፊ አገር አጥፊ፤ “ ነጻ ብትሆኝ ‘ ሸሌ” እንደ መካሪ ሲቃጣኝ እንዲህ እላለሁ- በማንኛውምማንበብ ይቀጥሉ... - [አክስቴ አክሊል](https://shegerblogs.com/%e1%8a%a0%e1%8a%ad%e1%88%b5%e1%89%b4-%e1%8a%a0%e1%8a%ad%e1%88%8a%e1%88%8d/): አክስቴ አክሊል በመላው ቤተሰብና ዘመድ አዝማድ ዘንድ የምትታወቅበትና የምትፈራበት አንድ ባህርይ አላት፤ ሽሙጧ! የአክስቴ አክሊል ማሽሟጠጥ ግን ዝም ብሎ ማሽሟጠጥ ብቻ አይደለም፡፡ ከባድ ጥበብ አለው፡፡ ቂቤ የምትቀባ መስላ በኩርኩም ታነድሻለቸች፤ ያሞገሰች መስላ ትሞልጭሃለች፡፡ በአንድ ሰበብ ዘመድ በተሰበሰበ ቁጥር ከእነ ረጅም ቁመቷ የድግስ ቦርሳዋን ብብቷ ሥር ወሽቃና ልክ እንደ ሰላም አምባሳደር ቀና ብላ ስትገባ ሰው ሁሉ ይሸበራል፤ እሷ ያለችበት ሰላም የሚባል ነገር የለማ! ዛሬም ያው የአሽሙር ባህሪዋን እንደ ቦርሳ አነግባ መጥታለች፡፡ የተሰበሰብነው የሌላዋ አክስቴን (እና የአክሊልን የታናሽ ታናሽ እህት) አዲስ ቤት ለመመረቅ በተዘጋጀ ግብዣ ነው፡፡ ገና ከመግባቷ እንደተለመደው የለበጣ ፈገግታዋን ፊቷ ላይ ስላ የተሰበሰብነውን ሁሉ አንድ በአንድ ሰላም ስትልና ስታወራ ሰቀቀኑማንበብ ይቀጥሉ... - [ሰወርዋራ](https://shegerblogs.com/%e1%88%b0%e1%8b%88%e1%88%ad%e1%8b%8b%e1%88%ab/): ያገባሁት ሰው እንዴት እንዴት ብሎ ሕይወቴን ብልሽትሽት እንዳደረገው፣ በእድሜዬ ጢቢ ጢቢ እንደተጫወተ ልንገራችሁ። እንዴት የሰው ልጣጭ፣ የሰው ቁሩ እንዳደረገኝ፣ በረቀቀ ዘዴ ቀስ በቀስ ከሰው ሁሉ እንደነጠለኝ፣ እንዴት ዋጋ ቢስ ነኝ ብዬ እንዳስብ፣ብቸኛ፣ ፈሪ፣ ጠርጣራና በእሱ ላይ ብቻ ጥገኛ እንድሆን እንዳደረገኝ ልንገራችሁማ፡፡ በእኔ ላይ የደረሰውን ቢያዩ እንደ ትግስት ዋልተንጉስ አይነቶቹ ባለሙያዎች፣ ‹‹ይሄ ሰው እዚህች ሴት ላይ የተጠቀመው የማታለል ዘዴ የመረጣትን ሴት ከምትወዳቸውና ከሚወዷት ሰዎች ለመነጠል፣ በራስ መተማመኗን ለመሸርሸር፣ በአጭር ገመድ ለማሰርና በመጨረሻም ተስማምታ በገነባቸው የስሜት እስር ቤት ውስጥ አንደ ባሪያ ለመግዛት ብዙ ጊዜ ስራ ላይ የሚውለውን ዘዴ ነው›› ሊሏችሁ ይችላሉ፡፡ እኔ ግን ነገር ሳላራቅቅ፣ የደረሰብኝን አንድ ሁለት እያልኩ፣ ፍትፍት -ብትንትን አድርጌማንበብ ይቀጥሉ... - [ደረሰ](https://shegerblogs.com/%e1%8b%b0%e1%88%a8%e1%88%b0/): ሕይወት አዲሱ ቦይፍሬንዷ ደረሰ ቤት ናት፡፡ ግንኙነታቸው የወራት ግን በፍጥነት እየጠበቀ ያለ ነው፡፡ ለወትሮው የአማካሪነት ስራውን በአመዛኙ ከቤቱ የሚሰራው ደረሰ ዛሬ ከጓደኞቹ ጋር ቁርስ ሊበላ በጠዋት ወጥቷል፡፡ ከጠዋቱ አምስት ሰዐት ቢሆንም እስካሁን በፒጃማ ስትንጎማለል የቆየችው ሕይወት የቤት ውስጥ ቢሮው ገብታ ልትሰልለው ወሰነች፡፡ ከደረሰ ጋር ፍቅር ከጀመረች አንስቶ እንዲህ ያለ ነገር አድርጋ አታውቅም፡፡ ከሳምንታት በፊት የላፕቶፕ ፓስወርዱን ‹‹ኢሜይል ቼክ ላድርግ›› ብላ ስትጠይቀው ያለማንገራገር ቢሰጣትም እንዲህ ያለው ነገር አልሞካከራትም፡፡ ታዲያ ዛሬ ለምን ልትሰልለው ወሰነች? ብዙ ምክንያት አላት፡፡ ገራገርና ሰው አማኝ፣ ለሳቀላት ሁሉ ምስጢሯን ዘርጋፊ ብትሆንም ከደረሰ በፊት የነበሩ ፍቅረኞቿ በሙሉ በብዙ አቅጣጫ ጎድተዋታል፣ በብዙ ስለት ብዙ ቦታ ወግተዋታል፡፡ ሁሉም እምነታቸውን አጉድለው ማግጠውባታል፡፡ማንበብ ይቀጥሉ... - [ጎስቋሎቹ](https://shegerblogs.com/%e1%8c%8e%e1%88%b5%e1%89%8b%e1%88%8e%e1%89%b9/): የማለዳ ጀምበር ጣሪያዬን ማሞቅ ሳትጀምር በፊት የአንድ ክፍል ቤቴ በር በእርጋታ ተንኳኳ። አባባ ናቸው፡፡ ክረምት በጋ ሳይሉ ዘወትር የሚለብሱትን አሮጌ ካፖርት ለብሰው ደጄ ቆመዋል፡፡ ካፓርቱ ከወትሮው የሰፋቸው ይመስላል፡፡ እንደዚህ ቀረብ ብዬ ባየኋቸው ቁጥር ከሲታ ሰውነትና ፊታቸው ይበልጥ ተጎሳቅሎ ይታየኛል፡፡ እንደሁልጊዜው በለሰለሰና ጨዋ አንደበታቸው፣ እንዴት ነህ ስራ እንዴት ነው? ደሴ ያለችው እናትህስ እንዴት ናት? አባትህ ተሸለው ወይ? እህትና ወንድሞችህ ደህና ናቸው? የሚሉ ጥያቄዎችን አከታትለው ጠየቁኝ፡፡ እንዳስለመድኳቸው፣ እኔ ደህና ነኝ እናቴም ይመስገን ደህና ናት አባዬ አገግሟል እህትና ወንድሜም ደህና ናቸው ብዬ በትህትና መለስኩላቸው፡፡ ከዚያ አዘጋጅቼ ያስቀመጥኩትን የቤት ኪራይ ገንዘባቸውን ሰጠኋቸው፡፡ “ዳዊት ልጄ” አሉኝ ብሩን ተቀብለው ከሸሚዝ የደረት ኪሳቸው ከጨመሩ በኋላ አንገታቸውን ሰበርማንበብ ይቀጥሉ... - [እየዘነበ ነው](https://shegerblogs.com/%e1%8a%a5%e1%8b%a8%e1%8b%98%e1%8a%90%e1%89%a0-%e1%8a%90%e1%8b%8d/): ከምሽቱ አስራ ሁለት ተኩል ገደማ ነው፡፡ሐይለኛ ዝናብ የቆርቆሮ ጣራዎችን እየደበደበ ይወርዳል፤ መንገዶች ላይ ትናንሽ ጅረቶችን ሰርቶ ይፈሳል፡፡ ከተማይቱ ለዝናብና ለቆፈኑ በጊዜ እጅ ሰጥታ እንቅስቃሴዋ ለዝቧል፡፡ሁለት ወጣት ፍቅረኛሞች በአንድ ክፍል ቤት ውስጥ ተቀምጠው ይጫወታሉ፡፡🌧🌧🌧🌧🌧🌧🌧🌧 - [የቱን ያስታውስ ይሆን?](https://shegerblogs.com/%e1%8b%a8%e1%89%b1%e1%8a%95-%e1%8b%ab%e1%88%b5%e1%89%b3%e1%8b%8d%e1%88%b5-%e1%8b%ad%e1%88%86%e1%8a%95/): ቀድማው ትነቃለች፡፡ምርጫ ስለሌላት ሆዷ እየተንቦጫቦጨ ጥላው ትሄዳለች፡፡ስራ ቦታ ስትሆን ‹‹ልጄ ልጅነቱን ሳላጣጥመው እያደገብኝ ነው›› ብላ ትብሰለሰላለች፡፡ከዳዴ ወደ እርምጃ በተሸጋገረበት ቀን ለመስክ ስራ አሶሳ ነበረች፡፡‹‹እሺ›› የምትለውን ቃል ለመጀመሪያ ጊዜ ከአንደበቱ ሲያወጣ በረጅም ስብሰባ ተጠምዳ ነበር፡፡ሞግዚቱን ‹‹ማማ›› ብሎ የጠራት ቀን ሽንት ቤት ተደብቃ አልቅሳለች፡፡ሞግዚቱ እረፍት የወጣች እለት ቀኑን ሙሉ ሲነጫነጭ በመዋሉ መጣሁ ብሎ ያስፈራራትን እንባዋን በመከራ ገትታለች፡፡በእሷ ተከፍቶና አልቅሶ ሞግዚቱ ጉያ ገብቶ ሲጽናና በሃዘን ተኮማትራለች፡፡ሞልቶላት ቤቷ ስትውል የልጇ ኮልታፋ አንደበት ስለማይገባት አሁንም አሁንም ሞግዚቲቱን ‹‹ምንድነው የሚለኝ?›› ብላ ትጠይቃለች፡፡ሞግዚቷ ‹‹ቼ ፈረሴ አጫውቺኝ ነው የሚልሽ››‹‹ምግብ አልፈልግም ነው ያለው›› እያለች ታስተረጉማለች፡፡ቤት ቤት ስትሆን ኢምፖርትድ አፕልና ብርቱካኑን ቃኘት፣ ውዱን የሳልመን አሳና ብሉ ቤሪ አየት፣ ቦታ ጠቧቸውማንበብ ይቀጥሉ... - [ሰሞንኛ](https://shegerblogs.com/%e1%88%b0%e1%88%9e%e1%8a%95%e1%8a%9b/): ስሙኝማ ! በቲቪ የኮመዲ ሾው እሚያቀርቡ ባለ መዋያዎች አሉ ፤ የአንጀራ ጉዳይ ሆኖባቸው ነው አንጂ በርግጥ አንዳንዶቹ መክሊታቸው ሌላ ነው፤ ወይ ጭራሽ መክሊት የላቸውም፤ እንደኔ እንደኔ፤ ልጆቻውን መክሊት ብለው ስም እንዲያወጡ ሊፈቀድላቸው አይገባም፤ እና ትንሽ የቸከ ጨዋታ ተረረር ያደርጉልንና በየሰክነዱ የብድር ሳቅ (laugh track ) ይለቁብናል። ዠለሶች! የእናንተ ድርሻኮ እንደምንም ተጣጥሮ መቀለድ ነው፤ መሳቁን ማለቴ አለመሳቁን ለምን ለኛ አትተውልንም? ታዳሚ ነን ስንል ታማሚ አረጋችሁንኮ ! እስቲ አስቡት ! የሆነ ቁርስ ቤት ገብታችሁ እዚህ ግባ እማይባል ዱለት ቀርቦላችሁ እየበላችሁ ፤ ሼፉ አጠገባችሁ ቆሞ “ አቤት ዱለት! ልብ እሚያጠፋ ጣእም ! “ እያለ ቢያዳንቅ አይደብራችሁም? እንደዚያ አድርጋችሁ አስቡት እንጂ ! ( አይማንበብ ይቀጥሉ... - [ሥራ ካለው ቦርጭ አለው](https://shegerblogs.com/%e1%88%a5%e1%88%ab-%e1%8a%ab%e1%88%88%e1%8b%8d-%e1%89%a6%e1%88%ad%e1%8c%ad-%e1%8a%a0%e1%88%88%e1%8b%8d/): ላግባ እንዴ ለምትል ላጤ ሴት ካገባችና ( እስካሁን) ደስተኛ በሆነ ትዳር ውስጥ ከምትገኝ ባለትዳር ሴት የቀረበ ምክረ ሃሳብ እንግዲህ ካገባሁ ሁለት አስርት ዓመታት ልደፍን ትንሽ ቀረኝ። ወቅቱ የሰርግ ነው፣ እኔም ቢከርምም ሙሽርነቴ በጥር ነበርና፣ እነሆ ስለትዳር ሃቅ ሃቁን መስማትን ለምትፈልጉ እንስቶች እቅጭ እቅጩን ፣ ነጭ ነጩን ሳላሞካሽ፣ ሳልቀባባ፣ እንደሚከተለው እመክራለሁ። ቅድመ-ጋብቻ —— ምርጫ ተትረፍርፎልሽ “ማንን ላግባ” በሚል የግርታ ጉም ተጋርደሽ ከሆነ ከዚህ በታች ያለው ሊጠቅምሽ ይችላልና አንብቢው፡፡ እቱ ገላ! ከሁሉ በፊት ይህንን እወቂ! አንድ) ለትዳር ብቁ የሆነ ወንድ… ስራ ካለው ቦርጭ አለው። ብር ካለው መላጣ ነው። ታታሪና ቤቴ ቤቴ ባይ አባወራ ሰላላ እግሮችና ነጋሪት ሆድ እንጂ ጡንቻና ሲክስ ፓክ ይለውም።ማንበብ ይቀጥሉ... - [ታሪክን ወደ ሁዋላና ወደፊት](https://shegerblogs.com/%e1%89%b3%e1%88%aa%e1%8a%ad%e1%8a%95-%e1%8b%88%e1%8b%b0-%e1%88%81%e1%8b%8b%e1%88%8b%e1%8a%93-%e1%8b%88%e1%8b%b0%e1%8d%8a%e1%89%b5/): ያልተበረዘውን የኢትዮጵያ ታሪክ የሚያነብ ሰው ፥ መጀመርያ የሚመጣለት ስሜት “ wtf ? ምን ጉድ ነው ?” የሚል ነው ፤ ለምሳሌ ነገስታት አንድ ልማድ ነበራቸው ፤ልክ ዙፋን ላይ ሲወጡ ልጆቻቸውን እና ወንድሞቻቸውን ሰብስበው ከመዲናቸው jራቅ ያለ ማጎርያ ቦታ ያስቀምጧቸዋል፤ የማጎርያው መልክአምድር ለማምለጥ አይመችም፤ ከዚያም አልፎ፤ በንቁና አስፈሪ ዘበኞች ይጠበቃል፤ በአክሱም ዘመን ደብረዳሞ የልኡላን ማጎርያ ሆኖ አገልግሏል፤ የሸዋ ነገስታት በተራቸው ሲገዙ፤ ለዚህ ተግባር የመረጡት ቦታ፥ ወሎ ዛሬ ግሼን ማርያም የምትገኝበትን አምባ ነበር፤ የጎንደር ነገስታት በበኩላቸው ዘመዶቻቸውን “ወህኒ” ወደ ተባለ ስፍራ ማጋዝ ጀመሩ፤ ወህኒቤት የሚለውን ቃል የወረስነው ከዚህ ስፍራ ነው ፤ ወህኒ በመሰረቱ የፖለቲካ እስር ቤት ሲሆን ፥የመጀመርያው የፖለቲካ ወንጀል ከንጉስ መወለድ ነበር፤ማንበብ ይቀጥሉ... - [ጠላታችን ሥም ነው!](https://shegerblogs.com/%e1%8c%a0%e1%88%8b%e1%89%b3%e1%89%bd%e1%8a%95-%e1%88%a5%e1%88%9d-%e1%8a%90%e1%8b%8d/): ሥም ከወላጅ የሚሰጠን ቅርስ ነው። በውስጡ ፍላጎት፣ እምነት፣ ፍቅር፣ ተስፋ…ያጨቁ እንድምታዎች ሊኖሩት ይችላሉ። በግብር የምንወርሳቸው ሥሞችም አሉ። የሆነ ተግባር ፈፅመን የምንደርባቸው አይነት። የሥም ዋና ጥቅሙ አንዱን ከአንዱን ለመለየት ይመስለኛል። ይህ ሆኖ ሳለ ግን ሥምን እንደ ማነፃፀሪያ መቁጠሩ እየተለመደ መጥቷል። የምናከብረው፣ ዋጋ የምንሰጠው፣ የምናስቀድመው የግለሰብ ማንነት ቀርቶ ሥምን ሆኗል። ሐብታም ለሚባል ስያሜ እናሸረግዳለን፤ የኔ ቢጤውን እናንቋሽሻለን። ለዶክተሩ ክብር ይኖረናል፤ ተራውን ዜጋ እንንቃለን። አንዱን ሰው ከሌላው፣ አንዱን ብሄር ተወላጅ ከሌላው፣ አንዱን ሐይማኖት ተከታይ ከሌላው የምንወደው፣ የምንጠላው…የምናከብረው፣ የምንንቀው…የምንቀርበው፣ የምንርቀው ማንነትን መሰረት አድርገን ሳይሆን ሥምን ተከትለን ነው። ግን ያልተገለፀልን ከሥም ሰው የመሆን ማንነት እንደሚቀድም ነው። በእኩል አይን ለመመልከት ሥም አያስፈልጋችሁም፤ ማንነት በቂ መሠረት ነው።ማንበብ ይቀጥሉ... - [ሕዝባዊ ሥነ-ቃሎቻችንን በጨረፍታ](https://shegerblogs.com/%e1%88%95%e1%8b%9d%e1%89%a3%e1%8b%8a-%e1%88%a5%e1%8a%90-%e1%89%83%e1%88%8e%e1%89%bb%e1%89%bd%e1%8a%95%e1%8a%95-%e1%89%a0%e1%8c%a8%e1%88%a8%e1%8d%8d%e1%89%b3/): የኛ ሕዝብ ሲከፋውም ሆነ ሲደሰት ሥነ-ቃሎችን ተጠቅሞ ብሶቱን፣ ችግሩንና ደስታውን ይገልፃል። ጉልበት ኖሮት በትር ባይወዘውዝም፣ ዘገር ባይነቀንቅምና ጠመንጃ ባይወድርም፣ ተንኳሹን፣ በዳዩን ወይም አጥቂውን ወገን በሥነ-ቃል ያለፍራቻ ያወግዛል። ይሄን ሲያደርግ እታሰራለሁ፣ እገረፋለሁ ወይም እሰቀላለሁ የሚል የፍራቻ ስሜት ልቡ ውስጥ ሽው የሚልበትም አይመስል። ይህ ዓይነቱ የሕዝብ እንደፈለገ ወይም እንዳሻው የመናገር ድፈረት በእጅጉ ያስደንቃል፤ ያስቀናልም። አንደው በሞቴ፣ በገና ጨዋታ ጊዜ አጤ ምኒሊክ በግላጭ የተተረቡባቸው (የተሸነቆጡባቸው) የተባሉት የሚከተሉት ዓይነት ሥነ-ቃሎች በአድናቆት አያስደምሙም? ቅማል ምን ታሳዝን ዳርዳሩን ስትባዝን፣ ራቷን ለቃቅማ እምን ስርፋ ትኛ (ትተኛ)! (አጤ ምኒሊክ መላጣ ነበሩ አሉ።) ታሪክ እንደሚነግረን ታዲያ የሄንን የገና ላይ ጨዋታ የሰሙት ነጉስ ምኒሊክ፣ “ተጫወቱ… ተጫወቱ…” በሚል ያበረታቷቸው ነበር ይባላል።ማንበብ ይቀጥሉ... - [ወዛደር እና ወዝውዞ አደር](https://shegerblogs.com/%e1%8b%88%e1%8b%9b%e1%8b%b0%e1%88%ad-%e1%8a%a5%e1%8a%93-%e1%8b%88%e1%8b%9d%e1%8b%8d%e1%8b%9e-%e1%8a%a0%e1%8b%b0%e1%88%ad/): በቀደም አንድ የተባረከ ዜጋ “የዶሮ በሽታ ገብቷል” ሚል ወሬ ነዝቶ የእንቁላልን ዋጋ ቁልቁል ወሰደው፤ አጋጣሚውን ለመጠቀም ሞከርኩ፤ የቤት ሰራተኛየ “ዛሬ ምን ይሰራልህ?” ስትለኝ “ ቆንጆ ሽሮ አንተክትኪልኝና አንድ አምስት የተቀቀለ እንቁላል ጣል አርጊበት” እላታለሁ፤ ከጥቂት ቀናት በሁዋላ የሆነ ክሊኒክ ምርመራ አደረግሁ፤ ኮሌስትሮል ውጤቴን ሲመለከቱ፥ ዶክተሮችና ነርሶች ተሰብስበው ተላቀሱ ፤ የክሊኒኩ ዘበኛ ግን “ አይዞህ ! በርሀብ ሞተ ከምትባል በኮሌስትሮል ብዛት ሞተ ብትባል ለስምህ ጥሩ ነው “ በማለት አጽናናኝ። በማግስቱ እዚህ ሀያ ሁለት ማዞርያ -ቺቺኒያ በሚገኘው ጂም ቤት Fitness dancing ተመዘገብኩና መስራት ጀመርኩ፤ “ምንድነው እምታደርጉት?” አለኝ ምኡዝ ፤ መስራት መጀመሬን የነገርኩት ቀን፥ “በጋራ እንወዛወዛለን፤ እንደንሳለን፤ “ “አላማው?” “ክብደት ለመቀነስ ይጠቅማል” ምኡዝማንበብ ይቀጥሉ... - [የአጎቴ አነቃቂ ንግግሮች እና የእኔ መፍዘዝ!](https://shegerblogs.com/%e1%8b%a8%e1%8a%a0%e1%8c%8e%e1%89%b4-%e1%8a%a0%e1%8a%90%e1%89%83%e1%89%82-%e1%8a%95%e1%8c%8d%e1%8c%8d%e1%88%ae%e1%89%bd-%e1%8a%a5%e1%8a%93-%e1%8b%a8%e1%8a%a5%e1%8a%94-%e1%88%98%e1%8d%8d%e1%8b%98/): እንደማንኛውም ዕድሜው ለማትሪክ የደረሰ ኢትዮጵያዊ ወጣት፣ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት መጥቶልኝ፣ ዩኒቨርሲቲ የመግባትና ተመርቆ የመውጣት ዕድል ገጥሞኛል። በዩኒቨርሲቲ ቆይታዬ አጎቴ ብዙ ምክርና ትንሽ የኪስ ገንዘብ በመላክ እያማረረ አስተምሮኛል። (አጎቴ ግን ለሰዎች ሲናገር “እያዝናናሁ አስተማርኩት” ነው የሚለው) የሚልክልኝ ብር በጣም ከማነሷ የተነሳ፣ አንዳንዴ እንደ ደሃ የሻምፖ ዕቃ፣ ኪሴን አለቅልቄ ነበር የምጠቀምባት። ተመርቄ እንደወጣሁ አጎቴ ድል ያለ ድግስ ደግሶ፣ ያንን ሁልጊዜ ፍርድ ቤት ሲሄድ የሚለብሰውን ሰማያዊ ኮትና ሱሪውን ለብሶና ነጭ ከረቫት አስሮ ፣ ለታዳሚው ረዘም ያለ የመክፈቻ ንግግር አደረገ። “አብርሃም ከድሮውም ገና ከልጅነቱ አንጎሉ ለትምህርትና ለነገር እንዲሁም ለእንስቶች ጨዋታ ክፍት ነበር፤ እንሆ አሁንም ከታላቁ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ዩኒቨርሲቲ በሳይኮሎጂ ተመርቆ አኩርቶናል” አለ። ታዳሚው ቀልቡንምማንበብ ይቀጥሉ... - [ካለመድረስ መድረስ!](https://shegerblogs.com/%e1%8a%ab%e1%88%88%e1%88%98%e1%8b%b5%e1%88%a8%e1%88%b5-%e1%88%98%e1%8b%b5%e1%88%a8%e1%88%b5/): አያልቅ የብሶት ገጽ ወዴትም ብንገልጠው፣ ሐዘን መጻፍ ነው ወይ ለኛ የተሰጠው ? አያልቅ የቀን መንገድ -ብንሄደው ብንሄደው፣ ፈቀቅ አይል ጋራው- ብንወጣ ብንወርደው፤ ረቂቅ ግዝፈቱ አይፈርስም ብ’ንደው፣ በ’ሳት ሰረገላ ሰማዩን አንቀደው! ምን ቢጠቁር ቆዳው -ምን ቢነጣ ፊቱ፣ ምን ቢሞላ ጓዳው- ቢራቆት ሌማቱ፣ ምድር ጥግ እስከጥግ አንድ ነው ሀለቱ፤ ሳይሻል አይቀርም እየሳቁ ማልቀስ፣ ሲጽፉት ይቀላል ፍቅርና ፤ መድረስ በወደብ ፍለጋ አትባዝን አትድከም፣ ጀልባህን ማክበድ ነው መልህቅ መሸከም፤ በዕንባ ባሕር ላይ በሳቅ ጀልባ መቅዘፍ፣ በሰፊው ሕይወት ላይ ሳይቆሙ መንሳፈፍ፣ ከየትም መነሳት ወደየትም ማለፍ፤ መድረሻህ ጉዞው ነው፣ በወደብ ፍለጋ ዛሬህን አትግደል፣ ያለውን መኖር ነው ነፍስን ማደላደል፤ ምን ቢደምቅ ስብከቱ -ሳይንስ ቢተነተን ፣ የሰው መዳረሻው-ማንበብ ይቀጥሉ... - [አንዳንዱ መፅሐፍ ...](https://shegerblogs.com/%e1%8a%a0%e1%8a%95%e1%8b%b3%e1%8a%95%e1%8b%b1-%e1%88%98%e1%8d%85%e1%88%90%e1%8d%8d/): ልድገመውና …ከአንድ ክፍለዘመን በፊት በፈረንጆቹ 1936 አንዲት ማርጋሬት ሜሸል የተባለች አሜሪካዊት ጋዜጠኛ እግሯን ወለም ብሏት አልጋ ላይ ዋለች …ታዲያ ስብራቷን እያዳመጠች ከማለቃቀስ ይልቅ በደጉ ጊዜ አእምሮዋ ውስጥ የተጠራቀመውን የአገሯን የእርስ በርስ ጦርነት ታሪክ መፃፍ ጀመረች … እንዲሁ በደረቁ ሳይሆን እንደኛው ፍቅር እስከመቃብር ዳር ዳሩን በፍቅር ታሪክ ዘምዝማ …. በዛ መፅሃፍ የአሜሪካ የእርስ በእርስ ጦርነት ምን ያህል የአገቱን ኢኮኖሚ እንዳመሸከው …መኳንትና መሳፍንቱ እንኳን ይደርቡት ካባ ይጎትቱት ቀሚስ … ለመቀመጫቸውም መሸፈኛ እራፊ ማግኘት መከራ እንደሆነባቸው የጦርነት አስከፊን ገፅታ ቁልጭ አድርጋ አሳይታበታለች ….…(የሰው አገር ጋዜጠኛ ተሰብሮ እንኳን በጥበብ አገር ይጠግናል😀) ቤተሰብ ብትንትኑ ሲወጣ የተፋቀሩ ሲለያዩ ሰዎች ሞራላቸው ሙቶ እንዲሁ የቁም ሬሳ ሁነው ሲንገላወዱማንበብ ይቀጥሉ... - [የወንዶች ሳሎን](https://shegerblogs.com/%e1%8b%a8%e1%8b%88%e1%8a%95%e1%8b%b6%e1%89%bd-%e1%88%b3%e1%88%8e%e1%8a%95/): በቀደም ዳጎስ ያለ ደመወዝ ተቀብየ ፥ ነጠር ነጠር እያልሁ በሰፈራችን ሳልፍ፥ “በውቄ ግባና ጸጉርህን ትንሽ ላሰማምርልህ “ የሚል ድምጽ ሰማሁ፤ የብዙ ዘመን ጸጉር አስተካካየ ሳሚ ነው ፤ ሚካያ በሐይሉ ‘ ጸጉሬንም ቆጥረሀል “ ብላ የዘፈነችው ለሳሚ ይመስለኛል፤ ሳሚ ፈጣን ነው ፤ ወሬ አያበዛም፤ በርግጥ ቶንዶሱ እንደ ጊንጥ ይቆነጥጣል፤ መቀሱንም በትርፍ ጊዜው የዳቦ ቆሎ እሚቆርጥበት ይመስለኛል ፤ ያም ሆኖ በሀያ ደቂቃ ውስጥ አሰማምሮ ይልከኛል፤ ሰባ ብር እከፍለዋለሁ፤ ሳሚ ብዙ አያወራም፤ደንበኞቹን አይሸነግልም፤ አንድ ቀን የሆነ ሰውየ ከመስተካከያው ወንበር ላይ ጉብ እንዳለ፥ “እንዴት ነው? ጸጉሬ ላይ ሽበት ጣል ጣል እያለበት ነው አይደል?” ሲል ሳሚን ጠየቀው፥ ምላሽ ሳይሆን ማጽናኛ ነበር የሚጠብቀው። ሳሚ ፥ ከቦረንቅማንበብ ይቀጥሉ... - [ቀውስጦስ የት ነው?](https://shegerblogs.com/%e1%89%80%e1%8b%8d%e1%8c%a6%e1%88%b5-%e1%8b%a8%e1%89%b5-%e1%8a%90%e1%8b%8d/): ከጥንት አዋልድ መጻህፍት ባንዱ ያነበብኩት ታሪክ ይህንን ይመስላል፤ ባንዱ መንደር በሚገኝ ቤተክርስትያን ውስጥ ቅዳሴ ይካሄዳል፤ ወላጆቻውን ተከትለው የመጡ ጥቂት ህጻናት ወድያ ወዲህ እየተራወጡ ቅዳሴውን መረበሽ ጀመሩ፤ እግዚር ከላይ ሆኖ ሲያይ ተቆጣ፤ ረባሽ ህጻናትን እንዲቀስፉ መላእክትን ላካቸው፤ መላእክት ወርደው የህጻናቱን አንገት በሰይፍ መቅላት ጀመሩ፤ በዚህ መሀል አንድ መላእክ ካንድ ህጻን ጋር ተገጣጠመ፤ መላእኩ፥ ህጻኑን የሚቀስፍበት አንጀት አልነበረውም፤ እና የእግዜርን ትእዛዝ ቸል ብሎ ህጻኑን ማረው፤ አሁን የእግዜር ቁጣ ከህጻናቱ ላይ ተነስቶ ትእዛዙን ባልፈጸመው መላእክ ላይ ሆነ፤ የመላእኩን ክንፍ አሽመደመደው! መላእኩ ለመብረር ሲሞክር ክፎቹ ከዱት፤ በቅጡ አስታውሸው ከሆነ ይህ መላእክ ሰሙ ቀውስጦስ ይባላል፤ ከተሳሳትሁ ዲያቆን ሄኖክ ያርመኛል፥ በጥንታዊ ተረካዎች ውስጥ ከማገኛቸው አንጸባራቂ የሞራልማንበብ ይቀጥሉ... - [ሰሞንኛ ጨዋታ](https://shegerblogs.com/%e1%88%b0%e1%88%9e%e1%8a%95%e1%8a%9b-%e1%8c%a8%e1%8b%8b%e1%89%b3/): ትናንት ቀለል ያለ ራት ለመብላት ፈለግሁ ፤ እናም” ባጫ ህንጻ “ውስጥ በሚገኘው የ”አማራ ባንክ” ቅርንጫፍ ጎራ ብየ በርከት ያሉ ሁለት መቶ ብሮችን ሸመጠጥሁ፤ ምግብ ቤት ገብቼ ፥ ምግቡ አላግባብ ውድ ከሆነብኝ ሂሳብ ለማካካስ ብዙ ነገሮች እጠቀማለሁ፤ ለምሳሌ ሬስት ሩም ገብቼ ለረጅም ጊዜ እቆያለሁ፤ ባጭሩ ፥ሬስት ሩምን ርስት ሩም አደርገዋለሁ፤ ያን ቀን ወደ ቤተ-ሰገራ ወሽንቤቱ ስራመድ መብራት ድርግምም አለ፤ ከግማሽ ሰአት የፈጀ ዘለግ ያለ ሽንት ሸንቸ ሳበቃ እያፍዋጨሁ ስወጣ የጽዳት ሰራተኛዋ፥ “ሴቶች ሽንት ቤት ውስጥ መሽናትህ የሚያሳፍር ነው” አለችኝ። “በዚህ ጨለማ ፥ ኪችን ውስጥ ባለመሽናቴ ልታደንቂኝ ይገባል “ ስላት ፈገግ አለችልኝ ፤ (ግን ጨለማ ከሆነ ፈገግታዋ እንዴት ሊታየኝ ይችላል ? ሰውማንበብ ይቀጥሉ... - [የሽግግር መንግሥቱ ትውስታ በጥቂቱ (1983-1987)](https://shegerblogs.com/%e1%8b%a8%e1%88%bd%e1%8c%8d%e1%8c%8d%e1%88%ad-%e1%88%98%e1%8a%95%e1%8c%8d%e1%88%a5%e1%89%b1-%e1%89%b5%e1%8b%8d%e1%88%b5%e1%89%b3-%e1%89%a0%e1%8c%a5%e1%89%82%e1%89%b1-1983-1987/): ትናንት በለጠፍኩት አንድ ጽሑፍ ግንቦት 19/1983 በለንደን ስለተከፈተው ኮንፈረንስ ተናግሬ ነበር። እስቲ አሁን ደግሞ የለንደን ኮንፈረንስ ቀጥተኛ ውጤት ስለነበረው የያኔው የኢትዮጵያ የሽግግር መንግሥት እናውጋ። ከግንቦት 19-20/1983 በተካሄደው የለንደን ኮንፈረንስ ላይ ዋነኛ ተሳታፊ የነበሩት አዲስ አበባን ጨምሮ አብዛኛውን የሀገሪቱን ክፍል የተቆጣጠረው ኢህአዴግ፣ በሀገሪቱ ምስራቅና ምዕራብ አካባቢዎች ብዙ ቦታዎችን የያዘው ኦነግ እና ኤርትራን ሙሉ በሙሉ የያዘው ህግሓኤ ናቸው። ***** በለንደን ኮንፈረንስ በተደረሰበት ውጤት መሰረት ኢህአዴግ በሽግግር መንግሥቱ የመሪነት ሚና እንዲኖረው የተወሰነ ሲሆን ኦነግ ደግሞ በመንግሥቱ ውስጥ ዋነኛው የስልጣን ተጋሪ ነበር። የሽግግሩ መንግሥት በይፋ የተመሠረተው ከሰኔ 23-27/1983 በተካሄደ ኮንፈረንስ ሲሆን ኮንፈረንሱ ሁለት ነገሮችን በማጽደቅ ነበር የተጠናቀቀው። እነርሱም የሽግግር ጊዜ መተዳደሪያ ቻርተር እና ለተወሰነማንበብ ይቀጥሉ... - [EPDA - በመጨረሻው ሰዓት የተገኘ አደገኛ ድርጅት](https://shegerblogs.com/epda-%e1%89%a0%e1%88%98%e1%8c%a8%e1%88%a8%e1%88%bb%e1%8b%8d-%e1%88%b0%e1%8b%93%e1%89%b5-%e1%8b%a8%e1%89%b0%e1%8c%88%e1%8a%98-%e1%8a%a0%e1%8b%b0%e1%8c%88%e1%8a%9b-%e1%8b%b5%e1%88%ad%e1%8c%85%e1%89%b5/): የደርግ መንግሥትን ለመደምሰስ ሲታገሉ የነበሩ ከደርዘን በላይ የሚሆኑ ድርጅቶች ነበሩ። ኢህአዴግ፣ ኦነግ እና ኢህአፓን የመሳሰሉት የታጠቀ ሰራዊት አስከትተው ሲዋጉ ነበር። አንዳንዶቹ ግን ሰራዊት ሳይኖራቸው በደርግ መንግሥት ላይ አደገኛ ፕሮፓጋንዳዎችንና ስውር የውስጥ ጥቃቶችን ሲያካሂዱ ነበር። ከነዚህም ውስጥ በብዙዎች ዘንድ ልዩ ትዝታን ጥሎ ያለፈው ድርጅት “የኢትዮጵያ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ትብብር” (በእንግሊዝኛው ምህጻር EPDA) ይባላል። ይህ ድርጅት በሲ.አይ.ኤ. ድጋፍ የተቋቋመ መሆኑ በደንብ ይታወቃል። የአሜሪካ መንግሥት በጊዜው ከፍተኛ የተባለ በጀት በመመደብ ይደጉመው ነበር። ኢፒዲኤ ይበልጥ የሚታወሰው መሰረቱን በካርቱም ከተማ ባደረገው Radio Free Ethiopia ሲያሰራጨው በነበረው ፕሮግራም ነው። በዚህ ፕሮግራም የተነሳ የደርግ መንግሥት ከሱዳን መንግሥት ጋር ውዝግብ ውስጥ ገብቶ ነበር። ከዚህ በተጨማሪም ድርጅቱ የደርግ ከፍተኛ ባለስልጣናትማንበብ ይቀጥሉ... - [ሽልማቱ](https://shegerblogs.com/%e1%88%bd%e1%88%8d%e1%88%9b%e1%89%b1-2/): “በምርጥ ነጠላ ዜማ ዘርፍ ያመቱ ኮከብ ተሸላሚ ማሞ መንገሻ “ ብሎ ለፈፈ ፥ የመድረክ መሪው አዳራሹ በጭብጨባ ተርገበገበ የማሞ ልብ በሀይል መምታት ጀመረ፥ ተሸላሚነቱን ከሰማ ጊዜ ጀምሮ መኪና እሸለማለሁ የሚል ሰመመን ጭንቅላቱን ተቆጣጥሮት ቆይቷል፤ ምን አይነት መኪና ይሆን እሚሸልሙኝ የሚል ሀሳብ ጠመደው፤ ወደ ሽልማቱ አዳራሽ የመጣው የሰፈሩን ላዳ ሹፌር አስቸግሮ ነው፤ በሰፈሩ የታወቀውን የላዳ ሹፌር ከዚህ በሁዋላ ማሞን በዱቤ ላለማጓጓዝ ምሎ ነበር፤ ይሁን እንጂ ማሞ ለሽልማት የታጨበትን መጥርያ ሲያሳየው ተረታ፤ ደንበኛው” ገንዘብ ከሸለሙኝ እስከዛሬ ያለብኝን እዳ እጥፍ አድርጌ እከፍልሀለሁ፤ መኪና ከሸለሙኝ ላንድ ወር ራይድ ትሰራባታለህ” የሚል ተስፋ ሰጥቶታል፤ ማሞ ከወንበሩ ተነስቶ ወደ መድረኩ አቅጣጫ ለመራመድ ሲቃጣ የፕሮግራሙ መሪ “ ማሞንማንበብ ይቀጥሉ... - [የተካደ ትውልድ](https://shegerblogs.com/%e1%8b%a8%e1%89%b0%e1%8a%ab%e1%8b%b0-%e1%89%b5%e1%8b%8d%e1%88%8d%e1%8b%b5-2/): የተካደ ትውልድ አይዞህ ባይ የሌለው ታዳጊ የሌለው ወይ ጠባቂ መላክ፥ ወይ አበጀ በለው ደርሶ ከቀንበሩ ፥የማይገላግለው፤ የተካደ ትውልድ አብዝቶ የጾመ፥ ተግቶ የጸለየ ጥቂት መና ሳይሆን፥ ጥይት ሲዘንብ ያየ እድሜ ይፍታህ ተብሎ፥ የተወለደ ለት አምባሩ ካቴና፥ ማተቡ ሰንሰለት፤ ምቾትን የማያውቅ፥ ረፍት የተቀማ አልጋው ያጋም እሾህ፥ ምኝታው የሳማ፤ የተካደ ትውልድ ሞቶ እንኳን ሬሳው፥ አይላላለት ቀንበር በዘብ እጅ ተገድሎ ፥ በሹም የሚቀበር ከጡት አስጥል በላይ፥ ኑሮ የመረረው እንዳይሄድ ጎዳናው ፥ የተደናገረው ድል ያልሰመረለት ፥ትግል ሳይቸግረው። የተካደ ትውልድ በስጋ በነፍሱ በቀልቡ በገላው ከቶ ምንድን ይሆን? ምንድን ይሆን መላው? (የማለዳ ድባብ፥ 28) - [አቦሌ](https://shegerblogs.com/%e1%8a%a0%e1%89%a6%e1%88%8c/): ከማውቃቸው ሰዎች መሀል በነውጠኝነቱ ወደር የሌለው አቦሌ ነው፤ ከብዙ ጊዜ በሁዋላ አንድ የጫማ መሸጫ ቤት ውስጥ ሳገኘው ገረመኝ፤ በፊቱ ያለው ውስብስብ ሰንበር የቀለበት መንገድ ይመስላል፤ ግንባሩ ላይ የብረት ቦክስ ጠባሳ አለ፤ ግራ ጉንጩ ላይ የሰንጢ ጭረት ይታያል፤ ማላመጫው ግድም የኮብልስቶን ምልክት ታትሟል። የባጥ የኮርኒሱን ስናወጋ ከቆየን በሁዋላ፤ “ስማ ፤ ያለፉትን አራት አመታት ብዙ መንፈሳዊ መጻህፍት በማንበብ አሳልፍያለሁ፤ ከራሴ ጋራ ተመካክርያለሁ፤ ሁሉንም አውጥቸ አውርጀ ጌታ ቡድሀን ተቀብያለሁ፤ የድሮው አቦሌ እንደሞተ ቁጠረው” አለና ትካዜ የተቀላቀለበት ፈገግታ አሳየኝ። ወድያው አንድ ሰውየ ገብቶ ንግግሩን አናጠበው፤ “ካልሲ አለ?” አለ ሰውየው፤ “ይሄ የጫማ መሸጫ ቤት ነው፤ ካልሲ እንዴት ትጠይቃለህ?’ አለ አቦሌ። “ጫማ ቤት ውስጥ ካልሲ መጠየቅማንበብ ይቀጥሉ... - [ሰይጣን ወይ እግዜር የጀመሩት... እኔ የቀጠልኩት (ክፍል ሃያ ሁለት)](https://shegerblogs.com/%e1%88%b0%e1%8b%ad%e1%8c%a3%e1%8a%95-%e1%8b%88%e1%8b%ad-%e1%8a%a5%e1%8c%8d%e1%8b%9c%e1%88%ad-%e1%8b%a8%e1%8c%80%e1%88%98%e1%88%a9%e1%89%b522/): (የመጨረሻው ክፍል) «ዶክተር ራሴን ሀኪም ቤት ካገኘሁት አልድንም ይብስብኛል እመነኝ! ትንሽ ቀን አይተኸኝ ከባሰብኝ ቃል እገባልሃለሁ ራሴው ሄዳለሁ» አልኩት። ከህክምና ጣቢያ ህክምናዬን መከታተል እንዳለብኝ ሲነግረኝ እቤቱ ይዞኝ ሄደ። በዚህ ጊዜ እንዳለፈው ለማላውቀው ጊዜ ያህል ጨለማና ፍርሃቴ ውስጥ አልነከርም!! አስፈሪው ደቂቃ ትንሽ ነው። ያቃተኝ እንቅልፍ ሲወስደኝ የምቃዠውን ቅዠት ነው። የእናቴ ሬሳ ሆኖ ይጀምራል። በእጄ እንደታቀፍኳት ማዕረግ ትሆንብኛለች። ወይም ሚስቴን! በሌላኛው ቀን ደግሞ ልክ የአባቷን ሞት ስትሰማ እጄ ላይ እንደወደቀችው ስትወድቅ እጀምራለሁ። እንደታቀፍኳት ወይ ማዕረግን ወይ እናቴን ትሆንብኛለች። ለቀናት መተኛት ፈራሁ። ዶክተር መድሃኒት አዘዘልኝ። ለሳምንታት እሱጋ ቆየሁ። አሁንም ግን እሱ የሚለውን ፋይል ለመክፈት ዝግጁ አልነበርኩም! እቤቴ ለመመለስ ዝግጁ ስሆን ተመለስኩ። ከተመለስኩ በኃላማንበብ ይቀጥሉ... - [ሰይጣን ወይ እግዜር የጀመሩት... እኔ የቀጠልኩት (ክፍል ሀያ አንድ)](https://shegerblogs.com/%e1%88%b0%e1%8b%ad%e1%8c%a3%e1%8a%95-%e1%8b%88%e1%8b%ad-%e1%8a%a5%e1%8c%8d%e1%8b%9c%e1%88%ad-%e1%8b%a8%e1%8c%80%e1%88%98%e1%88%a9%e1%89%b521/): ፅፎ እስኪጨርስ እረፍት አጣሁ። አስሬ ላይብረሪ እመላለሳለሁ። ጣቶቹ አሁንም 100% ስላልሆኑ ቀስ ብሎ ነው የሚፅፈው። «እሺ የፃፍከውን ላንብበውና ትቀጥላለህ?» እለዋለሁ። «አይሆንም ህፃን አትሁኚ!» ይለኛል። «ጮክ ብለሽ አታንብቢልኝ! የምትጠይቂኝ ነገር ከሌለ በቀር! ለራስሽ አንብቢው» ብሎኝ ሶፋው ላይ አጠገቡ እንድቀመጥ በእጁ እየመታ አሳየኝ። መስገብገቤ የሆነ እርቦት ውሎ ምግብ እንደሰጡት ርሃብተኛ ነው። «ከድምፅ ጋር የተለየ ፍቅር አለኝ። ሰውን ሳላየው በድምፁ ብቻ መልክ እስላለሁ። ከድምፁ ቃና ፐርሰናሊቲውን መገመት ደግሞ የበለጠ ደስ ይለኛል። ሬስቶራንት ውስጥ ከጀርባዬ ድምፅዋን ስሰማው ጠይም ጎራዳ ፣ ጥርት ያለቆዳ ያላት ፣ ጥርሷ የሚያምር ፣ ከንፈሯ ስስ ……… ገመትኩ። ድምፅዋ ውስጥ የዋህነት ደግሞ ለዛ ሙሉነት ነበር በመጀመሪያ የሰማሁት። ዞሬ ሳላያት ከውጪ ከመጡማንበብ ይቀጥሉ... - [ሰይጣን ወይ እግዜር የጀመሩት... እኔ የቀጠልኩት (ክፍል ሀያ)](https://shegerblogs.com/%e1%88%b0%e1%8b%ad%e1%8c%a3%e1%8a%95-%e1%8b%88%e1%8b%ad-%e1%8a%a5%e1%8c%8d%e1%8b%9c%e1%88%ad-%e1%8b%a8%e1%8c%80%e1%88%98%e1%88%a9%e1%89%b5-20/): እና ሰዓት ብላችሁ ከመነጫነጫችሁ በፊት ይቅርታ ብያለሁ!! ሜሪ ፈለቀ ከማይታይ ፊርማጋ ) «ትናንትህ ላይ በበደሉህ ሰዎች ነው ዓለምን በሙሉ እየዳኘህ ያለኸውኮ! በዙሪያህ ያሉ ሰዎች በሙሉ እንደእነሱ ናቸው ማለት አይደለም! በተቃራኒው የሆኑ ሰዎች አሉ። አንተ ያደረግከው ለማንም ምንም እድል አለመስጠትን ነው።» ከምሳ በኋላ ፀሃይ ቡና አፍልታ ሳሎን ቡናችንን እየጠጣን ነው ስላለፉት ውሳኔዎቹ የጀመርነውን የሀሳብ ልውውጥ የቀጠልነው። «ካለፈው ውድቀትሽ ወይም ስህተትሽ መማር ማለት ታዲያ ምንድነው? ትናንቴን አልደግምም ማለት አይደል? ያለፈውን ስህተትሽን አለመድገም አይደል? ያለፈው ስህተቴ አለልክ ሰዎችን ማመኔ ፣ ያለገደብ ራሴን እስኪያሳጣኝ ከሰው ጋር መቆራኘቴ አይደል? ያንን ነው ያስወገድኩት!! የሰዎችን ስሜት ለውጥ፣ ክፋት ወይም ቅንነት ልትቆጣጠሪ አትችዪም። ልትቆጣጠሪ የምትችዪው የራስሽን ስሜት እናማንበብ ይቀጥሉ... - [ሰይጣን ወይ እግዜር የጀመሩት... እኔ የቀጠልኩት (ክፍል አስራ ዘጠኝ)](https://shegerblogs.com/%e1%88%b0%e1%8b%ad%e1%8c%a3%e1%8a%95-%e1%8b%88%e1%8b%ad-%e1%8a%a5%e1%8c%8d%e1%8b%9c%e1%88%ad-19/): «ማዕረጌን ከጎኔ አድርጌ የተጋበዝነውን እራት ልንታደም ስንሄድ ዘውድ እንደተደፋለት ልዑል አንገቴን ቀና አድርጌ በኩራት ነበር። ምንም የጎደለኝ ነገር አልነበረም። ማዕረጌ ከጎኔ ነበረቻ!! ከሶስት ሳምንት በኋላ እሷ እንደተመኘችው በሷው አባባል <እልልልልልልል በተባለለት ሰርግ> ወዳጅም ጠላትም ምስክር ሆኖ ባደባባይ የእኔ ልትሆን ነዋ!! ዓለም የእኔ ብቻ ነበረች። የሆነኛው ዓለም በጦርነት ንፁሃን እንደማይሞቱ፣ የሆነኛው ሀገር ህፃናት በርሃብ እንደማይሞቱ፣ የሆነኛው የዓለም ክፍል በተፈጥሮ አደጋ እንደማይተራመስ ……… በቃ ከእኔና ከእሷ ውጪ ሌላ ምንም ዓለም እንደሌለ …… ዓለም በእኔና በእሷ ዙሪያ ብቻ እንደምትዞር …… ዓለሜ እሷ ብቻ እንደሆነች ….. እንደዛ እያደረገኝ ነበር። ፈጣሪን ለሰጠኝ ዓለም እየደጋገምኩ አመሰግነው ነበር። የሚመጣውን ሰርጋችንን እና እርቁን አስመልክቶ የተወሰነ የማውቃቸው ጎረቤቶች እናማንበብ ይቀጥሉ... - [ኑሮ እና ብልሀቱ](https://shegerblogs.com/%e1%8a%91%e1%88%ae-%e1%8a%a5%e1%8a%93-%e1%89%a5%e1%88%8d%e1%88%80%e1%89%b1/): የወሎ መንፈስ አድናቂ ነኝ፤ ስለወሎ ሲነሳ ይቺ ወግ ትዝ ትለኛለች፤ አንድ ሼህ እና አንድ ቄስ ወደ መስጊድ እየሄዱ ነው፤ ምንም አገሩ ወሎ ቢሆን ቄስና ሼህ ባንድ ላይ ወደ መስጊድ ሊሄዱ አይችሉም ልትሉኝ ትችላላችሁ፤ እሺ በቃ ፥ ቄሱ ሼሁን ወደ መስጊድ እየሸኘው ነው፤ እንዲያውም ምን አጨቃጨቀኝ፤ ቄሱና ሼኩ ወደ ገበያ እየሄዱ ነው፥ “ቄሱ” አይዋ! እንዲያው በሰማይ ቤት ከክርስትያን እና ከእስላም ማን የሚኮነን ይመስልሀል?” ብሎ ጠየቀ ሼሁ ፥ትንሽ ካሰበ በሁዋላ፥ “እንጃ ! ብቻ ተሁለት አንዱ አሩን የሚበላ ይመስለኛል” ብሎ መለሰ። በተወሳሰበው ማህበራዊ ህይወታችን ውስጥ “የኔ መንገድ ብቻ ነው መዳኛ ብለው የሚያምኑ ሰዎችን ያህል አደገኛ የለም፤ “እንጃ ፤ ይመስለኛል፤..” የሚሉና ለሌላው እድል የሚሰጡማንበብ ይቀጥሉ... - [ሰይጣን ወይ እግዜር የጀመሩት... እኔ የቀጠልኩት (ክፍል አስራ ስምንት)](https://shegerblogs.com/%e1%88%b0%e1%8b%ad%e1%8c%a3%e1%8a%95-%e1%8b%88%e1%8b%ad-%e1%8a%a5%e1%8c%8d%e1%8b%9c%e1%88%ad-%e1%8b%a8%e1%8c%80%e1%88%98%e1%88%a9%e1%89%b518/): «ታውቂያለሽ የአዕምሮ ክፍላችን እድገት በ25 ዓመታችን እንደሚያበቃ? ከዛም ውስጥ ከ80% በላዩ የሚያድገው እስከ 5 ዓመት አካባቢ ባለው እድሜያችን ነው። ጥናቶች እንደሚያሳዩት የሰው ልጅ ከ25 ዓመቱ በፊት በሚያዳብረው ልምድ ፣እውቀት ፣ ባህል ፣ ሀይማኖት ……. Whatever ነው የሚቀረፀው። ልክ አለመሆኑን ቢያውቅ እንኳን ለመቀየር ብዙ ጥረት እና ጊዜ ይወስድበታል። ከዛ በኋላ ባለን እድሜ ምንም ያህል እውቀት እና ልምድ ብናዳብር እንኳን ሳናውቀው በsubconscious የአዕምሮ ክፍላችን አማካኝነት አስቀድመን ወዳዳበርነው ልምድ እና እውቀታችን ስንሳብ እንገኛለን።» አለኝ። አደጋው ከደረሰበት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የህፃናት ማቆያውን ሊጎበኝ መጥተን ነው። ለህፃናቱን እኔ እየተመላለስኩ መጠየቅ አላቆምኩም ነበር እና አባታቸው አደጋ እንደደረሰበት አስቀድመው ያውቃሉ። ከበውት <እግዜአብሔርን አጊንተኸው ነው የተመለስከው?> ዓይነት የህፃንማንበብ ይቀጥሉ... - [ምንሽን](https://shegerblogs.com/%e1%88%9d%e1%8a%95%e1%88%bd%e1%8a%95-2/): የሰው አገር ሙጥኝ ብየ፥ በወጣሁበት እንዳልቀር አገሬ ፍቅርሽ ሳበኝ፥ ግና ምንድር ነው ማፍቀር እንዳስመሳይ አዝማሪ፥ ካልሸነገልኩሽ በቀር ከተወለድሁ እስከዛሬ፥ ከጣቶችሽ መች ጎርሼ ወተትሽን መች ቀምሼ ወለላሽን መቸ ልሼ ሲርበኝ ጠኔ በቀኝ በግራ፥ እንደ ጭፍራ ሲከበኝ የት ነበር የንጀራሽ ሌማት ሾላ ስለቅም ተሻምቼ፥ ከሽመላ ከማማት ኑሮየ ሁዳዴ ጦም፥ ፋሲካ አልባ ህማማት። እና ከድሎት አገር ፥ የሲሳይ ዶፍ ከሚያወርደው ምን ገፍቶኝ ነው በሞቴ፥ ወዳንቺ የምሰደደው ? ምን ነክቶኝ ነው? ምንሽን ነው የምወደው? እኔና ብጤዎቼ፥ እኛ ቅብዝብዝ ልጆችሽ መስኮት በሩ ተዘግቶብን፥ ተበትነን በደጆችሽ ይሄው ሶስት ሺ ዘበን፥ ወደ ሰማይ አንጋጠን በንዝርት እግር ተንበርክከን ፥ በቀይ እንባ ስንማጠን የለት እንጀራችንን ነፍጎ፥ የእለት ገጀራችንን ሰጠን።ማንበብ ይቀጥሉ... - [ሰይጣን ወይ እግዜር የጀመሩት... እኔ የቀጠልኩት (ክፍል አስራ ሰባት)](https://shegerblogs.com/6338-2/): «አንተ እረፍ ልመለስ! ያወቀ እንደሆነ ደግሞ ዲዳ ሆኖ ሀሁ ሳስቆጥረው ልክረም?» የሚለውን ሳቃቸው ያጀበውን ድምፅዋን ነው። ሳቃቸውን ሳይጨርሱ ብቅ ሲሉ መንቀሳቀስ አቅቶኝ እንደቆምኩ ነበር። > የሚለውን እንደፃፍኩ አቁሜ « በመድሃንያለም !ውይ ምን ሆና ነው?» አልኩኝ ራሴው ቁዝም ብዬ «ሰው! ሰው ሆና ነው! የትኛውስ ሰው ቢሆን እንዲህ አይደለም?» «ይሄ ሰውነት አይደለም!!» ለወሬ እየተቅለበለብኩ ኮንፒውተሩን መሬት ላይ አስቀምጬ በጉልበቴ መሬቱ ላይ ተንበርክኬ ወደእርሱ እየዞርኩ። «ትክክለኛ ሰውነት ውስጥ ክህደት የለም። ሰውነት ተፈጥሮ ነውኮ እንዴ? ልክ እና ስህተትን በሚያሰላ ህሊና በሚባል ሞተር የሚዘወር ተፈጥሮ ነው። የማንበብህ ብዛት፣ ሀይማኖት፣ የልምድህ ክምችት አልያም ስልጣኔህ ወይም ህግ የሚሰጥህ ነገር አይደለም።» «ህሊና ከጠቀስቻቸው ዝርዝሮች ተፅዕኖ በላይ አይደለም።» «በሱማንበብ ይቀጥሉ... - [ሰይጣን ወይ እግዜር የጀመሩት... እኔ የቀጠልኩት (ክፍል አስራ ስድስት)](https://shegerblogs.com/%e1%88%b0%e1%8b%ad%e1%8c%a3%e1%8a%95-%e1%8b%88%e1%8b%ad-%e1%8a%a5%e1%8c%8d%e1%8b%9c%e1%88%ad-%e1%8b%a8%e1%8c%80%e1%88%98%e1%88%a9%e1%89%b516/): «ስድስት ዓመት ሙሉ ምን ዓይነት ቀኖች እንደነበሩህ ለአንባቢ ምንም ፍንጭ ሳትሰጥ 20 ዓመትህ ላይ ወደ ሆነ ታሪክ መሄድ ታሪኩን አያጎድለውም?» «ምንም የሚፃፍ ታሪክ የለውም። ፊልም ቢሆን (በጭንቅላቱ ምስሉን እየከሰተ) ምን ዓይነት ትራንዚሽን መሰለሽ? ማታ 14 ዓመቱ ላይ ተኝቶ ጠዋት 20 ዓመቱ ላይ ሲነቃ የሚያሳይ ሲን ነው የሚሆነው።» ላይብረሪው ውስጥ ዊልቸሩ ላይ ለሰአታት ከሚቀመጥ በሚል ባስገባነው ሶፋ ላይ እሱ ጋደም ብሎ። እኔ መሬቱ ላይ ተቀምጬ ሶፋውን ተደግፌ ባዮግራፊውን መፃፋችንን እየቀጠልን ነበር። ከምንፅፈው በየመሃሉ የምናወራው ይበልጣል። «አባትህ? እንጀራ እናትህ? ወንድምህ? ከነርሱጋር የነበረህ ግንኙነት? ትምህርት ቤት? ጓደኛ ? የሆነ የሚወራ የሚወሳ ይኖረዋል። ለህፃን አይደለም ለአዋቂ የሚከብድ ሰቀቀን ያሳለፈ ህፃን እንደማንኛውም ልጅ የተለመደ ዓይነትማንበብ ይቀጥሉ... - [ሰይጣን ወይ እግዜር የጀመሩት... እኔ የቀጠልኩት (ክፍል አስራ አምስት)](https://shegerblogs.com/%e1%88%b0%e1%8b%ad%e1%8c%a3%e1%8a%95-%e1%8b%88%e1%8b%ad-%e1%8a%a5%e1%8c%8d%e1%8b%9c%e1%88%ad-%e1%8b%a8%e1%8c%80%e1%88%98%e1%88%a9%e1%89%b515/): ሲመስለኝ ፍቅርም ይረታል። በቁጣ ፣ በክፋት እና በበቀል ይረታል። ወይም ምናልባት እሱን ከማይመስሉ ባህርያት ጋር ግብ ግብ አይገጥም ይሆናል እና ቦታ ይለቃል። ቀስ በቀስ ቁጣ እና መከፋቴ ፍቅሬን እየሸፈነው መጣ። እዚህ ነጥብ ላይ የማስበው ሁሉ በምን መንገድ እኔን ማጣቱ እንዲቆጨው፣ እንዲፀፀት፣ የእግር እሳት እንዲሆንበት እንደማደርገው ነው። በቀል መሆኑ ነው!! በምትኩ በነገረ ስራው የምነደው እኔ ነኝ። ያቺን ከሱሉልታ ፒያሳ የሚሰማ ሳቅ የምታንባርቀውን ሴት እቤቴ ይዟት ከመጣ በኋላ ለሳምንታት ቃላት አልተቀያየርንም። የተያየነውም ለሆኑ ሰከንዶች ያህል ቢሆን ነው። ምግቤን ክፍሌ አስመጣለሁ። ማንበብ የምፈልጋቸውን መፅሃፍት ክፍሌ ይዤ እገባለሁ። (እሱ ከሰጠኝ ስጦታዎች ሁሉ ሳመሰግነው የምኖረው ከማንበብ ጋር በፍቅር እንድወድቅ ስላደረገኝ ነው።) የሆነ ቀን እሁድ ከሰዓትማንበብ ይቀጥሉ... - [ሰይጣን ወይ እግዜር የጀመሩት... እኔ የቀጠልኩት (ክፍል አስራ አራት)](https://shegerblogs.com/%e1%88%b0%e1%8b%ad%e1%8c%a3%e1%8a%95-%e1%8b%88%e1%8b%ad-%e1%8a%a5%e1%8c%8d%e1%8b%9c%e1%88%ad-%e1%8b%a8%e1%8c%80%e1%88%98%e1%88%a9%e1%89%b514/): «ታዲያ ቢያንስ ልታሳውቂኝ አይገባም ነበር? እኔ ምን አግብቶኝ ነው የአባትሽን ቁማር ቅሌት የምሸፍነው? ከዛሬ በኋላ ከገንዘቤ ላይ በዚህ ሰበብ ቤሳቤስቲን እንዲነሳ አልፈልግም።» አለኝ የብዙ ሰዎች ባህሪ መሰለኝ። እየተገፋን እና በፍቅር የወደቅንለት ሰው በማይገባን መልኩ ክፋትና ጥላቻ እያሳየን ያየነውን መመዝበር አምነን ልባችንን ከመሰበር እንደመጠበቅ ይልቅ እዛው እንቆያለን። ምክንያቱም ከሰውየው እውነተኛ የሚታይ ባህሪ ይልቅ ሰውየው ነው ብለን በልባችን የሳልነውን ምስል እናምናለን። ከዛም አንዴም አይደለም ሁለቴም አይደለም። እየደጋገመ በማይገባን መንገድ ክፉውን እሱነቱን ያሳየንና ልባችንም ተሰብሮ ፣ ሞራላችንም ደቆ፣ ከክብራችንም አንሰን ፣ በፍቅር ልባችን ውስጥ የተሳለውንም ምስል በአውሬ ተክተን ………… ያኔ እናምናለን። በዜሮ አማራጭ እና በሚያነክስ ልብ እንለያያለን። «በየወሩ የሚቆረጠው ብዙ ብር ስላልሆነ ነበርማንበብ ይቀጥሉ... - [ያ’መት በዓል ማግስት ትእይንቶች](https://shegerblogs.com/%e1%8b%ab%e1%88%98%e1%89%b5-%e1%89%a0%e1%8b%93%e1%88%8d-%e1%88%9b%e1%8c%8d%e1%88%b5%e1%89%b5-%e1%89%b5%e1%8a%a5%e1%8b%ad%e1%8a%95%e1%89%b6%e1%89%bd/): የሞላ ሽንት ቤት ጭር ያለ ቤተሰብ የተጠረገ ድስት፥ ድርቅ የመታው ሞሰብ፥ ያደፈ ቄጤማ በበግ በሰው እግር ፥የተደቀደቀ ወዙ ባንድ ሌሊት፥ ተመጦ ያለቀ መጥረጊያ ሚጠብቅ ፥ወድቆ ተበታትኖ ትናንት ጌጥ የነበር፥ ዛሬ ጉድፍ ሆኖ፥ የተወቀጠ ፊት ፥ የነጋበት ድንገት በዳንኪራ ብዛት፥ወለም ያለው አንገት። የዞረበት ናላ ፥ጌሾ ያበከተው እንኳንስ መገንዘብ፥ መጀዘብ ያቃተው። የወለቀ ወገብ፥ የዛለ ትከሻ መኪና ይመስል፥ ብየዳ የሚሻ። የጠጅና የጢስ ፥ድብልቅ እስትንፋስ ከሆድ ሸለቆ ውስጥ፥ የታፈነ ነፋስ ባንጀት የታሰረው እንደተከበበ አመጸኛ ሽፍታ፥ መውጫ የቸገረው ፥ የማይፈካ ሰማይ፥ የማይዘንብ ደመና በላባና በፈርስ፥ ያደፈ ጎዳና በበግ የራስ ምላስ የተልከሰከሰ የጠገበ ውሻ በመንፈቅ አንድ ጊዜ ፥ አጥንት የቀመሰ ፥ ሀንጎበር ያዛገው ፥ መሂና አሽከርካሪማንበብ ይቀጥሉ... - [ሰይጣን ወይ እግዜር የጀመሩት... እኔ የቀጠልኩት (ክፍል አስራ ሶስት)](https://shegerblogs.com/%e1%88%b0%e1%8b%ad%e1%8c%a3%e1%8a%95-%e1%8b%88%e1%8b%ad-%e1%8a%a5%e1%8c%8d%e1%8b%9c%e1%88%ad-%e1%8b%a8%e1%8c%80%e1%88%98%e1%88%a9%e1%89%b513/): «ሁሉም ሰውኮ አንድ የሆነ ስስ የሆነበት ጎን አለው። ሰዎች ስስ ጎንህን ማወቃቸው ሁሌም መጥፎ ነገር አይደለም። በእርግጥ አንዳንድ ሰዎች ድክመትህን ለመጥፎ ቀን አንተን ለመጣያ ጥይት አድርገው ሊጠቀሙበት ያስቀምጡታል። ለማን ምን ልንገር የሚለው ይመስለኛል እንጂ የሚወስነው ………..» ከአፌ ነጥቆኝ ቀጠለ «ሁሉም ድክመትሽን የነገርሽው ሰው ድክመትሽን በነገርሽው ሰዓት ይረዳኛል ያልሽው፣ ወዳጄ ያልሽው፣ ያዝንልኛል ያልሽው፣ የኔ ነው ያልሽው…….. ሰው ነው የሚሆነው። አብዛኞቻችን ስንወዳጅ እንለያየን ወይም እንጣላለን ብለን አስበን አይደለም እና ቁስልሽን ቀምሞ አንቺኑ የሚጥልበት ጥይት እንደሚያደርገው የምትረጂው በሆነ ነገር ሳትስማሙ ስትቀሩ እና ስትለያዩ ነው። አየሽ እኔ ደግሞ ትዳርን ጨምሮ ምንም አይነት በሰዎች መሃል ያለ መስተጋብር አንድ ቀን እንደሚፎርሽ አውቃለሁ። ያ ማለት ሳትለያዪም ሚስቴማንበብ ይቀጥሉ... - [ሰይጣን ወይ እግዜር የጀመሩት... እኔ የቀጠልኩት (ክፍል አስራ ሁለት)](https://shegerblogs.com/%e1%88%b0%e1%8b%ad%e1%8c%a3%e1%8a%95-%e1%8b%88%e1%8b%ad-%e1%8a%a5%e1%8c%8d%e1%8b%9c%e1%88%ad-%e1%8b%a8%e1%8c%80%e1%88%98%e1%88%a9%e1%89%b512/): «ዝናቡ ፀቡ ከምሽቱ ጋር ይሁን ከእርሱ ጥበቃ ጋር አይገባውም። የጠቆረው ሰማይ እያፏጨ ያለቅሳል። ……… » «የመብረቁ ብልጭታ ምናምን ምናምን ብለህ አትቀጥልማ?» ከት ብሎ ሳቀ በድጋሚ ሌላ ቀን ባዮግራፊውን ልንፅፍ ተቀምጠን ነው ከምን እንደምንጀምር ላልቆጠርነው ጊዜ የምንጀምር የምንሰርዘው። ዛሬ ባልተለመደ ሁኔታ ጥሩ ሙድ ላይ ነው። «why not?» አለው አይደል እየሳቀ የሚያወራበት ድምፁ? «come on you are better than this! ሰማዩ የአህያ ሆድ ሲመስል፣ ፀሃይዋ ብርቱካንማ ሆና ስትንቀለቀል አይነት ጅማሬ አንተ ብትሆን ይስብሃል? ተረኩን እያስኬድከው ባለታሪኩ ያለበትን ቦታና ሁኔታ ከታሪኩ ስሜት ጋር ተያያዥነት ካለው ሳለው። ካለዚያ ግን ምንድነው ዝናቡ፣ መብረቁ ? ዝናብ ከሆነ ሰማዩ እንደሚጠቁርና መብረቅ እንደሚኖር አንባቢው የሚያውቀውን እውነት እየደጋገሙ ማደናቆርማንበብ ይቀጥሉ... - [ሰይጣን ወይ እግዜር የጀመሩት... እኔ የቀጠልኩት (ክፍል አስራ አንድ)](https://shegerblogs.com/%e1%88%b0%e1%8b%ad%e1%8c%a3%e1%8a%95-%e1%8b%88%e1%8b%ad-%e1%8a%a5%e1%8c%8d%e1%8b%9c%e1%88%ad-%e1%8b%a8%e1%8c%80%e1%88%98%e1%88%a9%e1%89%b511/): እሱን ዞሬ አየሁት! መልሼ እነሱን አየሁ! እግሬ መቆም አቃተው! ዘሎ እጆቹን ከስሬ ሲያነጥፋቸው፣ እጁ ላይ ራሴን ስጥል፣ አይኔ ከመከደኑ በፊት ከጉሮሮው የማይወጣ ጩኸት እያማጠ ሊጮህ ሲታገል አየዋለሁ። ስቃይ ያለበት ፊት………. ሰከንዶች ወይ ደቂቃ አላውቅም እጁ ላይ ምንያህል እንደቆየሁ ግን እንደነበርኩ መሬቱ ላይ ስለሆነ የነቃሁት ብዙም ጊዜ እንዳልሄደ ገምቻለሁ። የረጠበ ፎጣ ደረቴና ግንባሬ ላይ አድርጎልኝ እሱ ቁና ቁና እየተነፈሰ ነቃሁ። ተጠርቶ ይሁን ማወቅ ያልቻልኩት ጎረቤት ያለው ሰውዬ ተሸክመው ወደ መኪናው እንዲወስዱኝ ይወተውታል። መርዶ ሊያረዱኝ የመጡት ሰዎች ይተረማመሳሉ። ፀሃይ ፀሎት ይሁን ወቀሳ ያልለየለት ማልጎምጎም ለአምላክም ለእኛም ታሰማለች። መተንፈስ አቅቶት ሲጨነቅ እሱን ያየው የለም። የተንተራስኳቸው እግሮቹ ይንቀጠቀጣሉ፣ ፎጣ የያዙት እጆቹ ይንቀጠቀጣሉ። ግንባሩ ላይማንበብ ይቀጥሉ... - [የሚያሳስበኝ](https://shegerblogs.com/%e1%8b%a8%e1%88%9a%e1%8b%ab%e1%88%b3%e1%88%b5%e1%89%a0%e1%8a%9d/): ይሄ ጨዋታ አይደለም፥ በቀደም ከሜክስኮ ወደ ፒያሳ የሚያወጣውን የቸርቺል አቀበት ስወጣ ሁለት ጎረምሶች ከግራ ቀኝ አጀቡኝ፤ አንዱ ናፕኪን እንድገዛው ጠየቀኝ ፤ ቸል ብየው ተራመድሁ፤ ከቀኘ ያለው ጎረምሳ ክንዴን አፈፍ አድርጎ ይዞ “ብራዘር ርቦኛል የዳቦ መግዣ ስጠኝ” አለኝ፤ ጣቶቹ ክንዴን ላይ የካቴና ያክል ከበዱኝ፤ ልመና ሳይሆን ልዝብ እገታ ይመስላል፥ በተቻለኝ መጠን ኮስተር ብየ ክንዴን እንዲለቀኝ ወተወትኩት፥ አለቀቀኝም፤ ናፕኪን የሚሸጠው ጉዋደኛውን “ልቀቀው ፤” ብሎ ከገሰጸው በሁዋላ “ግን ርቦን ነው” የሚል ቃል ጨመረ፤ ድርድር መጀመሩ ነው፥ አስራ አምስት ብር መጽውቸ ተገላገልሁ፤ ወይም ለጊዜው የተገላገልሁ መሰለኝ። ከጥቂት ቀናት በፊት ደግሞ ከፒያሳ ወደ ቀበና ስረማመድ ቱሪስት ሆቴል አካባቢ አንዲት ትንሽየ ልጅ እየሮጠች መጣችና ሱሪየን ይዛማንበብ ይቀጥሉ... - [ሰይጣን ወይ እግዜር የጀመሩት ….. እኔ የቀጠልኩት (ክፍል አስር)](https://shegerblogs.com/%e1%88%b0%e1%8b%ad%e1%8c%a3%e1%8a%95-%e1%8b%88%e1%8b%ad-%e1%8a%a5%e1%8c%8d%e1%8b%9c%e1%88%ad-%e1%8b%a8%e1%8c%80%e1%88%98%e1%88%a9%e1%89%b5-10/): «የእናቱን ለቀናት የቆየ የሚሸት ሬሳ ታቅፎ ከጎሮሮው የማይወጣ ጩኸት ጮኸ። ድምፁ ከጉሮሮው እንደማይወጣ ቢያውቅም በሆነ ተዓምር የሆነ ሰው እንዲደርስለት ተመኘ። በማይሰማ ድምፅ ሊደርስለት የሚችለው እግዚአብሔር ብቻ እንደሆነ ስላወቀ አይኞቹን ጨፍኖ <አምላኬ ሆይ እባክህ ድረስልኝ? እባክህ ድረስልኝ? እባክህ? ……… > እያለ በልቡ የፀለየውን ባይሰማው እንኳን እንባውን አይቶ እንዲራራለት እራሱ እግዚአብሔር ቢያጠራቅመው ለአንድ ክረምት የሚበቃውን እንባ አነባ። እግዚአብሔር ግን ለልቡም ፀሎት ለዓይኑም እንባ መልሱ ዝም ነበር! ዝም!! » የመጨረሻዎቹ ቃላት ላይ ድምፁ እየቀነሰ፣ እየሻከረ መጣ። ከመጀመሪያው ዓረፍተ ነገር በኋላ አልፃፍኩም። ጣቶቼ አደጋ ከደረሰባቸው የእርሱ ጣቶች በላይ ተንቀጠቀጡ። «ስንት ዓመቱ ነበር?» አልኩት ቀና ብዬ «አስራ ሁለት» አለኝ። ስሜቱ መረበሹ በግልፅ እያስታወቀበት አስተካክሎ መግፋትማንበብ ይቀጥሉ... - [ሰይጣን ወይ እግዜር የጀመሩት... እኔ የቀጠልኩት (ክፍል ዘጠኝ)](https://shegerblogs.com/%e1%88%b0%e1%8b%ad%e1%8c%a3%e1%8a%95-%e1%8b%88%e1%8b%ad-%e1%8a%a5%e1%8c%8d%e1%8b%9c%e1%88%ad-%e1%8b%a8%e1%8c%80%e1%88%98%e1%88%a9%e1%89%b59/): «እኔ ከዚህ በላይ ማስመሰል አልችልም! ከአቅሜ በላይ ነው የምወድህ!» እያልኩት እናቱ ናፍቃው እንዳገኘ ህፃን መንሰቅሰቅ ጀመርኩ። የሚያስለቅሰኝ ምኑ እንደሆነ ለራሴ ምክንያት መስጠት አልቻልኩም። ፍቅሩ፣ ፍርሃቴ፣ ሳልናገር መታፈኔ ……… አላውቅም። እንደህፃን ድምፅ አውጥቼ እዬዬ ማለት ጀመርኩ። እሱ መጀመሪያ እየከወነ ያለውን ልፋት በቀስታ አቆመ። «አውቃለሁኮ! » አለ ለእኔ ይሁን ለራሱ የተናገረው በማያስታውቅ አወራር። <አውቃለሁኮ!> ያለበት አባባል <አውቄልሻለሁኝኮ! ፍቅርሽ ገብቶኛል፣ ተረድቼሻለሁ።> ዓይነት አይደለም። የሆነ የቁጭት ዓይነት፣ የብስጭት ዓይነት ነበር። …….. መንሰቅሰቄ ሲብስበት በጎኑ ተኝቶ ደረቱ ላይ አጣብቆ አቅፎኝ ዝም አለ። የሳጌ ድምፅ ከፍ ሲልበት እቅፉን ጠበቅ ያደርገዋል። እንደማባበል ዓይነት። ደቂቃዎች ካለፉ በኃላ ………….. ለቅሶዬን ያለከልካይ ካስነካሁት በኃላ………. እንባዬ ደረቱን ካራሰው በኋላ ………. ከዚህማንበብ ይቀጥሉ... - [ሰይጣን ወይ እግዜር የጀመሩት... እኔ የቀጠልኩት (ክፍል ስምንት)](https://shegerblogs.com/%e1%88%b0%e1%8b%ad%e1%8c%a3%e1%8a%95-%e1%8b%88%e1%8b%ad-%e1%8a%a5%e1%8c%8d%e1%8b%9c%e1%88%ad-%e1%8b%a8%e1%8c%80%e1%88%98%e1%88%a9%e1%89%b58/): ጥፋቴ ማፍቀሬ ነበር አላልኳችሁም? የትኛው ዓመት ፣ መቼ ላይ እንዳፈቀርኩት እንኳንኮ አላውቅም! ቀስ በቀስ ……. መሰረቱን ሲጥል ….. ግድግዳውን ሲገነባ ….. ጣራውን ሲከድን …… ቀለም ሲቀባባባ ፣ ወለሉን ሲያሳምር …… ገዝፎ ገዝፎ ተሰርቶ አልቆ …… በአራተኛው ዓመት በራሴ ላይ ማዘዝ የማልችል ሆኜ ሽምድምድ ካልኩ በኋላ ነው ከእንቅልፉ እንደባነነ ሰው የማደርገው ጠፍቶኝ ጥፋት እንዳጠፋ ህፃን ባየሁት ቁጥር ልቤ ከአቃፊዋ ካላመለጥኩ ትል የጀመረችው። ሰርቆ መች ከመቼ ተነቃብኝ እንደሚል ሌባ .. መሰረቱን ሲጥል በተጋባን በሆኑ ወራቶች ውስጥ የሆነ ቅዳሜ ከሰዓት ሁሌም ላይብረሪ ሲቀመጥ እንደሚያደርገው ስልኩን አጠፋፍቶ እያነበበ ነበር። ሁሌም ማንበብ ሲጀምር በስርዓቱ ወንበሩ ላይ ተቀምጦ መፅሃፉን ጠረዼዛው ላይ አስቀምጦ ነው። ከሆነ ሰዓት በኋላማንበብ ይቀጥሉ... - [ሰይጣን ወይ እግዜር የጀመሩት... እኔ የቀጠልኩት (ክፍል ሰባት)](https://shegerblogs.com/%e1%88%b0%e1%8b%ad%e1%8c%a3%e1%8a%95-%e1%8b%88%e1%8b%ad-%e1%8a%a5%e1%8c%8d%e1%8b%9c%e1%88%ad-%e1%8b%a8%e1%8c%80%e1%88%98%e1%88%a9%e1%89%b57/): ሰርጉ የራሴ ሆኖ ፣ በሰው ሰራሽ ፋብሪካ የተመረተ ሮቦት ይመስል ዘመድ አልባ ባል ላገባ የተዘጋጀሁት እኔ ሆኜ ሳለሁ፣ ሰርጉ ላይ ሚዜ እንኳን የሚሆን ጓደኛ የሌለው ባል ለማግባት ራሴ አምኜ ………. ምን ይሉ ይሆን ብዬ የምጨነቀው ለቤተሰብ ፣ ሰርጉ እንከን እንዳይኖረው ቁጭ ብድግ የምለው ለታዳሚው ……ሙሽራዋ ግን እኔው …… ቀኑ መሆን የነበረበት የኔ «ለምን ራስሽን አትሆኝም?» አለኝ አዲስ የሰርጉ ውጥረት ቀልቤን ሲነሳኝ አይቶ «ይሄ ነገር ስለሚባል ነው አይደል የምትሉት? ራስህን መሆን እኮ …… የምትወደው ራስህ ሲኖርህ ነው! እኔን መሆን እንዴት እንደሚያስጠላ ብታውቅ <ራስሽን ሁኚ> አትለኝም! ራሴን አልወደውም አዲስ! የማልወደውን ራሴን እንድሆን አትንገረኝ! እኔን መሆን ይቀፋል! ሌላን ሰው መልበስ ይሻለኛል። ያ ሰውማንበብ ይቀጥሉ... - [ሰይጣን ወይ እግዜር የጀመሩት... እኔ የቀጠልኩት (ክፍል ስድስት)](https://shegerblogs.com/%e1%88%b0%e1%8b%ad%e1%8c%a3%e1%8a%95-%e1%8b%88%e1%8b%ad-%e1%8a%a5%e1%8c%8d%e1%8b%9c%e1%88%ad6/): የዛን ቀን …….. እንኳን ዶክመንተሪ ፊልሙን አይተን ስንጨርስ በሙቀቱ ወዝቶ ቅባት የተቀባ የመሰለውን ጠይም ፈርጣማ ደረቱን እጄ ሲንቀለቀል ሄዶ የነካው ቀን……… እጄን ደረቱ ላይ በእጁ ደግፎ እንዳላንቀሳቅሰው ይዞት «እርግጠኛ ነሽ?» «ቨርጅን አይደለሁምኮ።» «አውቃለሁ!! በኋላ የፀፀትሽ ምክንያት መሆን አልፈልግም።» እያለኝ ትንፋሹ ከንፈሬጋ ደርሷል። አሁን ማን ይሙት ሀሳቤን መቀየር እንኳን ብፈልግ የቱን ሀሳቤን እንደምቀይር አስተካክዬ ማስታወስ እችል ነበር? እየሳመኝ እያቋረጠ ያወራል። አንዳንዱን ቃል እየሳመኝም እያወራም ነው ልበል? ወይም መስሎኝ ነው። «ለምን እፀፀታለሁ?» አልኩኝ ከንፈሬን ነፃ ባደረገልኝ ቅፅበት። ደረቱ ላይ ይዞት የነበረውን እጄን አንስቶ እንደዋልዝ ዳንስ አሽከርክክሮ በጀርባዬ እያዞረኝ «የሴት ልጅ ክብሯ እግሯ መሃል ነው ብለው ነግረዋችኋል።r (ቅድም የቆጠራቸውን ሶስት ቁልፎች እየፈታ አንገቴማንበብ ይቀጥሉ... - [አሳዳጅ](https://shegerblogs.com/%e1%8a%a0%e1%88%b3%e1%8b%b3%e1%8c%85/): የኑሮ ውድነት የማያሳስባቸው ነዋሪዎች ፥ ደላላ፥ የመሬት ሽያጭ ሰራተኛ ፥ ሰባኪ ፥ ታዋቂ ዘፋኝ እና አነቃቂ ንግግር አቅራቢ ናቸው፥ ባለፈው አንድ የታወቀ አነቃቂ ነኝ እሚል ሰውየ ላስር ደቂቃ አፉን ያለገደብ ወለል አድርጎ ከፍቶ ሲያዛጋ አየሁት፥ ጠጋ አልሁና ”በውኑ ከዚህ አፍ መነቃቃት ሊወጣ ይችላልን?“ ስለው በስንግ ቃርያ ጥፊ ወለወለኝ! ብታምኑም ባታምኑም የሌለ ነቃሁ! እውነት ለመናገር በንግግር መነቃቃት የሚባል ነገር የለም፥ በንግግር የሚነቃቃ ንግግሩ ሲጠናቀቅ ይተኛል። እውነተኛ አነቃቂዎች የሚከተሉት ናቸው፥ የደመወዝ ጭማሪ፥ የኢኮኖሚ እድገት፥ ፍትሀዊ አስተዳደር እና የቶሞካ ቡና። ባለፈው እኔና ምኡዝ በረንዳ ላይ ቁጭ ብለን ቡና ስንጠጣ፥ “ስማ፤ ዘመኑ ክፍቷል፥ ተጠንቀቅ፡ አለኝ “እሞክራለሁ” “ በጊዜ እየገባህ ነው?” “ አዎ ! ለምሳማንበብ ይቀጥሉ... - [ሰይጣን ወይ እግዜር የጀመሩት... እኔ የቀጠልኩት (ክፍል አምስት)](https://shegerblogs.com/%e1%88%b0%e1%8b%ad%e1%8c%a3%e1%8a%95-%e1%8b%88%e1%8b%ad-%e1%8a%a5%e1%8c%8d%e1%8b%9c%e1%88%ad-%e1%8b%a8%e1%8c%80%e1%88%98%e1%88%a9%e1%89%b55/): «እኔ ደስ የሚለኝ ጓደኛሞች ብንሆን ነው።» አልኩት እቤቱ ይዞኝ የሄደ ቀን «እረፊ! እኔ አንዴ ልብስሽን አውልቄ ጭንቅላቴ ውስጥ ስዬሻለሁ። ጓደኛሞች እንሁን ብልሽ ውሸቴን ነው። ገና ሳይሽ የቀሚስሽን ሶስት ትንንሽዬ ቁልፎች ፣ ቀጥሎ ዚፑን …….. ወደታች ባወልቀው ወይ ወደላይ የቱ ይፈጥናል? አስቤ ጨርሻለሁ!» የገረመኝ ክፍት አፍነቱ አይደለም። እሱን እየለመድኩት ማፈር ትቻለሁ፣ በዛ ላይ ሌላ ሰው ሲያወራው የሚያሳፍረኝን ነገር እሱ ሲያወራው አለው የሆነ ልከኛ ወሬ የሚያስመስለው ድምፀት። በትክክል ቀሚሴ ከጀርባው የዚፑ መጨረሻ ማጅራቴ ጋር ትንንሽዬ ሶስት ቁልፎች መኖራቸው ነው። ከላይ ደርቤ የነበረውን ኮት ካወለቅኩት 5 ደቂቃ አይልፍም ነበር። ገርሞኝ አፍጥጬ ሳየው። <ነግሬሻለሁኮ> አይነት ፊቱን እና ትከሻውን ሰበቀ። ቤቱ <እንደማንኛውም ፊልሞች ላይ እንደምናያቸውማንበብ ይቀጥሉ... - [ሰይጣን ወይ እግዜር የጀመሩት... እኔ የቀጠልኩት (ክፍል አራት)](https://shegerblogs.com/%e1%88%b0%e1%8b%ad%e1%8c%a3%e1%8a%95-%e1%8b%88%e1%8b%ad-%e1%8a%a5%e1%8c%8d%e1%8b%9c%e1%88%ad-%e1%8b%a8%e1%8c%80%e1%88%98%e1%88%a9%e1%89%b54/): ለመጀመሪያ ጊዜ በተያየን በአስረኛው ደቂቃ ነው <ላግባሽ> ያለኝ። የሶስተኛ ታናሼን ሰርግ ልታደም አንደኛው የከተማችን ሆቴል ነበርኩ። የምሳ ቡፌ ከተነሳ በኋላ ማንም ሳያየኝ ከአዳራሹ ውልቅ ብዬ እዛው ህንፃ ላይ ያለ ሬስቶራንት ውስጥ ገባሁ። ቢያድለኝኮ የአክስቶቼን ውግምት የሆነ ዓይን መሸሼ ነበር። ገና ወንበር ስቤ ከመቀመጤ ከየት መጣች ሳልላት አንዷ አክስቴ «ምነውሳ ያን ከመሰለ ፌሽታ ተነጥለሽ እዚህ ብቻሽን?» «ቡና መጠጣት ፈልጌ ነው! አንቺስ?» «እኔማ ስልክ ላወራ ወጥቼ ስትዘልቂ አይቼሽ ነው። በይ እኔ ልመለስ እናቴ!» ብላ ፊቷን አዙራ ስትሄድ በግልግል ልተነፍስ የጀመርኩትን ትንፋሽ መለስ ብላ ስቅታ አደረገችብኝ። «እንግዲህ ሚጡዬ ታናናሾችሽን ሁሉ ድረን ጨረስን። ለሴት ልጅኮ ተፈጥሮም ገደብ ይጥላል! እንደው ምርጫው ይቅርብሽና ከአንዱ ሰብሰብ በይማንበብ ይቀጥሉ... - [ሰይጣን ወይ እግዜር የጀመሩት... እኔ የቀጠልኩት (ክፍል ሶስት)](https://shegerblogs.com/%e1%88%b0%e1%8b%ad%e1%8c%a3%e1%8a%95-%e1%8b%88%e1%8b%ad-%e1%8a%a5%e1%8c%8d%e1%8b%9c%e1%88%ad3/): ከሳምንታት በኋላ ዝም አለ። በቃ ዝም! በእኔ ቁጥጥር ስር መሆኑን ላለመቀበል መፍጨርጨሩን ተወው። የእኔ እርዳታ የሚሰጠውን የተሸናፊነት ስሜት ላለመዋጥ የሚያደርገውን መንፈራገጥ ተወው። ሳጎርሰው ከምግቡ ጋር የሚውጠውን እልህ ተወው። ሰውነቱን ሳጥበው ከጡንቻው ጋር የሚያፈረጥመውን ትዕቢት አተነፈሰው። መለፍለፉንም ተወው። ዝም ጭጭ አለ። ልክ እንደሌለ ነገር። እንደማይሰማ ፣ እንደማያይ ፣ ምንም ስሜት እንደማይሰጠው ፣ ጭራሽ እዛ እንደሌለ…………. ዝምታው ደስ አይልም ይሸክካል። የተሸነፈ ሲመስል የበቀሌን ጥፍጥና ይቀንሰዋል። ደስ አይልም! «ወደኋላ ተመልሰሽ ድጋሚ የህይወት ምርጫሽን የማስተካከል እድሉ ቢኖርሽ ታገቢኝ ነበር? ማለቴ ይሄን ትዳር ትመርጪ ነበር?» አለኝ ከብዙ ቀናት ዝምታ በኋላ የገና ቀን ጠዋት መኝታ ቤታችን መስታወቱ ፊት የበዓል ነጭ ልብስ እያለበስኩት ሳለ «አዎ ሁለቴ ሳላስብ!»ማንበብ ይቀጥሉ... - [ሰይጣን ወይ እግዜር የጀመሩት... እኔ የቀጠልኩት (ክፍል ሁለት)](https://shegerblogs.com/%e1%88%b0%e1%8b%ad%e1%8c%a3%e1%8a%95-%e1%8b%88%e1%8b%ad-%e1%8a%a5%e1%8c%8d%e1%8b%9c%e1%88%ad-2/): ከእኔ በፊት ሁለት ሚስት አግብቶ እንደነበር ሳላውቅ አይደለም ያገባሁት። አውቅ ነበር። ለሁለቱም ሚስቶቹ ልክ ከእኔ ጋር እንዳደረገው የሀብት ውርስ ኮንትራት አስፈርሟቸው እንደነበርም አልደበቀኝም ነበር። በፍቅሩ ነሁልዬ ከእኔ በፊት የነበረው ህይወቱ ገሀነም እሳት ጭስ ሳይሸተኝ ቀርቶም አይደለም። ወይም ፍቅሬ አቅሉን አስቶት በአበባና በስጦታ አንቆጥቁጦኝ ሚዛናዊነቴን አስቶኝም በፍፁም አይደለም። ገና ሳልገባበትም ትዳሬ ሲኦል ሊሆን እንደሚችል የሚንቀለቀል ፍም እሳት ነበልባሉ ሽው ብሎኛል። ገና ሳንጋባ «ሴት ይሰለቸኛል። ለዛ ነው ትዳር በተወሰነ አመት ኮንትራት መሆን አለበት ብዬ የማምነው።» «ኮንትራት ያበጀኸውኮ ለትዳሩ ሳይሆን ለውርስ ነው ታዲያ!» «ያው ናቸው። ለሴት ልጅ ትዳር እና ገንዘብ ያው ናቸው። ቤተሰቦቿ ገና ሽማግሌ ስትልኪ የሚጠይቁት ምንድነው? ልጃችንን በምን ያስተዳድራታል? እሷስ ገናማንበብ ይቀጥሉ... - [እያንዳንድህ ፥ እያንዳንድሽ!](https://shegerblogs.com/%e1%8a%a5%e1%8b%ab%e1%8a%95%e1%8b%b3%e1%8a%95%e1%8b%b5%e1%88%85-%e1%8d%a5-%e1%8a%a5%e1%8b%ab%e1%8a%95%e1%8b%b3%e1%8a%95%e1%8b%b5%e1%88%bd/): ከናትሽ ሙዳይ ሰርቀሽ፥ ኮኮስ ቅባት የተቀባሽ በጸደይ ወቅት ፥ የስሚዛ አበባ የጠባሽ ድድሽን ባጋም እሾህ የተነቀስሽ ጡትሽን ለማስተለቅ ፥አጎጠጎጤሽን በውሀ እናት ያስነከስሽ ቤት ባፈራው ጌጥ ብቻ፥ በዛጎል በዶቃ ያማርሽ በቃቃ ጨዋታ ወግ ፥ በሽቦ መኪና የተዳርሽ ሲያደንቁሽ የተሽኮረመምሽ ሲነኩሽ የተስለመለምሽ ሲስሙሽ፥ አገር ለቀሽ ለመመነን ያለምሽ በቸርቺል ጎዳና ላይ ፥ሰኞ ማክሰኞ የተጫወትሽ የኔ ትውልድ አባል ነሽ ብትኮሪ ምክንያት አለሽ። እያንዳንድህ! በጅምር አስፋልት ላይ ፥ ሽኩኔታ የነዳህ ወይራ ከታጠነ ማድጋ ፥ በመርቲ ጣሳ የቀዳህ በጥቂቱ የረካህ ፥ በመናኛው የተደነቅህ ድንኳን ሰብረህ በቅልውጥ፥ የጎረቤት ሰርግ ያደመቅህ ካባትህ ሽልንግ ሰርቀህ ፥ “ዲስኮ ዳንሰርን” ያየህ ባስር ሳንቲም ፥ ትኩስ ሽልጦ የገበየህ በየመስኩ፥ በየፈፋው ፥ፋንድያህን የነሰነስህማንበብ ይቀጥሉ... - [ሰይጣን ወይ እግዜር የጀመሩት... እኔ የቀጠልኩት (ክፍል አንድ)](https://shegerblogs.com/%e1%88%b0%e1%8b%ad%e1%8c%a3%e1%8a%95-%e1%8b%88%e1%8b%ad-%e1%8a%a5%e1%8c%8d%e1%8b%9c%e1%88%ad-%e1%8b%a8%e1%8c%80%e1%88%98%e1%88%a9%e1%89%b5-%e1%8a%a5%e1%8a%94-%e1%8b%a8%e1%89%80%e1%8c%a0/): «ሞቼ ቢሆን ኖሮ ደስ ይልሽ ነበር አይደል?» አለኝ በወጉ ማሽከርከር ያልለመደውን ዊልቸር እየገፋ ወደሳሎን ብቅ እንዳለ። ፊቱ ምሬት ወይ ጥላቻ በቅጡ ያልለየሁት ስሜት ይተራመስበታል። ዝም ያልኩት መመላለሱ ልቤን ስለሚያደክመኝ ነበር። በጎማው እየተንቀራፈፈ አጠገቤ ደርሶ « ንገሪኛ ደስ ይልሽ ነበር አይደል?» «አይከፋኝም ነበር።» መለስኩለት። እግዚአብሔር ይሁን ሰይጣን አደጋውን ያደረሱበት አንዳቸው ምርጫ ሰጥተውኝ ቢሆን ኖሮ እንኳን የቱን እንደምመርጥ እንጃ! (ሰዎች በህይወታቸው የሆነ የከፋ ነገር ሲገጥማቸው <እግዜር ሊያስተምረው ነው!> ይሉን የለ? ያው ራሳቸው ሰዎች ደግሞ የክፉ ነገር ምንጭ ሰይጣን ነውም ይሉናል። ነገሩ ለእኔ ጭንቅላት የተሳከረ ነገር ስላለው ነው ከሁለቱ አንዳቸው ቢሆኑ ያልኩት!! አስቡት የመልካም ነገር ሁሉ ምንጭ የሆነው አምላክ ፣ ለሰው ልጅ በምርጫውማንበብ ይቀጥሉ... - [የተሳሳተ](https://shegerblogs.com/%e1%8b%a8%e1%89%b0%e1%88%b3%e1%88%b3%e1%89%b0/): ከምኡዝ ጋራ ከረጅም ጊዜ በሁዋላ ተገናኘን፥ “ ከመንገድ ዳር ካለ አንድ ካፌ በረንዳ ላይ ቁጭ ብለን አቧራና ቡና እየጠጣን አላፊ አግዳሚውን እያየን እናወራለን፥ ድንገት አንዲት ሴት ብቅ አለችና ወደ ምኡዝ እያየች “ አንተ አለህ?” ብላ ባድናቆት ጮኸች፤ ሁለት እጆቿን በሰፊው ዘርግታ እቅፍፍፍፍፍ አደረገችው፤ ቀጥላ እኔንም እቅፍ ታደርገኛለች ብየ ተስፋ አደረግሁ ፥ ከእቅፉ ወጣችና እንደገና እጅጌዋን እስከ ክርኗ ሰብስባ ባዲስ ጉልበት ተጠመጠመችበት፤ ወረፋው እስኪደርሰኝ ከኪሴ ዶዶራንት አውጥቼ ብብቴ ላይ ነፋሁ፤ አሁንም እንደገና ተቃቀፉ፤ ስራ ከምፈታ ብየ ከግራ ብብቴ ላይ በላብና በዶዶራንት የፋፉ ሁለት የጸጉር ዘለላዎችን ነቀልሁ፤ በመጨረሻ ፈገግታየን እንደ ደጋን ወጥሬ፥ እጄን እንደ በረኛ ዘርግቼ ተጠጋሁዋት። ልጂቱ ግን ጸጉር የከበደውን ራሷንማንበብ ይቀጥሉ... - [ከአበታር ወደ አባተ](https://shegerblogs.com/%e1%8a%a8%e1%8a%a0%e1%89%a0%e1%89%b3%e1%88%ad-%e1%8b%88%e1%8b%b0-%e1%8a%a0%e1%89%a3%e1%89%b0/): አንዳንዴ የአማርኛ ዘፈን ቪዲዮ ሳይ ብዙ ነገር ይገርመኛል፤ የአማርኛ ሙዚቃ ቪድዮ ከማየትሽ በፊት ጃንጥላ መያዝ ይኖርብሻል ፥ ዝናብ የሌለው የፍቅረኞች ትእይንት ጥቂት ነው፤ በገሀዱ አለም ያገራችን ሰማይ ያሻሮ ብረት ምጣድ ማለት ነው፤ የብብታችን ላብ ካዲሳባ ሰማይ የተሻለ ያካፋል፤ ታድያ ዳይሬክተሮች ይሄን ሁሉ ዝናብ ከየት አመጡት? ቆየቸ ሳጣራ ፥ ከካሜራ ባለሙያው ጎንለጎን ጀሪካን አዝሎ የሚከተል የፍሳሽ ባለሙያ መኖሩን አጋገጥሁ፤ ለካ በመዲናይቱ ውሀ የተወደደው የሙዚቃ ኢንዱስትሪው አላግባብ ስለሚያባክነው ነው። ከፍቅር ቀጥሎ ብዙ የተዘፈነለት ጀግንነታችን ነው፤ ጀግንነት ሲነሳ አድዋን ድል ማጣቀስ የማይቀር ሆኗል ፤ባማርኛ ሙዚቃ ቪዲዮ ውስጥ አድዋ ሲቀርብ ባጭሩ እንዲህ ነው፦የጣልያን ጦር ይሮጣል፤ የወገን ጦር ያባርራል፤ ዘፋኙም ይፎክራል፥ ጣልያኖች መሮጥ ሲሰለቻቸው ይወድቃሉ፤ማንበብ ይቀጥሉ... - [ጥቆማ](https://shegerblogs.com/%e1%8c%a5%e1%89%86%e1%88%9b/): ራይድ ለመዲናይቱ አሪፍ ጸጋ ነው፤ ለብዙ ሰው ስራ ፈጥሮ የብዙ መንገደኞችን ኑሮ አቅልሏል። ራይድ የሚሰሩ ሰዎች መካከል አንዳንዶቹ እንደኔ የክፍለሀገር ልጆች መሆናቸውን መርሳት አይገባም። ባለፈው አንዱ ባለ ቢትስ መጣልኝ፥ ጢንጥየ መኪና ናት፤ አራት ጎማ ያላት የዲዮጋን ቀፎ በላት፤ አሁን በመንሽ እግሩ ያዲሳባን አቧራ ሲቀዝፍ የሚውል እንደ እኔ ያለ ዘመን አይሽሬ እግረኛ ሰው መኪና ላይ ሙድ መያዝ ነበረበት? ሰው ምን ይለኛል አይባልም? ሆ!” “ጋቢና ትገባለህ ወይስ ከሁዋላ ?” ሲል አማረጠኝ፥ የመኪናይቱን በር እንደ መርቲ ጣሳ ክዳን ከፍቼ፤ እንደ ሰርከስ ባለሙያ ተጣጥፌ ከሁዋላ ገባሁ፥ እንደ እውነቱ ከሆኑ የመኪናይቱ መላ አካልለሁለት የተከፈለ ጋቢና ቢባል ያስኬዳል፤ መኪናዋ ከመጥበቧ የተነሳ ከሾፌሩ ጋራ አንድ ቀበቶ ለሁለትማንበብ ይቀጥሉ... - [ጥቆማ](https://shegerblogs.com/%e1%8c%a5%e1%89%86%e1%88%9b-2/): ራይድ ለመዲናይቱ አሪፍ ጸጋ ነው ፤ ለብዙ ሰው ስራ ፈጥሮ የብዙ መንገደኞችን ኑሮ አቅልሏል፥ ራይድ የሚሰሩ ሰዎች መካከል አንዳንዶቹ እንደኔ የክፍለሀገር ልጆች መሆናቸውን መርሳት አይገባም፥ ባለፈው አንዱ ባለ ቢትስ መጣልኝ፥ ጢንጥየ መኪና ናት፤ አራት ጎማ ያላት የዲዮጋን ቀፎ በላት፤( አሁን በመንሽ እግሩ ያዲሳባን አቧራ ሲቀዝፍ የሚውል እንደ እኔ ያለ ዘመን አይሽሬ እግረኛ ሰው መኪና ላይ ሙድ መያዝ ነበረበት? ሰው ምን ይለኛል አይባልም? ሆ!” “ጋቢና ትገባለህ ወይስ ከሁዋላ ?” ሲል አማረጠኝ፥ የመኪናይቱን በር እንደ መርቲ ጣሳ ክዳን ከፍቼ፤ እንደ ሰርከስ ባለሙያ ተጣጥፌ ከሁዋላ ገባሁ፥ እንደ እውነቱ ከሆኑ የመኪናይቱ መላ አካልለሁለት የተከፈለ ጋቢና ቢባል ያስኬዳል፤ መኪናዋ ከመጥበቧ የተነሳ ከሾፌሩ ጋራ አንድ ቀበቶማንበብ ይቀጥሉ... - [እንደምትወዳት ንገራት](https://shegerblogs.com/%e1%8a%a5%e1%8a%95%e1%8b%b0%e1%88%9d%e1%89%b5%e1%8b%88%e1%8b%b3%e1%89%b5-%e1%8a%95%e1%8c%88%e1%88%ab%e1%89%b5/): ሕይወት የብድር በሬ፥ መቼ ሁሌ ይጠመዳል ለጊዜው ብቻ የመጣ፥ ጊዜው ሲደርስ ይሄዳል የተሰጠህ ጸጋ ሁሉ፥ ደሞ ካንተ ይወሰዳል። ቀለበት፥ አምባር አይደሉም እጅህ ላይ ሁልጊዜ የሉም ቀናት ሳምንታት ወራት ዛሬውኑ፥ አሁኑኑ፥ እንደምትወዳት ንገራት። አበቦች ሁሉ ሳይረግፉ ምኡዝ ሽታዎች ሳይጠፉ ያጸድ በሮች ሳይቆለፉ በንቦች ጎዳና ላይ፥ ተርቦች ሳይሰለፉ በንፋስ ክንፍ ሳይመታ ሕይወት የላምባ መብራት አሁንኑ ዛሬውኑ፥ እንደምትወዳት ንገራት። ርቃ ሳትገሰግስ ገና ስንቋን ስትደግስ እንዲሁ እንዳማረባት ቀልብህ እንደቀረባት መቃብር በመዳፉ እንደጠጠር ሳይቀልባት አፈሩን ሳትዛመድ ወደማትቀባው አመድ ወደማትስበው አየር ሳትቀየር አንትም አንደበት ሳለህ፥ እሷም ጆሮ ሳያጥራት ዛሬውኑ! አሁኑኑ! እንደምትወዳት ንገራት። - [ግ-ሽበት](https://shegerblogs.com/%e1%8c%8d-%e1%88%bd%e1%89%a0%e1%89%b5/): አዲሳባ እየሰፋች ነው፤ ከጥቂት አመታት በሁዋላ“ በአዲስአበባ አስተዳደር በአንኮበር ክፍለከተማ ነዋሪ ሆኑት አቶ በእውቀቱ“ የሚል ነገር መስማታችን አይቀርም፥ አያት ወደ እሚባለው ሰፈር ብቅ ካሉ የፈረስ ጋሪ፥ ባጃጅ እና ዘመናዊ መኪና ትከሻ ለትከሻ እየተጋፉ ሲያልፉ ያያሉ፥ ባንድ ከተማ ውስጥ ሶስት ክፍለዘመኖች፥ ጎንለጎን ይራመዳሉ። ሀብታሞች በሀብት ከላይ ሀብት ጭነዋል ፥ድሆች የባሰ ድሀ ሆነዋል፥ የዛሬ ሶስት አመት ያንድ ሆቴል ባለቤት የነበረው ሰውየ ዛሬ ሶስት ቅርንጫፎች ከፍቷል! የዛሬ ሶስት አመት መጽሀፍ እሚያዞረው ልጅ ዛሬም መጽሀፍ አዟሪ ነው። ከትናንት ወድያ። በከተማው ዘናጭ ከተባሉት ሬስቶራንቶች አንዱ ጎራ አልሁ፥ አዲስ ዩኒፎርም የተሰፋለት ዘበኛ፥ ከሸራ ጫማየ እስከ ጋሜየ ድረስ ገምግሞኝ ሲያበቃ፥ “ወዴት ነው?” አለኝ፥ “ወደ ምሳ“ ዘቡሌው ያለምንምማንበብ ይቀጥሉ... - ["መዶሻህን ብላው"](https://shegerblogs.com/%e1%88%98%e1%8b%b6%e1%88%bb%e1%88%85%e1%8a%95-%e1%89%a5%e1%88%8b%e1%8b%8d/): ወዳጄ (Netsanet) እንደነገረኝ ሰውዬው እሁድ ቀን እቤቱ ጋደም ብድግ ሲል ይቆይና ግድግዳው ላይ የተነቀለች ሚስማር አይቶ ሊመታት ቢፈልግ መዶሻ ያጣል። ጎረቤቱን ሊጠይቀው በሩጋ ከደረሰ በኋላ «ተኝቶ ቢሆንስ» ብሎ ይመለሳል። እቤቱ ከመድረሱ በፊት ግን «እህ የተኛ እንደሆነስ? መዶሻውን ከሰጠኝ በኋላ ተመልሶ ይተኛላ!» ብሎ ተመልሶ ሄደ። አሁንም በሩጋ ሲደርስ «ሰንበት ነው። በሰንበት እንዴት ትሰራለህ ቢለኝስ?» ብሎ ያስብና ወደቤቱ ይመለሳል። እቤቱ ቁጭ ብሎ ሲያስበው «እንዴ ምንአገባው እኔ ለምሰራው ሰንበትስ ፆምስ ቢሆን መዶሻህን ስጠኝ እንጂ ምታልኝ አላልኩት?» ይልና ተመልሶ ወደጎረቤቱ በር ይሄዳል። «እንግዳ ቢኖርበትስ? ከሴት ጋር አልባሌ ነገር እያደረገ ቢሆንስ?» ብሎ ያስብና ደግሞ ይመለሳል። እንዲህ አንዱን ምክንያት ሲያስብ ሲመለስ ውድቅ ሲያደርግ ደግሞ ሲሄድ ቀኑማንበብ ይቀጥሉ... - [የጥልቁ ትንታኔ](https://shegerblogs.com/%e1%8b%a8%e1%8c%a5%e1%88%8d%e1%89%81-%e1%89%b5%e1%8a%95%e1%89%b3%e1%8a%94/): በቀደም ስለሉሲፈር ፊልም በፃፍኩት ፅሁፍ ስር አንዱ “ትውልዱን በማር የተለወሰ መርዝ እያስነበብሽው ነው” ብሎኝ ሳቅቼ ሞተውት። እናውራ እንዴ? የትኛውን ትውልድ? ይሄ ትውልድ ቲክ ያላደረገው የሉሲፈር ስራ አለ ነው የምትሉኝ? ይሄ የኔ ዘር አይደለህም ብሎ ወንድሙን ዘቅዝቆ የሚሰቅለው ትውልድ ሉሲፈር እሩቁ ሆኖ ማለት ነው? ይሄ የኔ ሀይማኖት ተከታይ አይደለህም ብሎ ቤት በእሳት የሚለኩሰው ትውልድ? ይሄ በቀደም ሰው ከነነፍሱ እያነደደ በእርካታ ሲያብድ ያየነው የትውልዳችን አካል ከሉሲፈር በጣም ርቆ ማለት ነው? ተውኣ! ሉሲፈር ራሱ ሳድግ እንደሱ ነው መሆን የምፈልገው የሚያስብለውን ክፋት በውስጣችን አጭቀን ጣታችንን ምንጠቁምበት አጋንንት አንፈልግኣ! Focus on yourself! የጥልቁ ትንታኔ ላይ ትደርስበታለህ! እስኪ የጥልቁን ሴራ ትንታኔ ወደጎን አድርገን የጥልቁ ስራችንን እንተው።ማንበብ ይቀጥሉ... - [ካንደኛው ፌርማታ ወዳንዱ ስሻገር](https://shegerblogs.com/%e1%8a%ab%e1%8a%95%e1%8b%b0%e1%8a%9b%e1%8b%8d-%e1%8d%8c%e1%88%ad%e1%88%9b%e1%89%b3-%e1%8b%88%e1%8b%b3%e1%8a%95%e1%8b%b1-%e1%88%b5%e1%88%bb%e1%8c%88%e1%88%ad%e1%8d%a5/): ይፈርስ የማይመስል፥ እስከ ዘላለሙ አምና እዚህ ቦታ ላይ ፥አንድ ሱቅ ነበረ የሱቁ ባለቤት ሚፍታህ ነበር ስሙ፤ ሙሉቀን ሲተጋ፥ በከፊል የሚታይ፥ እንደዜና አንባቢ፥ በሱቁ መስኮት ላይ ከወገቡ በላይ፥እየተገለጠ ለወጭ ወራጂው፥ ፈገግታ እየሰጠ ሸቀጥ እየሸጠ በጋዜጣ ቅዳጅ እየጠቀለለ በልቃቂት አምሳል እየሸበለለ “የሁለት ብር ሱካር ፥ የብር ካምሳ ዳቦ ጢንጥየ ቅመም ትንሽየ ለውዝ፥የሽልንግ አሻቦ፣ ከተጠቀለለው በልቃቂት አምሳል ድሀውም ሀብታሙም ድርሻውን ያነሳል፤ “አደራው ጥብቅ ነው ፥ዱቤም አይከለክል ባንክ አይታመንም የሚፍታህን ያክል’ “አንደበቱ ቀና፥ መዳፎቹ ትጉ ከቶ እንደሱ የለም የትም ቢፈልጉ” ይሉት ነበር ሴቶች ቡና ላይ ሲያወጉ አሁን እዚህ ቦታ ፥ረጅም ፎቅ ቆሟል ከፊት ያለው መንገድ ባዲስ ተሰይሟል ሚፍታህ ጎዳናው ላይ ፥ዱካውን አልጣለም የት ይሆንማንበብ ይቀጥሉ... - ["lucifer"](https://shegerblogs.com/lucifer/): በራሴ ጉዳይ ተንበርክኬ የፀለይኩበት ቀን በጣም እሩቅ ነው። እውነት ለማውራት ከጠየቅኩት በላይ የማይገባኝ ሁላ የተሰጠኝ ሰው ነኝና ብዙም ጥያቄ የለኝም! ከፍቶኝ ፊቱ የቀረብኩባቸውንም ቀናት formal ፀሎት የፀለይኩባቸው ቀናት በጣም ድሮ ናቸው። አጠገቤ ሆኖ እንደሚሰማኝ እነጫነጫለሁ። «ከዚህ በላይ መሸከም እንደማልችል አታውቅም? እኔ ታውቃለህ ለሆነው ላልሆነው አላስቸግርህም! ይሄንንማ ስማኝ! ደሞ ታውቃለህ ፅድቄን ተማምኜ አይደለም ስምህን መጥራቴ፣ ከንቱ እንደሆንኩ አውቃለሁ ታውቃለህ! ምህረትህን ተማምኜ ነው በድፍረት የምጠይቅህ! ዝምታህ አልበዛም? ከዚህ በላይ አትፈትነኝ! አሳምረህ ታውቀኛለህ ወድቃለሁ ……… » እንዲህ ያለ ወሬም ፀሎትም አይሉት ነገር ነው የምነጫነጭበት። ሲመልስልኝ እና እጄን በአፌ ሲያስጭነኝ እንኳን እኔ በዙሪያዬ ያሉ ይገረማሉ! አርብ እለት የኔ የምላት ሰው ትንሽ ከበድ ያለ ነገርማንበብ ይቀጥሉ... - [ሚሽኑ](https://shegerblogs.com/%e1%88%9a%e1%88%bd%e1%8a%91/): አሳዛኝ ታሪክ ትናንት በራፌ ተቆረቆረ፤ ከፈትኩ፥ ሁለት ያሜሪካ ወታደራዊ መለዮ የለበሱ ሰዎች ቆመዋል ፤ ባለባበሳቸው መገመት እንደቻልኩት አንደኛው ፊልድ ማርሻል ነው፤ ሁለተኛው ፊልድ ሻለቃ ሳይሆን አይቀርም፥ “ሚስተር ቤኪቱ” ብሎ ጠራኝ ማርሻሉ ፥ “አቤት” “እንኳን ደስ ያለህ ለብሄራዊ ውትድርና አልፈሀል! “ አለና ተጠመጠመብኝ ፥ ከጥምጠማው ራሴን እንደምንም መንጭቄ አላቅቄ፤ “ የቅጥር ደብዳቤ ማስገባቴ ትዝ አይለኝም ጌታየ” አልሁ፥ “ጎረቤትህ ነው ያስገባልህ” ግር አለኝ፤ ሻለቃው ግርታየን ለማጥራት የሚከተለውን ማብራሪያ አበራልኝ፥ “ መቸም፥ ማረ ፋከ ብላድሚር ፑቲን ዩክሬንን እንደወረረ ሳትሰማ የቀረህ አይመስለኝም፤ ይሄ ትልቅ አገር በትንንሽ አገር ላይ የሚፈጸም ወንጀል ነው፤ የነገሩን ክብደት እንዴት ብየ ላስረዳህ፥ ኢትዮጵያ ጅቡቲን በወረራ ብትይዝ ብለህ አስበው” ኢትዮጵያ ጅቡቲንማንበብ ይቀጥሉ... - [የባላንታይን ዋዜማ ወግ](https://shegerblogs.com/%e1%8b%a8%e1%89%a3%e1%88%8b%e1%8a%95%e1%89%b3%e1%8b%ad%e1%8a%95-%e1%8b%8b%e1%8b%9c%e1%88%9b-%e1%8b%88%e1%8c%8d/): ከብዙ ዘመናት በሁዋላ ከወዳጄ ምእዝ ጋራ ትናንት በስልክ ተገናኘን፤ ላንድ ሰአት ተኩል ያክል ስናወጋ የተረዳሁት ነገር ፤ጊዜ ብዙ እንዳልቀየረን ነው፤ “የት ልትጋብዛት ነው ያሰብከው?” ሲል ጠየቀኝ፥ “ራቅ ያለ ሰፈር ልወስዳት ነው ያሰበኩት፤ እኛ ሰፈር ያሉት ሬስቶራንቶች ሁሉ ያውቁኛል” “በሬስቶራንቶች ውስጥ ያሉትን አስተናጋጆች ሁሉ ትጀነጀናለህ እሚባለው ሀሜት እንዴት ታየዋለህ” “ከውነት የራቀ አይደለም” “ደግ አደግህ፤ ፈጣን ሎተሪ የሚደርሰው ደጋግሞ በመፋቅ ነው” አለና አበረታታኝ፤ “አለባበሴ ምን ቢሆን ትመክረኛለህ?’ አልሁት፤ “ሮዝ ሸሚዝ ፤ ቀይ ክራባት” “ሱሪስ?” “ሱሪ መታጠቅም እንዳትዘነጋ” “ከድዴ በቀር የቀላ ነገር የለኝም፤ ቀይ ነገር የግድ ነው? “ “በባላንታይን ያለ ቀይ ማክበር ጥምቀትን ያለ ሎሚ እንደማሰብ ነው” “ወይን ጠጅ ሹራብ አለኝ፤ በላዩ ላይማንበብ ይቀጥሉ... - [የሰንበት ትዝታዎች](https://shegerblogs.com/%e1%8b%a8%e1%88%b0%e1%8a%95%e1%89%a0%e1%89%b5-%e1%89%b5%e1%8b%9d%e1%89%b3%e1%8b%8e%e1%89%bd/): ለመጀመርያ ጊዜ ሲኒማ የገባሁት አስራንደኛ ክፍል ሳለሁ ይመስለኛል፤ እሁድ ቀን ደብረማርቆስ ውስጥ ነው፤ ብቸኛው ሲኒማ ቤት ተከፍቶ ካስራምስት የማንበልጥ ሰዎች ታድመናል፤ ፊልሙን በቴክኒክ የሚቆጣጠረው ሰውየ የጤና እህል ማለቴ እክል ገጥሞት አልመጣም፤ ስለዚህ፥ የሲኒማ ቤቱ ዘበኛ ጋሽ ይትባረክ ሰውየውን ተክተው ለመስራት ወሰኑ፤ ትዝ እንደሚለኝ ከሆነ በጊዜው የነበረው የፊልም ፐሮጀክተር ከገጠር ወፍጮ ጋር በጣም ይመሳሰላል፤ ከዚያ ውስጥ የባውዛ መብራት የሚመስል ነገር እንደዝሀ እየተመዘዘ ይወጣና ግድግዳው ላይ ተአምር ይሰራል፤ ያን ቀን፥ ጋሽ ይባረክ ያለሙያቸው ያልሆነ ነገር ሲነካኩ ምን የመሰለውን የህንድ ፊልም ባፍጢሙ ዘቅዝቀው ማሳየት ጀመሩ፤ እነ አሚታብ ፥እነ ኩማር፥ እግራቸው ወደ ጣራው ተሰቅሎ፥ አናታቸው ወደ ምድር ተዘቅዝቆ ግድግዳው ላይ ውርውር ይላሉ፤ ታዳሚው ‘የዛሬውማንበብ ይቀጥሉ... - [በተመን..](https://shegerblogs.com/%e1%89%a0%e1%89%b0%e1%88%98%e1%8a%95/): ከባለንጀሮቼ ጋራ ስናወራ “ እኔኮ ዲያስፖራ አይደለሁም፤ ተመላላሽ፥ ሲራራ ነኝ “ እላቸዋለሁ፤ እነሱ ግን ”እሳት ካየው ምን ለየው“ ብለው በግድ በዲያስፖራነት ይመድቡኛል፤ እሺ ለዛሬ በነሱ ሀሳብ ልስማማና ልቀጥል። ባለፈው መንግስት ዲያስፖራውን አትመጣልኝም ወይ” እያለ ሲጀነጅነው አልነበር?! ብዙ ወዳጆቼ ልባቸው በጅንጀናው ቀልጦ ለገና በአል ትኬት ቆረጡ፤ እኔም ግፍ-ያው ትንሽ ቀለል ሲል ለመድረስ ብየ ለጥምቀት ቆረጥሁ፤ ይህ በእንዲህ እያለ“ ከውጭ አገር ለሚመጡ እንግዶች ያርሶ አደሩን ሰብል የሚሰበስቡበት እድል መመቻቸቱ ተገለጸ”! የሚል ዜና ለቀቁብን፥ እንዴት እንዴት ያለ ነገር ነው! ቀድማችሁ ብትነግሩን እኮ ደርዘን አይፎን ከገዛንበት ቀንሰን ዘመናዊ ማጨጃ እንሸምት ነበር፤ በበኩሌ አርሶ አደሩን ለማገዝ ሁሌም ዝግጁ ነኝ፤ ግን እድሜን ከግምት ያስገባ ስምሪት ቢደረግማንበብ ይቀጥሉ... - [እንዳይደም፤ እንዳይራዘም!](https://shegerblogs.com/%e1%8a%a5%e1%8a%95%e1%8b%b3%e1%8b%ad%e1%8b%b0%e1%88%9d%e1%8d%a4-%e1%8a%a5%e1%8a%95%e1%8b%b3%e1%8b%ad%e1%88%ab%e1%8b%98%e1%88%9d/): በሁለተኛው ያለም ጦርነት ጀርመን ኔዘርላንድን ወረረች። ወራሪም ተወራሪም ነጭ ናቸው። የሁለቱም አገሮች ካንድ ኩሬ የተቀዱ ቋንቋዎች ይናገራሉ። ሂትለር ግድ አለው? ኔዘርላንድ በሰማይ በምድር አጣድፎ ጨመደዳት። ለአራት አመታት ገደማ በቆየ የናዚ ጀርመን ጥጋብ የወለደው አገዛዝ ብዙ ሰዎች በጥይትና በረሀብ አለቁ። ከሰማንያ አመታት በሁዋላ አውሮፓ ውስጥ ራሴን አገኘሁት ፤ አንድ ቀን ኔዘርላንድ ውስጥ የሚኖረው ጋዜጠኛ ደረጀ ሀብተወልድ ቤቱ ምሳ ጋብዞኝ ሲያበቃ በመኪና ወደ ፍራንክፈርት (ጀርመን) ሸኘኝ ፤ ኔዘርላንድ እምታልቅበት፥ ጀርመን እምትጀምርበት ድንበር ላይ መድረሴን ሲነግረኝ የሰማሁትን ማመን አቃተኝ ፤ የግንብ አጥር የለ፤ ጠመንጃ የወደረ ወታደር የለ፤ ፍተሻ የለ፤ በቃ ከሳሎን ወደ ምኝታ ቤት ዘው ብሎ እንደ መግባት ነው። የሰው ልጅ በዚህ ደረጃማንበብ ይቀጥሉ... - [ተቆርጦ የቀረው](https://shegerblogs.com/%e1%89%b0%e1%89%86%e1%88%ad%e1%8c%a6-%e1%8b%a8%e1%89%80%e1%88%a8%e1%8b%8d/): በየነ ባልንጀራየ ነው፤ ጦርነቱ ሲጀመር “በዩማ ቲዩብ “ የሚል የዩቲዩብ አካውንት ከፍቶ መሸቀል ጀመረ፤ አንዳንዴ የድል ዜና ሲጠርርበት ሰለ አድዋ ወይም ስለዶጋሊ ድል በመተረክ ፕሮግራሙን ይሞላዋል፤ አንዳንዴ የኔን ግጥም ሳይቀር ከፌስቡኬ ላይ ወስዶ ይዶልበታል፤ ሳንቲም ማካፈሉ ይቅር ፤ ክሬዲት እንኳ ሊሰጠኝ አልፈለገም። አንድ ቀን ንድድ ብሎኝ ፤ “ለምንድነው ግጥሜን አንብበህ ስሜን የዘለልከው? ”ብየ ጠየኩት። “ለደህነነትህ ስለማስብ ነው” አለኝ ኮሰተር ብሎ። “ስለፍቅር በጻፍኩት ግጥም ምን አይነት የደህንነት ችግር ሊገጥመኝ ይችላል? “ህዝብ በየግንባሩ እየተዋደቀ ስለፎንቃ መፈላሰፍህ ያናደደው አንዱ ደብድቦ ሊገልህ ይችላል! ጊዜውን መምሰል ያልቻለ እድሜው ያጥራል” “ጊዜውን መምሰል ያልቻለ እድሜው ያጥራል “ የሚለው የማን ጥቅስ ነው ?” አልኩት፤ “የኔው ነው! የተልባ ማሻውማንበብ ይቀጥሉ... - ["ኢትዮጵያ ደግሞ... አጉል ትመፃደቃለች!"](https://shegerblogs.com/%e1%8a%a2%e1%89%b5%e1%8b%ae%e1%8c%b5%e1%8b%ab-%e1%8b%b0%e1%8c%8d%e1%88%9e-%e1%8a%a0%e1%8c%89%e1%88%8d-%e1%89%b5%e1%88%98%e1%8d%83%e1%8b%b0%e1%89%83%e1%88%88%e1%89%bd/): ይሄ ለስራ የመጣሁበት አፍሪካዊ ሃገር የእንግሊዝ ቅኝ ግዛት ነበር። መቼ እለት ነው… የዚህ አገር ዜጋ ከሆኑ የስራ ባልደረቦቼ ጋር ሻይ-ቡና ስንል የ‹‹በቃ›› ወይም ” #No More›› ንቅናቄ በወሬ ወሬ ተነሳና ብዙ ነገር ሲያስመዝዘን አመሸ። በዚያ ሰሞን የበቃ ንቅናቄ ጀማሪዎቹ ኢትዮጵያዊያን እና ኤርትራዊያን ፣‹‹እንደውም ለምን እኛ ብቻ…? ድፍን አፍሪካ አዲሱን የእጅ አዙር ቅኝ ግዛት አሻፈረኝ ማለት አለበት‹‹ ብለው ጉዳዩን ከኢትዮጵያ ወደ አፍሪካ ከፍ ሲያደርጉት እዚሁ ነበርኩ። በዚህ ጥሪ ግን ከዚህ አገር ጓደኞቼ መሃከል ደስ ያላላቸው ነበሩ። ያበጠው ይፈንዳ ብለው በግልፅ፣ ‹‹ኤጭ! ኢትዮጵያ ደግሞ አጉል ትመጻደቃለች….›› ያሉኝምነበሩ። አንዳቸው ለአንዳቸው ተደርበው፣ ‹‹እርግጥ ነው። ኢትዮጵያ የአፍሪካ የነጻነት ቀንዲል ናት። ኩዋሜ ንክሩማ ሳይቀር ‹‹ትነሳለች›› ብሎማንበብ ይቀጥሉ... - [‹‹ብንሄድ ብንሄድ- አንደርስም ገና ነው››](https://shegerblogs.com/%e1%89%a5%e1%8a%95%e1%88%84%e1%8b%b5-%e1%89%a5%e1%8a%95%e1%88%84%e1%8b%b5-%e1%8a%a0%e1%8a%95%e1%8b%b0%e1%88%ad%e1%88%b5%e1%88%9d-%e1%8c%88%e1%8a%93-%e1%8a%90%e1%8b%8d/): ቴዲ አፍሮ ‹‹ቀና በል›› የሚለውን ሙዚቃውን በለቀቀ ማግስት ለስራ ጉዳይ ጎረቤት ሃገር ተላክሁ። ከአየር ማረፊያው ወደ ሆቴሌ የሚወስደኝ ታክሲ ውስጥ ገብቼ ብዙዎችን ያላቀሰውን ሙዚቃ በጥሞና ለማዳመጥ የጆሮ ማዳመጫዬን ከስልኬ አገናኘሁ። ልክ ቴዲ ‹‹አርማሽ ይውለብለብ ከደጄ-ልቤ ናፍቆሻል ወዳጄ›› ብሎ መዝፈን ሲጀመር ‹‹ቪንሰንት›› ነኝ ብሎ የተዋወቀኝ ትሁት ሹፌርም መኪናውን ማንቀሳቀስ ጀመረ። ብዙ አልቆየም፤ ቪንሰንት በሙስና በተበላው የከተማዋ ጎዳና ላይ ሰውነቴን እየናጠ ሲወስደኝ፣ ቴዲ ደግሞ ስለት ባላቸው ግጥሞቹ እና አንጀት በሚቦረቡር ዜማው ሁለንተናዬን በስሜት ያናውጠው ጀመር። ይሄ ሰውዬ …ስንኝ በሰንኝ ላይ እየደረበ፣ ዜማን ከዜማ እየቀጣጠለ… አዲሱን ከአሮጌው፣ ዘንድሮን ከድሮ እያደባለቀ…. በአንድ ጊዜ ቁስሌ ላይ ጨውም የሚነሰንሰው፣ እንጨትም የሚሰደው እንዴት ነው? በተመሳሳይ ጊዜ እያከመማንበብ ይቀጥሉ... - [ድል ምርኮና ምህረት](https://shegerblogs.com/%e1%8b%b5%e1%88%8d-%e1%88%9d%e1%88%ad%e1%8a%ae%e1%8a%93-%e1%88%9d%e1%88%85%e1%88%a8%e1%89%b5/): በአጼ ዮሀንስ አራተኛ ዘመነ መንግስት የጎጃሙ ንጉስ ተክለሀይማኖት እና የሸዋው ንጉስ ምኒልክ በመሬትና በንብረት ተጣልተው ሰራዊት አስከትተው እምባቦ በሚባለው ስፍራ ተገናኝተው ተሸካሸኩ፤ በጦርነቱ ምኒልክ እና አጋሮቻቸው በለስ ቀናቸው፤ ንጉስ ተክለሃይማኖት ብዙ ቦታ ቆስለው ተማረኩ፤ ምኒልክ በጦርነቱ ማግስት የግል ሀኪማቸውን በማዘዝ ምርኮኛውን ንጉስ አሳከሟቸው፤ ክብራቸው የሚመጥን እንክብካቤም አደረጉላቸው፤ ከጥቂት ቀናት በሁዋላ አሸናፊና ተሸናፊ ከነተከታዮቻቸው ምሳ እየበሉ ሲያወጉ፥ ምኒልክ “እኔን ማርካችሁኝ ቢሆን ኖሮ ምን ታረጉኝ ነበር?” የሚል ጥያቄ ወረወሩ፤ ምርኮኞቹ ለመቅለስለስ አልሞከሩም ፥ “ ቆራርጠን ያሞራ ራት እናደርገዎ ነበር” የሚል ምላሽ ሰጡ። “ታድያ ከናንተ ጭካኔና ከኔ ርህራሄ ይሻላል ?” አሉ ምኒልክ ፤ ( “እንዴታ! የርስዎ ምህረት ይሻላል እንጂ “ የሚል መልስ እንደጠበቁማንበብ ይቀጥሉ... - [ከሞተላት በላይ የወደዳት ማነው?](https://shegerblogs.com/%e1%8a%a8%e1%88%9e%e1%89%b0%e1%88%8b%e1%89%b5-%e1%89%a0%e1%88%8b%e1%8b%ad-%e1%8b%a8%e1%8b%88%e1%8b%b0%e1%8b%b3%e1%89%b5-%e1%88%9b%e1%8a%90%e1%8b%8d/): ትንሽ ልጅ ሳለሁ… ይህች …ከልጅነት እስከ ጉልምስና የትም፣ መቼም ሳያት እምባ በአይኔ የምትሞላውን ሰንደቅ ዓላማ ትምህርት ቤት በተጠንቀቅ ቆሜ ሳሰቅል፣ ሳላሳልስ ‹‹ኢትዮጵያ…ኢትዮጵያ…ኢትዮጵያ ቅደሚ…አብቢ ለምልሚ›› እያልኩ በስሜት ሳዜም… ‹‹ይህች ሰንደቅ ዓላማ ተከፍሎባታል›› እያሉ ሲነግሩኝ፣ ‹‹ባንዲራችን ብዙ ታሪክ አላት›› እያሉ ሲያስተምሩኝ…. ‹‹ወድቆ በተነሳው ባንዲራ ተብሎ ተምሎባታል›› እያሉ ሲያወጉኝ…. የቀለማቱን ትርጉም ለማወቅ እጓጓ ነበር። ጎጉቼ አልቀረሁም። ገና ኢትዮጵያ ሰፈሬ ሳለች፣ ዓለሜ ሳትሰፋ፣ ከቤተሰቤ ውጪ ሰው ሳላውቅ በፊት የሰንደቅ ዓላማዬን ትርጉም መምህሬ እንዲህ ብሎ አሳወቀኝ። ››አረንጓዴው ለልምላሜዋ ተምሳሌት ነው ቢጫው ለመጪው ጊዜ ተስፋዋ ምሳሌ ነው ቀዩ …ቀዩ ደግሞ ለመስዋእትነት ምልክት ነው። ለሃገር ነጻነት የተከፈለውን ዋጋ ለማስታወስ›› ከዚያ ወዲህ እኔና ባልንጀሮቼ የቀለማቱን ምሳሌ ባንድ ጊዜማንበብ ይቀጥሉ... - [ዘማች](https://shegerblogs.com/%e1%8b%98%e1%88%9b%e1%89%bd/): በቀደም እኔና አዩ እራት ለመብላት አበሻ ምግብ ቤት ቁጭ ብለናል፤ አዩ ባልንጀራየ ናት ፤ ለስድስት ወራት ያክል ብንተዋወቅም ሙሉ ስሟን አልነገረችኝም፤ ሙሉ ስሟ “ አያልነሸ” ወይም “ አያንቱ” ሊሆን ይችላል። ቅርብ ማዶ ካለው ጠረጴዛ ፊተለፊት ሁለት ፍቅረኛሞች ተቀምጠዋል፤ ሴቲቱ በሰውየው ትከሻ ላይ ዘንበል ብላ ታለቅሳለች ፤ ሰውየው በፈርጣማ ክንዱ አቅፎ እያባበላት ነው፤ “ልጂቱዋ ምን ሆና ነው እምትነፋረቀው?’ አልኳት አስናጋጂቱን። “እጮኛዋ ነገ ወደ ኢትዮጵያ ሊሄድ ነው፤ ዘመቻ” አለች አስተናጋጄ ጠረጴዛውን እያስተካከለችኝልኝ ። “ይገርማል! ሸገር ፤ መሀል ቦሌ ላይ የሚኖሩ ቤተሰቦችን ማየት የሚፈራ መአት ዲያስፖራ ባለበት አገር እንዲህ አይነት ቆራጥ ማየት ልብ ያሞቃል“ አለች አዩ። “የጠረጴዛው ልብስ በጣም ነው የሚያምረው “ አልኩማንበብ ይቀጥሉ... - [መጠናናት](https://shegerblogs.com/%e1%88%98%e1%8c%a0%e1%8a%93%e1%8a%93%e1%89%b5/): አንድ በድሜና በምጣኔ ሀብት የሚበልጠኝ ወዳጅ ነበረኝ ፤ አንዳንዴ በግድግዳ ስልክ ደውየ “ ለጥብቅ ጉዳይ ስለምፈልግህ እንገናኝ” ስለው ” ጋብዘኝ፥ ሊፍት ስጠኝ፥ ገንዘብ አበድረኝ፥ ዋስ ሁነኝ፥ ሽማግሌ ሆነኝ አትበለኝ እንጂ ለጥብቅም ሆነ ለላላ ጉዳይ ልታገኘኝ ትችላለህ ” ብሎ ይመልስልኝ ነበር ፤ እና እኔንም ፖለቲካ ጻፍ አትበሉኝ እንጂ ፌስቡክ ላይ ለማንዣበብ ቃል እገባለሁ። “እስቲ አንዴ እንደማመጥ !” አለ የዳምጠው ሹፌር፤ ድሮ ከትዳር በፊት መጠናናት የሚባል ነገር ነበር፤ አባቶቻችን ውሃ አጣጫቸውን ሲያጠኑ “ሙሽራዋ የማን ልጅ ናት? ዶሮ መበለት ትችላለች? ቤተእግዚሀር ትስማለች ?” በሚሉ ጉዳዮች ላይ ብቻ ይወሰኑ ነበር፤ የሙሽራዋ መልክ ራሱ በጫጉላው ቀን ብቻ የሚገለጥ “Top secret ነበር ። ዛሬ ከትዳር ቀርቶማንበብ ይቀጥሉ... - [መጠያየቅ](https://shegerblogs.com/%e1%88%98%e1%8c%a0%e1%8b%ab%e1%8b%a8%e1%89%85/): በቀደም ዩቲዩብ ላይ ስርመሰመስ አንድ ለየት ያለ ፕሮግራም አየሁ፤ ሁለት አርቲስቶች መድረክ ላይ ይቀርቡና ርስበርስ ቃለ መጠይቅ ይደራረጋሉ፤ ይካካባሉ ፤ ይሸነጋገላሉ ማለት ይሻላል። ቃለ መጠይቁ በገሀዱ አለም ያለውን እውነታ አያንጸባርቅም! በገሀዱ አለም፤ አርቲስት አርቲስትን ይቦጭቃል፤ አርቲስት ባርቲስት ላይ ይሸምቃል፤ አርቲስት እና አርቲስት እሳትና ጭድ ፥ አቤልና ቃየል፤ ኦባማና ቢንላዲን ናቸው። “በጠቅላላውም ባይሆን ባመዛኙ” እንዲል መንጌ። ባነሳሁት ፕሮግራም ላይ ወንድና ሴት አርቲስቶች ቀርበዋል፤ እና ወጋቸው እንደሚከተለው አካባቢ ነው ፥ እሱ – ጎበዝ ተዋናይት መሆንሽ መላው አለም የመሰከረው ሀቅ ነው! በበጎ አድራጎት ስራሽ ትንሿ አበበች ጎበና የሚል ስያሜ አግኝተሻል፤ ቁንጅናሽም በጣም አደገኛ ነው! ትዝ እሚለኝ የመጀመርያ ፊልማችንን ስንሰራ ፤ አንድ ካሜራማን ከጣራማንበብ ይቀጥሉ... - [( ግብዣው ፤ ቅጽ 2)](https://shegerblogs.com/%e1%8c%8d%e1%89%a5%e1%8b%a3%e1%8b%8d2/): ጓደኛየ ዘፈን መስራት ካቆመ አስር አመታት ያለፈው ድምጻዊ ነው። ዋና ስሙ ፋኑኤል ሲሆን ለደህንነቱ ሲባል ” ዘነመ” እያልሁ እጠራዋለሁ፤ ከቀናት ባንዱ ሰንበት “ወለላ “ ምግብ ቤት በረንዳ ተቀምጠን አስተናጋጅ እንጠብቃለን፤ አንዲት እንዲያው በደፈናው የአፈወርቅ ተክሌን ስእል የመሰለች ሴት ከፊታችን ብቅ አለች። “አድናቂ ነኝ” “በጣም አመሰግናለሁ” አልኩ፤ “ፈርምልኝ” “ምን ላይ ልፈርም?’ አንባቢያን ሆይ ! ባታምኑኝም ከመናዘዝ ወደ ሁዋላ አልልም፤ እየተሽኮረመመች “ጡቴ ላይ“ አለችኝ። እኔም ከኢትዮጵያ ባህል ጋር ላለመጋጨት፤ ከጡቷ ጋራ ደግሞ ሙሉ በሙሉ ላለመቆራረጥ ፤ የጡት ማስያዣዋ ላይ ፈረምኩ። “የት ነው እምትኖሪው?” “ ሪችመንድ ነኝ! ከሁለት ሳምንት በሁዋላ አገር ቤት እሄዳለሁ” “እቃ ይዘሽልኝ ትሄጃለሽ?” ‘ ኖ ፕሮብሌም! ይሄ ላንተ የማደረገው ትንሹማንበብ ይቀጥሉ... - [ለከፋ ችግር የማይዳርግ ለከፋ](https://shegerblogs.com/%e1%88%88%e1%8a%a8%e1%8d%8b-%e1%89%bd%e1%8c%8d%e1%88%ad-%e1%8b%a8%e1%88%9b%e1%8b%ad%e1%8b%b3%e1%88%ad%e1%8c%8d-%e1%88%88%e1%8a%a8%e1%8d%8b/): ከጥቂት አመታት በፊት” የምነው ሸዋ “ ባለቤት አቶ ሸዋ ኢተና፥ ለእህቱ ልደት፥ ዲሲ በሚገኝ ክለብ ውስጥ የእራት ግብዣ አዘጋጀ፤ በእሱ መጥርያ ወደ አሜሪካ የመጡ ዘፋኞች አንደኛው ጥግ ላይ ተከማችተው ተቀምጠዋል ፤ ፋሲል ደሞዝ ፥ አጫሉ ሁንዴሳ ፥ ሃይሉ ፈረጃ ፤ ሀፍቶም (አባቱን የረሳሁት) ዘፋኝ እና ሌሎች ድምጻውያን ነበሩ ። ይህን ማስታወሻ የጻፈው ጭሮ- አደርም የዘፋኝ ለምድ ለብሶ ተቀላቅሏል። እኛ ከተጠቀመጥንበት ጥግ የተረፈው የክለቡ ሆድ ፥ ካፍ እስከ ሰደፉ በሌሎች ደንበኞች ተሞልቷል ፤ ከወድያ ማዶ ጥግ የሆነ ሰውየ ሲመጣ ተመለከትኩት፤ የሚጨበሱ ፤ የሚደንሱ፤ ወይም ያለምንም አላማ በትጋት የሚቆሙ ሰዎችን እየጣሰ አሁንም አሁንም ” እስኪውዝ ሚ” እያለ እኛ ወደ ተቀመጥንበት ይሳባል ፤ማንበብ ይቀጥሉ... - [ምኞት፥ ስለ ለመጪው አሮጌ ዐመት](https://shegerblogs.com/%e1%88%9d%e1%8a%9e%e1%89%b5%e1%8d%a5-%e1%88%b5%e1%88%88-%e1%88%88%e1%88%98%e1%8c%aa%e1%8b%8d-%e1%8a%a0%e1%88%ae%e1%8c%8c-%e1%8b%90%e1%88%98%e1%89%b5/): አዲስ ሆኖ ይምጣ፤ መጪው አሮጌ ዐመት ሰው በውድ ይገመት እህልና ሲሳይ በርካሽ ይሸመት። በጦም በፍስክም፥ ዱላ ለምንጠግብ ጨቅላ ልጅ አስርበን፥ ጆፌ ለምንመግብ ሰላም ይለግሰን ከለታት አንድ ቀን ፥ የሰው ወግ ይድረሰን። ያርሶ በሌ ልጆች በእንግዳ ሰው እጆች ሳናረጅ ከመጦር፥ ይሰውረን ከጦር -ያስጥለን ከበቀል እንደ ድንኳን ችካል አመሻሽ ተተክሎ ፤ ጠዋት ከመነቀል ። በእልህ ምትክ መላ ልባችንን ይሙላ ። ጉልበቱን ለሚያመልክ ፤ ጉልበቱን ያቅልጠው ለደግ ሰው አክሊል ለክፉ ልብ ይሰጠው። ይፍለቅ ከየመስኩ የርህራሄና የማስተዋል ጠበል ቃል ምግባር ይወልዳል ፤ አሜን! ይሁን እንበል! - [ስለአወዳመት](https://shegerblogs.com/%e1%88%b5%e1%88%88%e1%8a%a0%e1%8b%88%e1%8b%b3%e1%88%98%e1%89%b5/): አሜሪካን አገር፥ አበሻና ላቲኖ የሚበዛበት ሰፈር ውስጥ ቤት ስከራይ ለደላላው እማቀርበው የመጀመርያው ጥያቄ “ ሽንት ቤቱ የብቻ ነው የጋራ ?” ሚል ነው። ወድጄ አይደለም፤ ደባል አበሻ ነህ እንበል! ዶሮ ወጥ ትወዳለህ! አሜሪካን አገር ያለው “ችክን” ደግሞ ችክ ያለ ነው ፤ አጥንት ያለው አይስክሬም እንደመብላት ልትቆጥረው ትችላለህ ። እናትህ የላክህላትን ዶላር መንዝራ ፤ ስድስት ዶሮ ረሽና ጉርድ በርሚል በሚያክል አገልግል አጭቃ ትልክልሀለች ፤ ዶሮ ወጡ ፤ ከናትህ ወደ መልክተኛው፥ ከፍሪጅ ወደ ሻንጣ ሲንከራተት ከርሞ ይደርሰሀል፤ አንተም ተቀብለህ በቅርስነት በማስመዝገብ ፋንታ ወደ ሆድህ ታዛውረዋለህ ! ከዚያ በማግስቱ የዳጉሳ ቂጣ እንደበላ ምስኪን ዘለግ ያለ ምጥ ይጠናብሀል፤( በተወለድሁበት አካባቢ ጤፍ መሸመት የማይችል ሰው ዳጉሳማንበብ ይቀጥሉ... - [ዘመም ይላል እንጂ](https://shegerblogs.com/%e1%8b%98%e1%88%98%e1%88%9d-%e1%8b%ad%e1%88%8b%e1%88%8d-%e1%8a%a5%e1%8a%95%e1%8c%82/): እንደ ጊዜው መክፋት እንደ ግፉ መስፋት እንዳገሩ ክስመት እንዳገሬው ጥመት እንደሰው ጭካኔ፥እንደ ልቡ ፍሬ ታምር ነው መትረፍሽ፥ ታምር ነው መኖሬ። የበጎ ሰው ሀሳብ፥ ሲካድ እለት በእለት ጉድጓድ ተምሶለት፥ ሰብእና ሲቀበር በዚህ ዓለም መኖር፥አያስመኝም ነበር ። ምድሩ ሳር ቅጠሉ፥ በስጋት ተሞልቶ የማለዳው ሰማይ፥ እንዳንቀልባ ቀልቶ ታረደ ነደደ ከዘብጥያ ወጥቶ ዘብጥያ ወረደ የሚል ዜና ብቻ ፥ አየሩን ሲሞላው ሰው በገዛ ጥላው ፥ በርግጎ ሲሸበር በዚህ ምድር መኖር፥ አያስመኝም ነበር ፤ አዎ ለጊዜውም ቢሆን ግፍ ያደነዝዛል በደል ያስተክዛል ጊዜም ጠብን ሽሮ፥ ወደ ፊት ይጓዛል በልብ ሰሌዳ ላይ፤ ቂም ይደበዝዛል በነገ ያመነ ልጁን ቀብሮ መጥቶ ፥ ሚስቱን ያስረግዛል። ይቅርታና ምህረት ፍቅርና ህብረት ከግፍ ጋርማንበብ ይቀጥሉ... - [ጎባጣው ትዳሬ](https://shegerblogs.com/%e1%8c%8e%e1%89%a3%e1%8c%a3%e1%8b%8d-%e1%89%b5%e1%8b%b3%e1%88%ac/): በየሳምንቱ ቅዳሜ አንድ መርህ አለኝ ፤ ያገርቤትም ሆነ የውጭ አገር ፖለቲካ ዜና እጦማለሁ፤ ኪነጥበብና ማህበራዊ ጉዳይ ላይ እጣድና ነፍሴን አለመልማታለሁ፤ በዚህ መሰረት ፥ ቅድም ዩቲዩብ ላይ ስርመሰመስ ቆየሁ። በቀደም አንድ የሞሮኮ ዜጋ የሆነ ዘፋኝ “ ሊጋባው በየነ” የሚለውን ዘፈን በራሱ ቃና ዘፍኖ አስደምሞኝ ነበር ፤ ዛሬ ደግሞ ሸገር ውስጥ በስደተኝነት የሚኖር ሶርያዊ ዘፋኝ “ ለዚህ ለዚህማ ምናለኝ አገሬ “ የሚለውን የጌቴ አንላይን ዘፈን ዘፍኖ አስለቀሰኝ። ወደ ፌስቡክ ተመለስኩ፤ ባለፈው አንዱ “ ላጤ” የሚለውን ግሩፕ እንድቀላቀል መጥርያ ልኮልኝ ነበር ፤ ያለሁበትን ተጨባጭ ሁኔታ ለመሰለል ፈልጎ ይመስለኛል፤ እኔም ግሩፑን ቀስ ብየ በለሆሳስ እየተራመድኩ ሰለልኩት፤ ፍቅር የተራቡ ” ሆርኒ” ወጣቶች የተደራጁበት ቡድን መሆኑንማንበብ ይቀጥሉ... - [ስለ ኢምፔርያሊዝም፥ አልልም ዝም](https://shegerblogs.com/%e1%88%b5%e1%88%88-%e1%8a%a2%e1%88%9d%e1%8d%94%e1%88%ad%e1%8b%ab%e1%88%8a%e1%8b%9d%e1%88%9d%e1%8d%a5-%e1%8a%a0%e1%88%8d%e1%88%8d%e1%88%9d-%e1%8b%9d%e1%88%9d/): (በእውቀቱ ስዩም ፤ የውስጥ አርበኛ) ያንደኛ ደረጃ ተማሪ እያለሁ የሆነ Bully የሚያደርገኝ ልጅ ነበር ፤ ስሙ ራሱ ሙሉጌታ ቡሊ መሰለኝ ካልተሳሳትኩ ፤ እና አንድ ቀን ሄጄ ኮሌታውን ጨምድጄ ያዝኩት፤ እሱም እጁን ወደ አንገቴ በመስደድ አጻፋውን ለመመለስ ኮሌታየን ይፈልግ ጀመር ፤ በጊዜው ኮሌታ ስላልነበረኝ የቡዳ መዳኒቴን ጨምድዶ ለመያዝ ተገደደ ፤ በዚህ አጋጣሚ፥ እኛ ሰፈር የነበረው ቡዳ ፥ መልክ ሳይሆን ጸባይ ያለውን እየመረጠ እሚበላ እንደነበር ላስታውስ እፈልጋለሁ። ተያያዘን፤ ተንሽ ተንገዳገድን ፤ ተንሸ ተቦጫጨርን፤ በቴስታ ልመታው ስሞክር ራሱ በጣም ራቀብኝ፤ ብቻ በድብድብና በዳንስ መካከል ያለ እንቅስቃሴ ስናካሄድ አንድ ሃያ ደቂቃ ሞላ፤ ደሞ ባጋጣሚ ሞላ የተባለ ቦርድ የወጣ አየር ወለድ በጋሪ ወደ አብማ ማርያምማንበብ ይቀጥሉ... - [[ዛሬ ቀን 11/12/13]](https://shegerblogs.com/6164-2/): ዛሬ ቀኑ 11 ወሩ 12 ዘመኑ ሁለት ሺ 13 (11/12/13) ነው። በዘመን ቀመር ቀን፣ ወር፣ ዓመት በአጻጻፍ 11/12/13 ሲደረደር ለዘመን ቀመር ተመራማሪ እጅግ ያስደስታል። ዛሬ በ11/12/13 ከጓደኞቼ መካከል ልደታቸውን የሚያከብሩ ነበሩና 11/12/13 ብለው ጽፈው በመመልከቴ ለእነርሱ የመልካም ልደት መታሰቢያ እንዲሆን የቁጥሩ መንፈሳዊ ቀመር ትርጓሜን 11/12/13 ጻፍኩት ሌሎቻችሁም ለዕውቀት ብታነቡት ደስ ይለኛል። ቊጥር 11 ቊጥርን ለሚመረምሩ ሰዎች 11 የውሳጣዊ ግጭት፣ ዐመጽ፣ ተቃውሞ፣ የፍርድ ምሳሌ ያደርጉታል።ምክንያታቸውም ቊጥር 7 እና 10 ፍጹም ቊጥርን ወካይ ናቸው። ለምሳሌ 7 የሳምንቱን ፍጹም ዑደትን የያዘና የፍጹም ሰው መሆን ቁጥር 4 ባሕርያትና 3 ባሕርያተ ነፍስ 4+3=7ሲሆን፤ ቊጥር 10 ደግሞ የአምላክ 10ሩን ትእዛዛት፣ ወካይ ነው። ቀጣዩ 11 ግን ይህንንማንበብ ይቀጥሉ... - ["አይ ምፅዋ"](https://shegerblogs.com/%e1%88%9d%e1%8d%85%e1%8b%8b/): በዕለቱ (የካቲት 9/1982) የ6ኛው ነበልባል ክፍለ ጦር ዋና አዛዥ የነበሩት ብ/ጀኔራል ተሾመ ተሰማ ከጠዋቱ 1፡30 ላይ በምፅዋ ከተማ ርዕሰ ምድርዕ በተባለ አካባቢ የተወሰኑ የጦር መኮንኖችንና ባለሌላ ማዕረግተኞችን ሰብስበው ንግግር አደረጉ። ንግግራቸውም … “እኔ የሚፈለግብኝን አደራ ተወጥቻለሁ። ከጥር 30 ቀን 1982 ዓ.ም እስከ ዛሬ የካቲት 9 ቀን 1982 ዓ.ም የሞት ሽረት ትግል አድርጌያለሁ። የሻዕቢያን የጥፋት ዓላማ ለመግታት ያላደረኩት ጥረት የለም። ከዚህ በኋላ ግን የራስን ሕይወት በክብር ከማጥፋትና ለኢትዮጵያ ጀግኖችና ታሪክ ጸሃፊዎች ታላቅ ተምሳሌት ከመሆን ሌላ አማራጭ የለኝም።” አፄ ቴዎድሮስ በእንግሊዞች እጅ ወድቀው ከመዋረድ ሞትን መርጠው የራሳቸውን ህይወት መቅደላ ላይ አጠፉ። እኔ ደግሞ በተራዬ ከኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥት የተሰጠኝን የጄኔራልነት ማዕረግ ሳላስደፍር ለመንግስትናማንበብ ይቀጥሉ... - [ካልፎሂያጁ ማስታወሻ](https://shegerblogs.com/%e1%8a%ab%e1%88%8d%e1%8d%8e%e1%88%82%e1%8b%ab%e1%8c%81-%e1%88%9b%e1%88%b5%e1%89%b3%e1%8b%88%e1%88%bb-4/): ‘ እቴ ሸንኮሬ’ የተባለ ያበሻ ሬስቶራንት ውስጥ ተቀምጨ ያዘዝኩትን በያይነቱ እጠብቃለሁ፤ ከፊትለፊቴ ባለው ግድግዳ ላይ የነገስታት ምስሎች ተደርድረው ይታያሉ፤ አጼ ቴዎድሮስ፥ ሀጸይ ዮሀንስ ፥ አጼ ምኒልክ ፥ ልጅ ኢያሱ፤ አጼይት ዘውዲቱና አጼ ሐይለስላሴ ይታዩኛል፤ ሰአሊው አጼ ተክለጊዮርጊስን ዘሏቸዋል። ያዘዝኩት ምግብ መጣልኝ ፤ በያይነቱ ብለው ያቀረቡልኝን አየሁትና ለረጅም ደቂቃ ተከዝኩ። ብጫ ክክ- ቀላ ያለ ክክ-ቀለም አልባ ክክ፤ ክክ በየፈርጁ ነው ያመጡልኝ፤ አንዱን ፍንካች ክክ ብድግ አድርጌ በመዳፌ መዘንኩት ፤ ቀዳዳ ቢበጀለት የካፖርት ቁልፍ ይሆናል ፤ ክኩ እንዲህ ከጠበደለ አተሩ ምን ሊያክል ነው? ከቶ በምን ከኩት? በቡልዶዘር መሆን አለበት ፤ ኢትዮጵያ ውስጥ በመጥፋት ላይ የሚገኘው ቀይስር በስፋትና በጥራት ተሰርቶ፤ የጽጌረዳ ጉንጉን መስሎማንበብ ይቀጥሉ... - [ሐዲስ አለማየሁ](https://shegerblogs.com/%e1%88%90%e1%8b%b2%e1%88%b5-%e1%8a%a0%e1%88%88%e1%88%9b%e1%8b%a8%e1%88%81/): ሐዲስ አለማየሁ የበዛብህ እና የጉዱ ካሳ ቅልቅል ናቸው። በዛብህ የተማሪነታቸው ጉዱ ካሳ የአዋቂነታቸው። በሚቀጥሉት ሁለት ታሪኮች በሐዲስ አለማየሁ ነፍስ ውስጥ ስናጮልቅ ጉዱ ካሳንና በዛብህን እናገኛለን! ፨፨፨ ያንድ ሃገር ሕዝቦቹ በሙሉ ያብዱና ንጉሡ ብቻ ጤነኛ ነበር። ህዝቡ ግን ወጥቶ ንጉሡ አበዱ እያሉ ይጮሁ ነበር። ንጉሱ ግራ ገባው፤ ልብሱን አውልቆ ተመሳሰላቸው። አውቆ የአበደ መሰለ️። ካሳ ዳምጤ አይመሳሰልም። አለም ሁሉ ቢያብድ ብቻውን ጤነኛ ሆኖ የመኖር ብቃት አለው። ትንሹ የዲማ አለም ለፊታውራሪ መሸሻ ቢሰግድ አብሮ አያጎነብስም። በአማርኛ ስነፅሁፍ ውስጥ እንደ ካሳ ዳምጤ አብረቅራቂ ገፀባህሪ የለም። ታድያ ካሳ ዳምጤ ሙሉ ለሙሉ ፈጠራ አይደለም። ካሳ ዳምጤ ሃዲስ አለማየሁ ናቸው። በራሳቸው ላይ ተመስርተው ነው የፃፉት። ሃዲስ አለማየሁማንበብ ይቀጥሉ... - [ፅነፈኝነትን መፍጠር (Radicalization)!](https://shegerblogs.com/%e1%8d%85%e1%8a%90%e1%8d%88%e1%8a%9d%e1%8a%90%e1%89%b5%e1%8a%95-%e1%88%98%e1%8d%8d%e1%8c%a0%e1%88%ad/): ፅንፈኝነት በምታምንበት አቋም ላይ ጫፍ መድረስ ነው። በዚህ ዓለም ላይ በያዝከው ጫፍ አቋም ላይ ተንጠላጥለው የጫፍ ጫፍ እንድትደርስ የሚያበቁ አንድ ሺህ ምክንያቶችን ጧት ማታ በገፍ እየሰጡ ጫፍ የሚያስረግጡህ የፅንፈኝነት ፈጣሪዎች አሉ። ለምሳሌ ሁሉም ኢተዮጵያዊነትህን አፍቃሪ ሕዋሳትህ እስኪያልቁብህ ድረስ አሰቃይተው፣ ቀምተው፣ ረግጠው፣ ዘርፈው፣ አስረው… ሁሉንም መጥፎ ነገሮች ፈፅመውብህ “ኢትዮጵያዊነቴ ከመከራ በቀር ምን አስገኘልኝ?” እንድትል የሚያስገድዱህ የፅንፍ ፈጣሪዎች አሉ። ኢትዮጵያዊነትህን ተቀብለህ በኢትዮጵያዊነትህ ተደስተህ ለመኖር የሚያስችሉ ምክንያቶችህን በየተራ አንድ በአንድ የሚጨርሱብህ ሰዎች። ኢትየጵያዊነትህን ስታስብ በዓለማቀፍ የእርዳታ ለጋሽ ሀገራትና ተቋማት ፊት ሁሌ የደረቀ ገላ ያላቸው ህፃናት ምስሎች ለማሻሻጫነት እየቀረቡ “አስቸኳይ” እርዳታ ሲለመንልህ ይታሰብሃል? ኢትዮጵያዊነትህን ስታስብ በየጎዳናው የተዘረሩ ውር ውር የሚሉ በሰው ልጅ ክቡር ፍጡርነትማንበብ ይቀጥሉ... - [Déjà Vu / ዲጃቩ !](https://shegerblogs.com/deja-vu-%e1%8b%b2%e1%8c%83%e1%89%a9/): ከቀናት በፊት አዋሬ አካባቢ … ልክ ከታክሲ እንደወረድኩ ዝናብ ይዘንብ ስለነበር ተራሩጬ እግሬ እንዳመራኝ ተደርድረው ከተሰሩት ሱቆች ወደ አንዱ በረንዳ አመራሁ። የኮስሞቲክስ መሸጫ ሱቅ ነበር የተጠለልኩበት በረንዳ። ወደ ካሳንቺስ አዘውትሬ ብመላለስም አዋሬ ሚባለውን ሰፈር ግን አላውቀውም ነበር። መንገዱ ላይ ህዝቤ ዝናቡን ለማምለጥ ይራወጣል! ድንገት አጠገቤ በሰፊ ትሪ ሻይና ወተት የያዘች ሴት ገፋ አድርጋኝ ወደ ኮስሞቲክሱ ቤት ገባች! የልጅቷ ጥድፍ ጥድፍ ማለት ገርሞኝ በአይኔ ተከተልኳት የሆነ የካፌ አስተናጋጅ ሽርጥ አድርጋለች ትሪውን የኮስሞቲክሱ መደርደሪያ ላይ አስቀምጣ ሻዩን ከመደርደሪያው ጀርባ ላለች ወፈር ያለች ሴት አቀበለቻት ፣ ቀስ ብላ ደሞ ወተቱን ከመደርደሪያው ወዲህ በርጩማ ላይ ለተቀመጠ ወጣት ልጅ አቀበለችው ! የስኳር እቃ አቀበለቻቸውና እመለሳለሁማንበብ ይቀጥሉ... - [ትውስታ ስለ ጀግናው አበበ ቢቂላ](https://shegerblogs.com/%e1%89%b5%e1%8b%8d%e1%88%b5%e1%89%b3-%e1%88%b5%e1%88%88-%e1%8c%80%e1%8c%8d%e1%8a%93%e1%8b%8d-%e1%8a%a0%e1%89%a0%e1%89%a0-%e1%89%a2%e1%89%82%e1%88%8b/): የታሪካዊዎቹ ጥቅምት 10 እና ጥቅምት 11 52ኛ ዓመት እና 56ኛ ዓመት ‹‹ማሞ›› ‹‹አቤት አበበ›› ‹‹እኔ ሩጫውን አልጨርሰም ላቋርጥ ነው›› ‹‹ምን! አዝናለሁ›› ‹‹ማሞ አደራህን እንድታሸንፍ፣ ከኛ ማለፍ የለበትም›› ‹‹እሺ አቤ›› ‹‹አደራ›› ዕለቱ እሑድ ጥቅምት 10 ቀን 1961 ዓ.ም. ከሃምሳ ሁለት ዓመት በፊት ነበር። የሜክሲኮ ኦሊምፒክ የማራቶን ሩጫ የተካሄደበት ቀን። የሮምና የቶኪዮ ኦሊምፒክ የማራቶን ባለድሉ አበበ ቢቂላ ሦስተኛውን ወርቅ ለማሸነፍ ሲሰለፍ አብረውት ማሞ ወልዴና መርዓዊ ገብሩም ነበሩበት። በውድድሩ ሒደት 17 ኪሎ ሜትርን እንዳለፉ ነበር፣ አበበ ቢቂላ ድንገት ወደ ማሞ ወልዴ ቀርቦ ከላይ የተጠቀሰው ምልልስ ያደረጉት። ከ41 አገሮች 75 ተወዳዳሪዎች በተሳተፉበት የሜክሲኮ ማራቶን አበበ ቢቂላ ጨምሮ ዐሥራ ስምንቱ ውድድሩን አቋርጠዋል። በአገሬው ሰዓት አቆጣጠርማንበብ ይቀጥሉ... - [ሠማየ ውድውድ (ምዕራፍ፡፫)](https://shegerblogs.com/%e1%88%a0%e1%88%9b%e1%8b%a8%e1%8d%a1%e1%8b%8d%e1%8b%b5%e1%8b%8d%e1%8b%b53/): እና፥በእዚህ፡አስደናቂ፡ጎዞ፡ወቅት፡ነው፥ለተረት፡የማይመስል፣ለዕውን፡የሚያስፈራ፣ለግምት፡የቸገረ፡`ኣጋጣሚ`፡ከፊት፡ለፊታችን፡የተደቀነብን።የሆነው፡ስለ፡ሆነ፡እና፤መዝገብ፡የሙያ፡ግዴታዬ፡በመሆኑም፤አነሆኝ፤ገጠመኙን፡እንደሚከተለው፡ከትቤዋለሁ።ትርጉም፥የግል፣ዕምነትም፡የተጸውዖ፡ናቸው፡እና፥እንደመሰላችሁ፡ተረዱት። - [የባንዲራው ጦርነት!! (ዝክረ ኢታሎ ቫሳሎ)](https://shegerblogs.com/%e1%8b%a8%e1%89%a3%e1%8a%95%e1%8b%b2%e1%88%ab%e1%8b%8d-%e1%8c%a6%e1%88%ad%e1%8a%90%e1%89%b5/): …ድርጊቱ የተከሠተው በጋና አክራ በተዘጋጀው በአራተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ጫወታ ላይ ነው። 3ኛውን የአፍሪካ ዋንጫን ያሸነፈችው ኢትዮጵያ ከጋና ጋር እየተጫወተች ነበር። በወቅቱ የኢትዮጵያ ልኡካን ቡድን ወደ ጋና ከገቡበት ጊዜ ጀምሮ ብዙ በደሎች ሲደርስባቸው ስለነበር በመጥፎ ስሜት ነበር ወደ ሜዳ የገቡት። በጨዋታው ላይ በጉዳት ምክንያት ያልተሳተፈው “ኢታሎ ቫሳሎ” ክራንቹን እንደያዘ ቤንች ወንበር ላይ ተቀምጧል። ገና ከጅምሩ የኢትዮጵያ ባንዲራ ሆን ተብሎ ተዘቅዝቆ እንዲሰቀል በመደረጉ ተናዶ አምባጓሮ ፈጥሮ እንዲስተካከል ያስደረገው ኢታሎ ነበር። … ኢታሎ የአስመራ ተወላጅ ሲሆን በወቅቱ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ይጫወት ነበር። ጨዋታው ቀጥሏል። በዳኛው አድሏዊነት ምክንያት ኢትዮጵያ ላይ አንድ ጎል ተቆጠረ። የኢታሎ ንዴት ይበልጥ ናረ! ጎሉ ሲቆጠር በጫወታው ላይ የክብር እንግዳ የነበሩትማንበብ ይቀጥሉ... - [እራሱን ያስተማረው ምሁር](https://shegerblogs.com/%e1%8a%a5%e1%88%ab%e1%88%b1%e1%8a%95-%e1%8b%ab%e1%88%b5%e1%89%b0%e1%88%9b%e1%88%a8%e1%8b%8d-%e1%88%9d%e1%88%81%e1%88%ad/): ብዙዎቻችን አንድን ሰው የተማረ ነው የምንለው ወይም ደግሞ እውቀቱን የምንለካው በቆጠራቸው ክፍሎች አለያም በድግሪ፣በማስትሬት እና ዶክትሬት ደረጃው ነው።ነገር ግን እምብዛም በአለማዊ ትምህርት ሳይገፉ ጥበብን የታደሉ እንዲሁም እውቀትን በማንበብ ብዛት ያዳበሩ በየአገሩ ብዙ ሰዎች አሉ። ቢልጌትስ እና የፌስቡክ ባለቤት ማርክ የጀመሩትን ኮሌጅ እንኩዋን አልጨረሱትም። ወደ አገራችን ስንመጣ ብዙ አርቲስቶችን ወይንም ታዋቂ ሰዎችን መጥቀስ ቢቻልም።ዛሬ ስለታላቁ የጥበብ ሰው ጳውሎስ ኞኞ ጥቂት ልል ወደድኩ።በጣልያን ወረራ ምክንያት ትምህርቱን ከአራተኛ ክፍል ማዘለል አልቻለም ነገር ግን አያሌ መጻህፍትን ሳይታክት አነበበ። ‘ንባብ ደግሞ የማይገፋው የመሃይምነት ተራራ የለምና ጳውሎስ የመሀይምነትን ግንብ ደርምሶ ከጥበብ ማማ ላይ ደረሰ’። ከጥበብ አናት ላይ ሆኖ ዘመንን ለማሸነፍ በዘመን ሳይቀደም እውቀቱን ለኛ አካፍሎን አለፈ።ማንበብ ይቀጥሉ... - [የእናኑ መልዕክት ለሽሮ ሜዳ ዜጎች](https://shegerblogs.com/%e1%8b%a8%e1%8a%a5%e1%8a%93%e1%8a%91-%e1%88%98%e1%88%8d%e1%8b%95%e1%8a%ad%e1%89%b5-%e1%88%88%e1%88%bd%e1%88%ae-%e1%88%9c%e1%8b%b3-%e1%8b%9c%e1%8c%8e%e1%89%bd/): . . . ሁሉን ነገር ካስተዋሉት ያስገርማል። የኑሮ ትንሽ የለውም። እዛ የወደቀችው ሳር አስገራሚ ናት። ወፍ ለቅሞ ጎጆ ይሰራባታል። ይሄን ሳር አጭዶ ያመጣው ማጭዱ አስገራሚ ነው። ሰዎቹ ማጭድ ማሰባቸው?! .. ሳሩን አጭዶ ያመጣልኝ ሰውዬ ዘገየ ይባላል። ጨዋታ ያውቃል። እሱ ሲያወራኝ የሚገርም ነው ታሪኩ። ‘ለምን?’ ብትል እንዳው ወንድ ሆነ እንጂ ታሪኩ ተኔው አንድ ነው። የእኔ ታሪክ ምንም ብለፋ፣ ምንም ብቀባጥር የእኔ ብቻ አይሆን። ‘ለካ የእሱ የእኔን ይመስላል!’ ብለህ መታዘብ አለ። ያንተ የአንተ ተሆነ፣ የእናትህ የእናትህ ተሆነ፣ የሰብለ የሰብለ ከሆነ፣ እንዴት እዝህ ደረስን? እሱ እኮ ነው! *** ጠዋት እዚህ ፀሐይ ስሞቅ የቆረጥኩት የአውራ ጣቴ ጥፍር ለስንት ጉንዳን እራት ይሆናል? ባላርስም አበላሁ ማለትማንበብ ይቀጥሉ... - [...ገነት](https://shegerblogs.com/%e1%8c%88%e1%8a%90%e1%89%b5/): ” እየተስለመለምኩ ፊትዋን በሁለት እጆቼ ያዝኩ . . አሟልጮኝ እንደሚወድቅ ሁሉ. . . እንደሚፈስ ሁሉ . . . ፊቴ ገነት ፊት ላይ ወደቀ… አፌ ዉስጥ ከንፈሮቿን እንደ ቢራቢሮ ክንፎች ይዤአቸዋለሁ በገላዬ ዉስጥ አየር እንደሚያልፍ ሁሉ ነበር . . . እንኰይ እንኰይ ከሚል….. ዉሃ እናቶች ከሚከናበሉበት የአምቦ ምንጭ ዉስጥ እንደተኛሁ ነበር . . . ዐይኖቿ … ወተት መሃል እንደወደቁ አጋሞች ነበሩ . . . ልቤ እንዳይፈነዳ እፀልያለሁ .. ልቤ እንዳይፈርስ እንቀጠቀጣለሁም … ጣቶቼ በጀርባ ቆዳዋ ላይ ተማስለዉ እንደተኙ ነበር ደማችን ተደባልቆ ሲፈስ….. ፈረሰኛዉ ከተራሮች በላይ ነበር መዝፈን አማረኝ . . . እንደ ንጋቷ ከልካይ መዝፈን አማረኝ… እንደጥላሁን መጮህ አማረኝ… እንደ አስቴርማንበብ ይቀጥሉ... - [እመነኝ፣ እምነትና ሐይማኖት የዘር ጭፍጨፋን አያስቆሙም!](https://shegerblogs.com/%e1%8a%a5%e1%88%98%e1%8a%90%e1%8a%9d%e1%8d%a3-%e1%8a%a5%e1%88%9d%e1%8a%90%e1%89%b5%e1%8a%93-%e1%88%90%e1%8b%ad%e1%88%9b%e1%8a%96%e1%89%b5-%e1%8b%a8%e1%8b%98%e1%88%ad-%e1%8c%ad%e1%8d%8d%e1%8c%a8/): እመነኝ፣ እምነትና ሐይማኖት የዘር ጭፍጨፋን አያስቆሙም! ጭፍጭፍ ሲጀመር ፈጣሪ ከሥፍራው ይሰወራል!? “In Search of Rwanda’s Génocidaires – French Justice and the Lost Decades” (Author: David Whitehouse, 2014) ሳላስበው በዓመታት ውስጥ አንድ፣ ሁለት፣ እያልኩ የሩዋንዳን የዘር ጭፍጭፍ (ጄኖሳይድ) ታሪክ ከሚከታተሉ መሐል ተደብልቄ ራሴን አገኘሁት። ለምን? እና እንዴት? የሚሉ ጥያቄዎች ሳይሆኑ አይቀሩም ወደዚያ የዘር ጭፍጨፋ ታሪክ ደጋግመው የሚስቡኝ። እነዚሁ ተመሳሳይ ጥያቄዎች ናቸው ወደ አይሁዳውያን ጭፍጨፋ፣ እና በተለያዩ አህጉራት ባሉ ቀደምት ህዝቦች ላይ ቀደም ባሉ ክፍለዘመናት ወደ ተካሄዱት የዘር ጭፍጨፋዎች አትኩሮቴን የሚስቡት። ‹‹የዘር ጭፍጨፋ›› የሚል ስም ይሰጣቸውም አይሰጣቸውም፣ ባለፉት ሁለትና ሶስት ክፍለዘመናት ውስጥ የሰው ልጅ ያስተናገዳቸው አሰቃቂ የዘር ጭፍጨፋዎች የተከናወኑት ጠንካራ የፈጣሪ እምነትማንበብ ይቀጥሉ... - [ስጦ-ታ](https://shegerblogs.com/%e1%88%b5%e1%8c%a6-%e1%89%b3/):  የሆነ ነገር የሚሸጥበት ቤት አለ፤ የሆነ ነገር ገዝቼ ከከፈልኩ በሁዋላ ፤ “እዚህ ቀረህ እንዴ? “ አለቺኝ፤ “ አይ! ልደቴን ለማክበር ወጣ ብየ ነው እንጂ ኢትዮጵያ ነው እምኖረው” ያብማይቱ! ይህን ያህል የመጎረር ብቃት አለኝ!? “ ስንት አመት ሆነህ?” እጇን ሳብ አርጌ መዳፏ ላይ ጻፍኩላት። “ብዙ አይደለም” አገጨን ዳርዳሩን የከበቡትን ሽበቶች እየጠቆምኳት “ አታይም እንዴ! ስጦ ቃሚ ፍየል መስየ ” አልኳት፤ ትስቃለች ብየ አስቤ ነበር ፤ አልተሳካም ፤ ሳስበው ልጂቱ ስጦ እሚባል ነገር አታወቅም ፤ የተከካ አተር በሩ ላይ ለኢግዚብሽን በማቅረብ የሚታወቀው የመጨረሻው ትውልድ አባል መሆኔ ትዝ አለኝ ፤ አገጬ ላይ ከተዘመዘሙት የሽበት ቡቃያዎች በላይ ይህ ግኝት ልቤ ውስጥ የአምስት ደቂቃ ከሁለትማንበብ ይቀጥሉ... - [የቀይ ልክፍት](https://shegerblogs.com/%e1%8b%a8%e1%89%80%e1%8b%ad-%e1%88%8d%e1%8a%ad%e1%8d%8d%e1%89%b5/):  “ጥሬ ስጋ በቀይ ወይን ምሳ ልጋብዝሽ” ብሎ ነው የጀመረኝ። “በደስታ” አልኩኝ። ጥሬ ስጋ ነፍሴ እንደሆነ ማንም ያውቃል።…… “ምሳ በልቼ አሁን መጣሁ” ብዬ ከቤት ወጥቼ የሚቀጥለውን ቀን ምሳ በልቼ ተመለስኩ። በቁርጥ ሰበብ ስንቋረጥ ዓመት ሆነ።…… “ሜዬ ገብቶልሻል ይሄ ልጅ! “ይሉኛል ጓደኞቼ…… በፍፁም! በጠዋት ደውሎ ካላሳቀኝ ደህና ዋዪልኝ ካላለኝ ደህና አልውልም እንጂ ፍቅር አልያዘኝም። ደሞ ምሳ ሰዓት ላይ ደውሎ “የት ነሽ? እ? ልይሽ? ” ካላለኝ እህሉን እንደቀሙት ህፃን እነጫነጫለሁ እንጂ ፍቅር አልያዘኝም። ማታ ደውሎ ደህና እደሪ ካላለኝም አድራለሁ እንቅልፍ በዓይኔ አይዞርም እንጂ…… “ኸረ ሜዬ ገብቶልሻል! ” ይሉኛል ጓደኞቼ ለወትሮው ስንገናኝ አዲስ ስለወጣ መፅሃፍ በመጨቃጨቅ የምናጠፋውን ቅዳሜ ከሰዓት እኔ አዲስ ስለሆነው የኔ ታሪክ፣ማንበብ ይቀጥሉ... - [ሁለቱ ባሎቼን ላስማማ እያሸማገልኳቸው ነው (ክፍል 11 - የመጨረሻ ክፍል)](https://shegerblogs.com/%e1%88%81%e1%88%88%e1%89%b1-%e1%89%a3%e1%88%8e%e1%89%bc%e1%8a%95-%e1%88%8b%e1%88%b5%e1%88%9b%e1%88%9b-%e1%8a%a5%e1%8b%ab%e1%88%b8%e1%88%9b%e1%8c%88%e1%88%8d%e1%8a%b3%e1%89%b8%e1%8b%8d-11/): ሁለቱ ባሎቼን ላስማማ እያሸማገልኳቸው ነው (ክፍል 11 የመጨረሻ ክፍል) እንደዛ ከደነፋ ከቀናት በኋላ የተመራቂ ተማሪዎች ፓርቲ አዘጋጅተን ዝግጅቱ የነበረው ከተማ ነበር። ልንመረቅ ሁለት ወር ነበር የቀረን። እኔን ብሎ ደግሞኮ ተተራማሽ። መግቢያ ትኬት ምናምን እየሸጥኩ ስተራመስ ከርሜ የፓርቲው ቀን ጠዋት ከጓደኞቼጋ ጫማ ልንገዛ ከተማ ስንወጣ አገኘሁት። ምንም እንዳላደረገ …… እንደዛ እንዳልደነፋ (ማለት ሁኔታውኮ የዛን ቀን ሳይገለው የሚያድር አይመስልም ነበር።) “እንዴት ነሽ እማ?” አላለም? “ደህና!” አልኩት ግራ ገብቶኝ። ሁኔታው የሰማሁትን እንድጠራጠር አደረገኝ። “ዛሬ ፓርቲ አላችሁኣ??”አለኝ ደነገጥኩ። እየተከታተለኝ እንደሆነ ገባኝ ግን ዝግጅቱ የነበረው ማታ ከ2 ሰዓት ጀምሮ ስለነበር ቢያንስ ቺኩን ትቶ አይመጣም ብዬ ተረጋጋሁ። “ይመችሽ ፈታ በይ!! ይገባሻል!!” ብሎኝ እንደሰላማዊ ሰው ቻው ብሎኝማንበብ ይቀጥሉ... ## Pages - [Data Deletion](https://shegerblogs.com/data-deletion/): [wpforms id=”5821″] - [Privacy Policy2](https://shegerblogs.com/privacy-policy2/): Shegerblogs.com built the DailyLaughter app as a Free app. This SERVICE is provided by Shegerblogs.com at no cost and is intended for use as is. This page is used to inform visitors regarding my policies with the collection, use, and disclosure of Personal Information if anyone decided to use my Service. If you choose to use my Service, then you agree to the collection and use of information in relation to this policy. The Personal Information that I collect is used for providing and improving the Service. I will not use or share your information with anyone except as describedማንበብ ይቀጥሉ... - [Privacy Policy](https://shegerblogs.com/privacy-policy/): Shegerblogs app is a Free app. This SERVICE is provided by ikansoft.com at no cost and is intended for use as is. This page is used to inform visitors regarding our policies with the collection, use, and disclosure of Personal Information if anyone decided to use our Service. If you choose to use our Service, then you agree to the collection and use of information in relation to this policy. The Personal Information that we collect is used for providing and improving the Service. We will not use or share your information with anyone except as described in this Privacyማንበብ ይቀጥሉ... - [](https://shegerblogs.com/shegerfm/): [php snippet=1] ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ በቀጥታ እዚህ ያድምጡ – Listen Sheger FM 102.1 LIVE here   ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 [mashshare]       - [Ethiopian Music](https://shegerblogs.com/ethiopian-music/): Listen Non-stop Ethiopian Music Online [mashshare] - [ስለ ኮፒ ራይት እና የተጠቃሚዎች ግዴታ](https://shegerblogs.com/%e1%8a%ae%e1%8d%92-%e1%88%ab%e1%8b%ad%e1%89%b5/): ኮፒ ራይት / ዲሰክሌመር - [አግኙን](https://shegerblogs.com/%e1%8b%ad%e1%8d%83%e1%8d%89%e1%88%8d%e1%8a%95/) - [አባል ለመሆን ይመዝገቡ](https://shegerblogs.com/%e1%8b%ad%e1%88%98%e1%8b%9d%e1%8c%88%e1%89%a1/): [ajax_register] - [የአባሎች መግቢያ](https://shegerblogs.com/%e1%88%98%e1%8c%8d%e1%89%a2%e1%8b%ab/): [ajax_login] - [ፀሓፊዎች](https://shegerblogs.com/%e1%8d%80%e1%88%93%e1%8d%8a%e1%8b%8e%e1%89%bd/) [comment]: # (Generated by Hostinger Tools Plugin)