Tidarfelagi.com

የጥንቷ አባ ኮራን ሸቀጣ ሸቀጥ መደብር እናስታውሳት

La Tribuna ተብላ ከምትጠራው የጥንት የፈረንሳይኛ መጽሄት ላይ የገኘሁት የዝች ምስሉ ላይ የምትታየው Super market አባ ኮራን በሚል ቅጥል ስም በምዕራባውያን አቆጣጠር በ1914 ዓም ላይ በጥንቱ ሰራተኛ ሰፈር አካባቢ ተክፋታ ህብረተሰቡን ስታገልገል ቆይታ ከዛም በምዕራባውያን አቆጣጠር በ1936 ዓም በጥሊያን ወራራ ዘመን ” Caratoleria Garami” በሚል መጠሪያ ተሰይማ እና ወደ ማተሚያ ቤት (Stationery) ተቀይራ ለዘመናት የኖረችው ስለዝች ሱቅ የሚገልጽ ሌላ ተጨማሪ መረጃ ካላችሁ አክሉበት።

ከመቶ አመት በፊት የኖረችው ይህቺ መደብር በእኔ ግምት በአዲስ አበባ ከተማ የመጀመሪያዋ ዘመናዊ Super Market ትሆናለች የሚል እምነት አለኝ ግን የጥንት የአራዳ ልጆች ለምን አባ ኮራን ብለው ሰየሟት? ኮራንብሽ ለማለት ይሆን እንዴ? በዚህ የሩቅ ትውልድ የኖረው ወተት ከበረት ቅቤ ከማጀት የማያጣው በእንዶድ ሸማውን የሚያጥበው, በሰላ ቀላጭ ጢሙን እና ጸጉሩን የሚላጨው እንዲሁም ሁሉ በእጁ ሁሉ በደጁ የሆነው አባ ይሁኔ ለምንስ መደብር አስፈለገው?

ከዚህ ምስል ላይ ከመደብሩ አጠገብ የምትታየው ሻይ ቤት ቢጤ የጥንቱ ድንቅ ሰው ጳውሎስ ኞኞ የግሪኮች ሻይ ቤት ብሎ የነገርን ትሆን እንዴ? በመጨረሻ በጽሁፊ ላይ ዘውትር የምጠቀመው ሰም “አባ ይሁኔ” ክፉንም ደጉንም ከፈጣሪ የመጣ ከሆነ በቃ ይሁን ብሎ ተቀብሎ እጅ ነስቶ የኖረውን የቅድም አያቴን የአይዋ ሰዒድን የሩቅ ትውልድ የምገልጽበት የታሪክ ጦማር ገጸባህሪ ነው።

One Comment

  • በላይ commented on February 13, 2020 Reply

    ጥሩነው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *