በድንገት ከኋላዬ መጥተህ አትንካኝ ብዬህ ነበር፡፡
ያጠብኳቸውን ብርጭቆዎች አንድ በአንድ እያደረቅኩ ከጀርባዬ መጥተህ ስትጎነትለኝ ጩኸቴን ለቀቅኩት፡፡
በድንጋጤ የወረወርኩት ብርጭቆ ወለሉ ላይ አርፎ ሲበተን አንዱ ስባሪ እግሬ ላይ ተሰካ፡፡ማንበብ ይቀጥሉ…
መልካም ጋብቻ
(ከማታ ማታ መጽሐፌ (2012 ዓ.ም.) ከጓደኞቼ ማኅደርና እስከዳር ጋር፣ ዘናጭ ካፌ ቁጭ ብለን ውድ ማኪያቶ እየጠጣን ነበር፡፡ ማኪያቶው አሪፍ፣ ጨዋታው ደማቅ ነበር፡፡ መርዶዬን እስኪነግሩኝ… “ናሆምና ማርታ ሊጋቡ ነው” እስኪሉኝ፡፡ እንደሰማሁ በድንጋጤ ምራቄ ከአፌ አለቀ፡፡ በማኪያቶ የሞቀ ሰውነቴ በአንድ ጊዜ ቀዘቀዘ፡፡ማንበብ ይቀጥሉ…
ቀኑ እንዴት ይመሻል ያንን ሳናነሳ
አዝማሪ ወርቄ (ሻምበል ወረቀት) እንዲህ ይል ነበር፤ “ቢናገሩ አፈኛ፤ ዝም ቢሉ ሞኝ ቢወፍሩ ዝሆን፥ ቢቀጥኑ ትንኝ ‘ አወይ ሰው! አወይ ሰው! ሰው አስቸገረኝ” ካዝማሪው የተረፈውን እነዲህ መዘርዘር ይቻላል- ብትጋብዝ “ አባካኝ “ ትባላለህ- ብትቆጥብ “ ቁዋጣሪ” – ብታሞግስ “ አሽቃባጭ፥-ማንበብ ይቀጥሉ…
አክስቴ አክሊል
አክስቴ አክሊል በመላው ቤተሰብና ዘመድ አዝማድ ዘንድ የምትታወቅበትና የምትፈራበት አንድ ባህርይ አላት፤ ሽሙጧ! የአክስቴ አክሊል ማሽሟጠጥ ግን ዝም ብሎ ማሽሟጠጥ ብቻ አይደለም፡፡ ከባድ ጥበብ አለው፡፡ ቂቤ የምትቀባ መስላ በኩርኩም ታነድሻለቸች፤ ያሞገሰች መስላ ትሞልጭሃለች፡፡ በአንድ ሰበብ ዘመድ በተሰበሰበ ቁጥር ከእነ ረጅምማንበብ ይቀጥሉ…
ሰወርዋራ
ያገባሁት ሰው እንዴት እንዴት ብሎ ሕይወቴን ብልሽትሽት እንዳደረገው፣ በእድሜዬ ጢቢ ጢቢ እንደተጫወተ ልንገራችሁ። እንዴት የሰው ልጣጭ፣ የሰው ቁሩ እንዳደረገኝ፣ በረቀቀ ዘዴ ቀስ በቀስ ከሰው ሁሉ እንደነጠለኝ፣ እንዴት ዋጋ ቢስ ነኝ ብዬ እንዳስብ፣ብቸኛ፣ ፈሪ፣ ጠርጣራና በእሱ ላይ ብቻ ጥገኛ እንድሆን እንዳደረገኝማንበብ ይቀጥሉ…
ደረሰ
ሕይወት አዲሱ ቦይፍሬንዷ ደረሰ ቤት ናት፡፡ ግንኙነታቸው የወራት ግን በፍጥነት እየጠበቀ ያለ ነው፡፡ ለወትሮው የአማካሪነት ስራውን በአመዛኙ ከቤቱ የሚሰራው ደረሰ ዛሬ ከጓደኞቹ ጋር ቁርስ ሊበላ በጠዋት ወጥቷል፡፡ ከጠዋቱ አምስት ሰዐት ቢሆንም እስካሁን በፒጃማ ስትንጎማለል የቆየችው ሕይወት የቤት ውስጥ ቢሮው ገብታማንበብ ይቀጥሉ…
ጎስቋሎቹ
የማለዳ ጀምበር ጣሪያዬን ማሞቅ ሳትጀምር በፊት የአንድ ክፍል ቤቴ በር በእርጋታ ተንኳኳ። አባባ ናቸው፡፡ ክረምት በጋ ሳይሉ ዘወትር የሚለብሱትን አሮጌ ካፖርት ለብሰው ደጄ ቆመዋል፡፡ ካፓርቱ ከወትሮው የሰፋቸው ይመስላል፡፡ እንደዚህ ቀረብ ብዬ ባየኋቸው ቁጥር ከሲታ ሰውነትና ፊታቸው ይበልጥ ተጎሳቅሎ ይታየኛል፡፡ እንደሁልጊዜውማንበብ ይቀጥሉ…
እየዘነበ ነው
ከምሽቱ አስራ ሁለት ተኩል ገደማ ነው፡፡ሐይለኛ ዝናብ የቆርቆሮ ጣራዎችን እየደበደበ ይወርዳል፤ መንገዶች ላይ ትናንሽ ጅረቶችን ሰርቶ ይፈሳል፡፡ ከተማይቱ ለዝናብና ለቆፈኑ በጊዜ እጅ ሰጥታ እንቅስቃሴዋ ለዝቧል፡፡ሁለት ወጣት ፍቅረኛሞች በአንድ ክፍል ቤት ውስጥ ተቀምጠው ይጫወታሉ፡፡🌧🌧🌧🌧🌧🌧🌧🌧
የቱን ያስታውስ ይሆን?
ቀድማው ትነቃለች፡፡ምርጫ ስለሌላት ሆዷ እየተንቦጫቦጨ ጥላው ትሄዳለች፡፡ስራ ቦታ ስትሆን ‹‹ልጄ ልጅነቱን ሳላጣጥመው እያደገብኝ ነው›› ብላ ትብሰለሰላለች፡፡ከዳዴ ወደ እርምጃ በተሸጋገረበት ቀን ለመስክ ስራ አሶሳ ነበረች፡፡‹‹እሺ›› የምትለውን ቃል ለመጀመሪያ ጊዜ ከአንደበቱ ሲያወጣ በረጅም ስብሰባ ተጠምዳ ነበር፡፡ሞግዚቱን ‹‹ማማ›› ብሎ የጠራት ቀን ሽንት ቤትማንበብ ይቀጥሉ…
ሰሞንኛ
ስሙኝማ ! በቲቪ የኮመዲ ሾው እሚያቀርቡ ባለ መዋያዎች አሉ ፤ የአንጀራ ጉዳይ ሆኖባቸው ነው አንጂ በርግጥ አንዳንዶቹ መክሊታቸው ሌላ ነው፤ ወይ ጭራሽ መክሊት የላቸውም፤ እንደኔ እንደኔ፤ ልጆቻውን መክሊት ብለው ስም እንዲያወጡ ሊፈቀድላቸው አይገባም፤ እና ትንሽ የቸከ ጨዋታ ተረረር ያደርጉልንና በየሰክነዱማንበብ ይቀጥሉ…