( በማርች 8 ሰበብ ወዲህ የተሳበ።ሃሃሃ፣ ይሄን ሰፈር ባሰብኩት ጊዜ ለራሴ እድቃለሁ። አንዳዶች ይህ ፖስት ብልግና አለበት ይላሉ።ጭብጡ ብልግና አይደለምና አቋቋማችሁን አስተካክሉ። ከዛ ወደ ፅሁፉ…)
****
የኟ ሰፈር “እናት ፌሚኒስቶ” አመፁ። የሚገርመው ማመፃቸው አይደለም፣ እሱን ሰፈሩ ለምዶታል። ድንገት ተነስተው ሁሉም “አንሰጥም….ከባሎቻችን ጋር ወሲብ አናደርግም” አሉ። በወንዶች ሲመራ የነበረው ሰፈር አመዱ ቡን አለ። አሁን ሰው ወሲብ ያምፃል ጎበዝ? ባሎች ስራ ውለው አካላቸው ደክሞ፣ ነፍሳቸው ሻፍዶ ወደቤት ሲገቡ ጀርባ ይሰጣቸው ጀመር። እጃቸውን ሰደድ አድርገው ሲደባብሱ፣ “ ወዲያ በል እጅህን… ደክሞኛል እዛ!” በሚል ቃል እየተሸማቀቁ እጃቸውን ሰበሰቡ። ……የአመፃቸው ምክንያት ወ/ሮ አስካለች ናት። ከዚህ በፊት፣ “ቹመሳ” የሚለው ቃል “ጉረሳ” ይባል ብላ ሰፈሩን አወዛግባ ነበር። የፌሚኒስቶቹን እንቅስቃሴ እሷ ናት የምትመራው። ሰፈራችን ውስጥ ሴት የተባለች ሁሉ ከትዕዛዟ ፍንክች አትልም። የወሲብ አድማ ከመምታታቸው በፊት እንዲህ ብላቸው ነበር፣ “ወንዶች ከኛ የሚፈልጉት ነገር ምንድነው? ወሲብ ነው! ለነገሩ ወንዶች ከኛ ብቻ ሳይሆን ከሕይወትም አጥብቀው የሚፈልጉት ነገር ወሲብ ነው። ቀሚሳችሁን ገለብ አድርጋችሁ ካሳያችኋቸው፣ ጨረቃም ላይ ብትወጡ፣ እንጦሮጦስም ብትወርዱ ይከተሏችኋል። እህቶቼ….ወንዶች ላይ ያለን አንዱና ልቁ ስልጣን ያለው ጭናችን ውስጥ ነው። ይሄንን ሃብታችንን( ሃብት ወዳለችው ነገር እየጠቆመች) ዝም ብለን እያነሳን ከሰጠናቸው ዋጋችንን አይረዱም። የሲዳማዋ ንግስት ሞቲቴ ፉራ ምን እንዳደረገች ታውቃላችሁ አደል? መጀመሪያ ረዥም ና ትልቅ ጉድጓድ አስቆፈረች። ወንድ በሬዎችን በዛ በኩል፣ ላሞቹን በዚህ አስደርጋ ሳር እንዲግጡ አስደረገች። በሬዎቹ ግጠው ሲጨርሱ ወሲብ አማራቸው። ሴቶቹን አሻግረው አዩ። በመሃል ጉድጓድ አለ። ጉድጓዱ እያለ ግን በሬዎቹ ወደ ሴቶቹ ከመሄድ አላመነቱም። እያዩ ወደ ገደሉ ገብተው አለቁ። አያችሁ፣ ጭናችን ውስጥ ለመግባት ወንድ ገደል መግባት እንኳን የማይታየው በሬ ነው። እህቶቼ፣ ጭናችን ውስጥ ወንድ የሚባል ፍጡርን የሚያዝ- የሚያናዝዝ ሃይል አለ። እምዛችን ሃይላችን ነው እንጠቀምበት!!” (ሴት የባህል ባሪያ መሆን የለባትም ብለው ስለሚያምኑ፣ “ነውር” የተባሉ ቃላትን እንደልባቸው ይጠቀማሉ) ሴቶቹ በተመስጦ ይሰሟታል…. “ስለዚህ ከዛሬ በኋላ የትኛዋም ሴት ለባሏ ቀሚሷን እንዳትገልብ። መቼ ቀሚሷን መግለጥ አለባት የሚለውን በስብስባ እንወስናለን። ከዚህ ትዕዛዝ ያፈነገጠች ሴት! ያለምንም ማስጠንቀቂያ ከማህበራችን ትሰናበታለች። ምንም ዓይነት የወንድ ጥቃት ቢደርስባት ዞር ብለን አናያትም። ወንድ የሚባል ቀንበር ተጭና እያየን ከንፈር መጠጣ እንኳን አንለግሳትም። ጨርሰናል።” ሴቶቹ በከፍተኛ ጭብጨባ መስማማታቸውን ገለፁ። ግማሽ ያህሎቹ ቅልጥ ያለ ፉጨት አፏጩ። “ ሴት ልጅ እልል ማለት እንጂ ሟፏጨት የለባትም የሚለው ህግ የወንዶች ነው” ብለው ስለሚያምኑ ነው ከእልልታ ፉጨትን የሚመርጡት። ሲሰሩ ያፏጫሉ፣ ድግስ ላይ ያፋጯሉ፣ በእንዲህ አይነት ስብሰባ መደምደሚያ ላይም ያፏጯሉ።
*********
የስብሰባው ውሳኔ ተግባራዊ መሆን ጀመረ። ወንዶቹ ግራ ገባቸው። አንድ ሁለት ቀን ነው ብለው ሲያስቡ ሳምንት ሞላ። ሳምንት ሙሉ ሚስቶቻቸውን “የኔ ማር… እስቲ ወዲዚህ ዙሪ….” እያሉ በቆመ ወንድነታቸው እየተሻሹ ሊያግባቧቸው ሞከሩ። የሚያገኙት መልስ ሁሉ፣ “አንተ ስውዬ፣ ተወኝ ብዬሃለው ተወኝ! እምቢ ካልክ መሬት ነው አንጥፌ የምተኛው” የሚል ሆነ። በፍም ስሜታቸው ላይ ይህ አይነት ቀዝቃዛ መልስ እየተቸለሰባቸው ሳምንት ሆነ። ይህ ሁላ ሲሆን ሚስቶች ሳያምራቸው ቀርቶ አይደለም። በልባቸው “ ምን ቀን ይሄ የሴትነት ማህበር ውስጥ የገባሁት?!” ብለዋል። አንደበታቸው “ ሂድ ወዲያ” ይበል እንጂ፣ ባሎቻቸውን ዞሮ የማቀፍ ሙቀት ሰውነታቸውን ፈትኖታል። ያን ማድረጋቸው ከታወቀ
ግን እራሳቸውን ለወንድ እንዳስገዙ ልፍስፍሶች ይቆጠራሉ፣ ከማህበሩ ይባረራሉ፣ ሴትነታቸው ሲነካ መከታ የሚሆናቸው ያጣሉ። የትኛዋም ሴት ይህን አትፈልግም።
*****************
በሳምንቱ የሰፈራችን ወንዶች ተሰብስበው መከሩ። “የሚስቶቻችን ነገረ እንዴት ይሻላል? ኸረ መላ እንምታ??” ተባባሉ። መላ ያሉትን ሰነዘሩ። የአቶ ለገሰ ሃሳብ በሙሉ ድምፅ ፀደቀ። ሃሳቡን ተግባራዊ ለማድረግ ከዚያች ደቂቃ ጀምሮ ሁሉም ተንቀሳቀሱ። ተያይዘው ጉዞ ወደ ቡና ቤት….. በዛች ቀን ባሎች በተለመደው ሰዓት ወደ ቤታቸው አልገቡም። ሚስቶች ተጨነቁ። ቢጠብቁ….ቢጠብቁ….. ምንም! “ሰናይት ባልሽ ገባ?” ትጠይቃለች እመቤት የተባለችው ሴት! “ ኸረ አልገባም! ያንቺም አልገባም??” —- “ዮዲት፣ አስመሮም አልገባም?” “ አልገባም። ብደውልለት ስልኩ ጥሪ አይቀበልም….” ሰፈሪቷ ለረዥም ሰዓታት ባል አልባ ሆነች። ሰዓት በሄደ ቁጥር ሚስቶች ተጨነቁ። እኩለ ለሊት ሆነ። ባሎች እስካሁን ድራሻቸው የለም!
“ ማነሽ! ስመኝ?”
“ አቤት?”
“ኸረ የሆነ ነገር እናድርግ? እስቲ ስልኩን እንሞካክር? ሁሉም ባንዴ ሙልጭ ብለው የት ሄዱ ይባላል?” ሴቶቹ ከቤታቸው ወጣ ወጣ አሉ። ተሰብስበው የየባሎቻቸውን ስልክ መሞከር ያዙ። የሞከሩት ሁሉ ጥሪ አይቀበልም ሆነ መልሱ። ሁሊም አንዲት ቦታ ላይ ክብ ሰርተው ስልኩን ይቀጠቅጣሉ። ዝግ ነው። ተስፋ አይቆርጡም። የሌላዋ ባል ላይ ይሞክራሉ። ዝግ ነው…. እንደገና ይሞክራሉ….. “ ጠራ! ጠራ!!….” አለች ዮዲት በጩኸት። ሌሎቹ ሴቶች በሙሉ ግርርር ብለው ስልኳ ስር ተኮለኮሉ። “ የማን ስልክ ነው የጠራው?” “የለገሰ ነው! ቆይ ዝም በሉ…. ዝም በሉ ቆይ አንዴ ላናግረው!!” ዮዲት ተነጫነጨች።
“ሄሎ…… ሄሎ….. ለገሰ ነህ?
“ አዎ ነኝ ዮዲት! ምነው ሰፈር ሰላም አይደለም?”
“ኸረ በሰፈሩ አንድም ወንድ የለም፣ ምነው አብረውህ አይደለም እንዴ ያሉት?”
“ አብረውኝ ናቸው….. ግን አስቸግረውኛል። ዛሬን እሺ ብለው፣ ወደ ሰፈር የሚመጡልኝም አይመስለኝም”
“ እንዴ! ምነው ምን ተፈጠረ?”
“ ሁሉም ሴተኛ አዳሪ ይዘን ካላደርን ብለው አስቸግረውኛል። ሚስቶቻችን እንቢ ካሉን እንፈነዳለን ወይ ታዲያ?” ነው የሚሉት።
የስልክ ልውውጡን የሚሰሙት ቶች መንጫጫት ጀመሩ። እርስ በእርስ መደማመጥ አቃታቸው። ዮዲት ዝም በሉ እያለች ብትጮህም የሚሰማት አላገኘችም። በብዙ ጩኸት እንደምንም ዝም አሉ። “ ሄሎ….ሄሎ…. ለገሰ እየሰማኸኝ ነው?”
“ አዎ! አዎ!”
“ እባክህ! እንደምንም ብለህ ይዘሃቸው ና! እባክህ! የዛሬን ብቻ በምንም አግባብተህ ይዘህልን ና!”
“ግን በአንድ ነገር ከተስማማችሁ ነው?”
“ በምን??” …………………………. ነገራቸው። ተስማሙ። ስልኩ ተዘጋ። ሴቶቹ ወዲያውኑ አስቸኳይ ስብሰባ ወሰኑ። ምንአልባት በኢትዮጵያ ውስጥ ከእኩለ ለሊት በኋላ የተደረፈ ብቸኛው ስብሰባ ሳይሆን አይቀርም። ስብሰባው ወ/ሮ አስካለች ላይ ያነጣጠረ ነበር። ተራ እንኳን ሳይጠባበቁ የመጧላቸውን ጮክ ብለው መናገር ጀመሩ… አንዷ፡- “ ይሄውልሽ! አስካለ እንዲህ ዓይነት ዞሮ እኟኑ የሚጎዳ ዘዴ ይቅርብን!! ባልጠፋ ነገር ይሄን የሚያስከለክል ምን ተገኘ?” ሌላዋ፡- “ እኔ በበኩሌ የተከለከልኩ እንጂ የከለከልኩ አልመሰለኝም። እንዴ ስንቴ ነው ባሌ ለሊቱን ሙሉ እላዬ ላይ ሆኖ እንዲጋልበኝ ፈልጌ….
ሳልወድ እምቢ ያልኩት??” ያችኛዋ፡- “ አዎ! እኔ እራሴ ከዚህ በኋላ አንድ ቀን ባድር ከባሌ ቀድሜ በጥማት ፍግም ብዬ የምሞት ነው የሚመስለኝ! እንዴ…. ከባሌ በላይ እኮ የቆመብኝ እኔ ነበርኩ”….. በአንድነት በሳቅ አውካኩ። የወዲያኛዋ፡- “አስካለች ይሄውልሽ! የማህበሩን ሃሳብ እንወደዋለን። እንዲህ እኛኑ በሚጎዳ መልኩ ግን መሆን የለበትም። ስለዚህ ይሄኛው አመፅ አላዋጣንም፣ ከአሁን ጀምሮ ልናቆመው ይገባል….. ሌላ ጊዜ የተሻለ ሃሳብ ማሰብ ነው ያለብን” በመጨረሻ ሴት ሃሳብ ሁሉም ተስማሙ። ብዙም ሳይቆይ ባሎች መጡ። ….. ሴቶቹ ባሎቻቸውን ይዘው ወደየቤታቸው ገቡ!!
በዚህች ለሊት ሰፈራችን አልተኛችም ። ከየቤቱ የሚያቃስቱ አልጋዎች ድምፅ ይሰማሉ። “ኸረ! ገደልከኝ…..ኡውው….. እናንተ ወንዶች ሳትበ* ትንሽ ስትቆዩ ይብስባችኋል ልበል? ኡህህህህ…..” ከሌላ ቤት አንድ ባል እንዲህ ይላል፣ “ እህ….ኦህ…. አንቺ እንዲህ ይጥም ነበር እንዴ? እስቲ ምን አባሽ ሲያቀብጥሽ ይሄን ሁሉ ቀን ከለከልሽኝ” “ አኣኣዎ! የኔ ጌታ እንደእሱ ኡፍፍ….” ብዙ ማቃሰቶች። ብዙ የደስታ ውጥረት ድምፆች። የሳምንት በቀል!! እንዲሁ አደረች ሰፈራችን!
አልፋዎቿ ከፍ ዝቅ እንዳሉ… እያቃሰተች…. እየቃተተች….. ሳታንቀላፋ ነጋላት…
One Comment
ምርጥ ነዉ ግን ቡዙ አልተመቸኝም!