Tidarfelagi.com

አለመታደል ነው (ክፍል ሁለት)

እርቃኗን ለቄንጥ የተዘረረች የሚመስል አነጣጠፍ ነው ወለሉ ላይ የተነጠፈችው።…… አልፎ አልፎ የሳሙና አረፋ ሰውነቷ ላይ አለ። ከፊል ፀጉሯ ወለሉ ላይ ተበትኗል። …… ከፊሉ በትከሻዋ አልፎ ደረቷንና የግራ ጡቷን ሸፍኖታል። (ፀጉሯን ሁሌም ጠቅልላ ነው የማውቃት… … ረዥም ፀጉር እንዳላት አስቤ አላውቅም) …… የቀኝ እጇ የቀኝ ጡቷን በከፊል ከልሎ ዘንፈል ብሏል። ጡቷን አይቶ ምንም አለማለት ይከብዳል። የግራ እጇ ወለሉ ላይ…… ከጀርባዋ የተጣበቀው ሆዷ እና ከታችኛው አካሏ ጋር ሲተያይ የሌላ ቀጭን ሴት የሚመስል የሰመጠ ወገቧ በአንድ ጎኗ ወለሉን ተደግፈዋል። …… እግሮቿ በመጠኑ ገርበብ ብለው ቀኙ አጠፍ ብሎ ግራው ተዘርግቷል። …… አይቼ አለመገረም ያቃተኝ ዙሪያውን ተላጭታው ለ”እሙሙዬዋ” የቀረበችቦታ ላይ ትንሽዬ ሶስት ማዕዘን ቅርፅ የተወችለት ጭገሯ ነው። (ይህቺ ሴት ማናት? አላውቃትም ነበር ማለት ነው? ወይም የፖሊስ ልብሷን ስታወልቅ ቁሌታም ትሆናለች?)

ትንፋሿን ማረጋገጥ እንዳለብኝ እንኳን ያሰብኩት ከደቂቃዎች በኋላ ነው። …… ተሸክሜ አልጋዋ ላይ አስተኛኋት። ቤቷ ኮንዶሚኒየም ነው። …… ስቱዲዮ… ቁምሳጥኑን ከፍቼ ያገኘሁትን ልብስ አወጣሁ። …… በፎጣ ሰውነቷን አደራርቄ ሳበቃ ፓንቷን አለበስኳት… … የሴት ልጅ ፓንት ያወለቅኩበት ጊዜ እንጂ ያለበስኩበት ቀን አልከሰትልህ አለኝ። …… የሆነ ገለፃ አልባ ነገር እየተሰማኝ ልብሷን አለባበስኳት እና ወዳቆምኩት ታክሲ ተሸክሜያት ሄድኩ።…… ህፃኗ ድምፅ የሌለው ለቅሶ እያለቀሰች እየተከተለችኝ እንደሆነ ያወቅኩት ታክሲ ውስጥ ከገባሁ በኋላ ነው። ግራ ተጋባሁ። …… ይዣት ልሂድ? ህፃን ናት እንዴት ትቻት እሄዳለሁ? …… የቤቱን በር ዘግቼው ታክሲው ውስጥ አስገብቻት አብረን መጓዝ ጀመርን። …… ስምሪት እግሮቼ ላይ ናት።

“ስምሪት ምንሽ ናት?” ጠየቅኩ

በአትኩሮት በጥያቄ አየችኝ። ፊቷ ተቆጣ።

“ስምረት ምንሽ ናት?” አስተካክዬ ደገምኩ

አልመለሰችልኝም። …… ስምሪት ስለራሷ ነግራኝ የምታውቀው ነገር ካለ ማሰብ ጀመርኩ። …… መርማሪ ፖሊስ መሆን ህልሟ መሆኑን ብቻ… … አስቤው አላውቅም። ጠይቂያት አላውቅም። …… ስለእኔ የማልነግራት የለም። ……
………እንዴት ሆንክ? ያ ነገር እንዴት ሆነልህ? ያሁኗ ቺክህ እንዴት ናት?ምን ሆነህ ነው ፊትህ ልክ አይደለም? አይንህ ቀልቷል ማታ አልተኛህም እንዴ?……… የመሳሰሉ ጥያቄዎች ትጠይቀኛለች። …… የጠየቀችን እመልስላታለሁ… … አንዲትም ቀን አንቺስ? ብያት አላውቅም። …… ፊቷ ጠቆረ? ቀላ? አይቼው አላውቅም።

“እናቴ ናት” አለችኝ ህፃኗ ቆይታ… … ልጅ እንዳላት ስታወራ ሰምቼ አላውቅም። …… እንዴት አትነግረኝም? …… ለምን ትነግረኛለች? መች እንድትነግረኝ ጠየቅኳት? ምናልባት ልትነገረኝ አስባ ታውቅ ይሆናል። …… እኔ ግድ እንደሌለኝ ታውቃለች። …… ጆሮውን እንኳን ሊያውሳት ቁብ ላልሰጠው ሰው ለምን ትነግረኛለች? …… እሷ ታዲያ ለምን ትሰማኛለች? ለምን ትጠይቀኛለች? ለምን ውሎ አዳሬ ያሳስባታል?

“እናቴ ናት” ደገመችልኝ ህፃኗ ትኩረት የሰጠኋት አልመሰላትም

“ስምሽ ማነው?” አልኳት

“አርሴማ” ……
………
………
ስምሪት ነቃች…… አይኖቿ ስትገልጣቸው ቀይ ወጥ መስለዋል። ……

“ወደ ቤት መልሰኝ ምንም አልሆንም አንዳንዴ እንዲህ ያደርገኛል” አለችኝ የሆነውን ከነገርኳት በኋላ

“አንዳንዴ? መታየት አለብሻ?”

“‘እንቅልፍ ተኚ፣ እረፍት አድርጊ፣ ፈሳሽ ውሰጂ… ‘ ነው የሚሉኝ” አለች እየተነቃቃች። …… ብዙ ተጨቃጨቅን። …… በእንቢታዋ ፀናች። …… ወደ ቤት ተመለስን። …… ምንም የማውራት ፍላጎት አልነበረኝም። …… እሷም እቤቷ መቀመጤ ምቾት የሰጣት አይመስለኝም። አርሴማ እናቷ ጉያ ተሸጉጣ ቁልጭ ቁልጭ እያለች አንዴ እኔን አንዴ እናቷን ታያለች።

“ደህና ትሆኛለሽ? ልሂድ?” አልኳት

“አዎን ደህና እሆናለሁ ሂድ!” አለችኝ የመገላገል አይነት ስሜት ባለው ድምፅ

ከቤቷ ወጥቼ በእግሬ ብዙ መንገድ ተጓዝኩ። …… ራሴን ፣እሷን ፣ልጇን…… እየዛቆሉ የሚኖሩትን ይህ በስባሳ ኑሮ… እያሰብኩ ብዙ ተጓዝኩ። …… የማላወቀው ስሜት ረበሸኝ። …… ግድ የለኝም ፣ ረስቼዋለሁ፣ ተሻግሬዋለሁ…… ያልኩት ትላንት ልቤን እየጨመደደ ሲፈነቅለኝ ይታወቀኛል።…… ደጋግሜ አጨስኩ። … ራስ ምታት ጀመረኝ……

ያለፈው በሚመጣው ላይ ምንም ጥቀርሻ መተው የለበትም ብዬ ያለፈውን ከኔ አርቄ የጣልኩ ይመስለኝ ነበር። …… ምናልባት አይቻል ይሆናል። ዛሬ ከተከሰተው ክስተት ምኑ ከኔጋ እንደሚያያዝ አላውቅም። …… የሰው ልጅ ሁሉ ከትላንቱ ተጋብቶ ሳይሆን አይቀርም የሚኖረው … … ሀበሻ ሙዚቃው ውስጥ እንኳን ትዝታ ስልት መኖሩ ከትናንት መፋታት አለመፈለጉ ወይ አለመቻሉ ይሆናል። …

ስልኬ ጮኸ… … ስምሪት ናት። ደነገጥኩ።

“ወዬ ምነው? አመመሽ እንዴ?”

“ኸረ ደህና ነኝ። ቅድም ስላልተረጋጋሁ አመሰግናለሁ እንኳን ሳልልህ…”

“አሁን አልሺኝ!”

 

አለመታደል ነው (ክፍል ሦስተ)

One Comment

  • መሀመድ commented on July 5, 2017 Reply

    ጥሩነዉ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *