ግርማዊነታቸው ዛሬ በረመዳን የመጀመሪያ ቀን የሳውዲ አቻቸውን (“አቻ” ሲባል ያው ሳውዲ በንጉስ የምትመራ ከመሆኗ አንጻር በቀጥታ ይወሰድልኝ) ሊያነጋግሩ በሳውዲ አረቢያ ተገኝተዋል።ትላንት በቲቪ እንዳየነው ንጉሰነገስቱ በግዛታቸው የሚያገለግሉ የተለያዩ ደጃዝማችና ራሶቻቸውን ሰብስብው ስለአገር አስተዳደር ሲያወጉ ሳት ብሏቸው ድሮ እቴጌ (እናታቸው) “የኢትዮጲያ 7ኛው ንጉስ አንተ ትሆናለህ “ብላኝ ነበር በማለታቸው…”ያው እንኩ ስጋዬን ቦጫጭቁት “ብለው አቀብለውናል…አንዲ ማኛ በዚህ ቀላል ጉዳይ ላይ ከጉዳዩ ቅለት የተነሳ (አንቱ የተባሉ ተካዎችና ጉምቱ ጭራቆይዎች እራሱ በተሳቀቁበት ) ግርማዊነታቸውን ለመፎተት የምር ደብሯታል። በዛ ላይም በዚህ አይነት ለከት የለሽ ንግግር ከቀጠሉ (በተለይ የተከበሩ አቶ ለማ ከሁሉም በበለጠ ያፈሩባቸው ይመስለኛል) የትይሄዱብኛልይሄዱብኛል በማለትም ጭምር ለዛሬ ብዙም አልልም…ግን …የፈለገ ቢሆን የእህልና የወሬ ጡር አለው በማለት ትንሽ ላስ ላስ እንዳደርጋቸው ፍቀዱልኝ ..ሌባ ላመሉ….።
ያው ግርማዊነታቸው እንዳሉት በ”ትንቢቱ” እስከዛሬ ድረስ በጥልቅ ያምኑበታል….ወገን ይህ አይነት እምነት ግን እንደቀልድ መታየት ያለበት አይመስለኝም!…ዚስ ኢዝ ሃው ዲክታተርስ አር ክርኤትድ….አብይ ሲሪየስሊ ጉዳዩን ይወስደዋል ብዬ ባላስብም ሃሳቡ ግን ገና በእንጭጩ ሊቀጭ የሚገባው ከዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ ያፈነገጠ አፍሪካ ውስጥ ከዚህ ቀደም እነ ቦካሳ እና ኢዲአሚን ብለውት አለም የሳቀባቸው የቀሽም ቀሽም ሃሳብ ነው…በእርግጥ አሁንም ቢሆን ጠሚው እንደ እነ ቦካሳ ጨክነው ሰርፕራይዝ የሆነ “በአለ ንግስ” አዘጋጅተው ይነግሳሉ ብየ ባላሳብም(ቢ/ኮ.. ሂ ኢዝ ናት ክሬዚ ኤንድ ሚ ኒዘር)…….መረሳት የሌለበት እንደዚህ አይነት “ንግርቶች” እና “ትንቢቶች” ኋላ ላይ “ይህ ነገር ይሳካ ዘንድ ቶሎ ምቀኛህን አስወግድ ..ምናምን” በሚሉ መሰሪ ሃሳቦች ተደጋግፈው ምክንያታዊ የሚባሉ ሰዎችን እንኳን እልም ወዳለ የኢራሽናልነት ጥግ እንደሚወስዱ ነው። …ምናልባት “አንተም ደግሞ ዝም ብለህ አታካብድ!” ትሉ ይሆናል..ምናልባትም በቦታው የነበሩት እነ ነጋድራስ ሲራጅ ፈጌሳ …አፈ ንጉስ አህመድ ሽዴ….በጅሮንድ አብርሃም ተጠምቀ..ፊትአውራሪ ሞቱማ መቃሳ….እልፍኝ አስከልካይ ዛድግ አብርሃ….ጉዳዩን በቀልድ አይተውት ይሆናል…ግን ለእኔ ይህ አይነት ሃሳብ ለቀልድም እንኳን ቢሆን አይጥመኝም ጠቅላዩም ቢሆኑ በቶሎ እርግፍ አድርገው ሊተውት የሚገባ ጉዳይ ነው።
ግርማዊነቶ ይህ የዋህ ህዝብ እኮ ነገ ለምርጫ ተቃዋሚዎች ሲጠሩት “አረ ተውኝ እናንተዬ !….ሰውየው ንግርት አላቸው እየተባለ የምን ምርጫ ነው የምታደክሙኝ!?” ይልም ይሆናል..ግን ዶክተርዬ አሁን ማይሙት ከሚመሩት ድሃ ህዝብ የበዛው እጅ መሃይም መሆኑን አጥተውት ነው በብሄራዊ ጣቢያ “ንግርት ያለኝ ሰባተኛ ንጉስ ነኝ!” ብለው የሚናገሩት? ! …አቤት ይሄ ወሬ በአደጉት አገራት ተብሎ ቢሆን ኖሮ?!….በርግጥ ፍላጎቱ ኖሮት ለስኬቱ ተግተው ሰርተው ይሆናል (ዋት ኤቨር ዛት ኩድ ቢ ..አስ ዩ አር ኦንሊ ሂር ዊዝ ዘ ሄልፕ ኦፍ ሲክዌንስስ ኦፍ ኤክስትራ ኦርዲነሪ ኢቨንትስ )(ያው እንደሳቸው ኢንግሊፋ ላብዛ ብየ ነው) ….ከዛም በላይ ይህንን ነገርም ለተለያዩ ሰዎች ቀደም አድርገው ተናገረውም ይሆናል (የጠሯቸው ምስክሮች ግን ሁለቱም የማይናገሩ መሆናቸው ፈገግ አስብሎኛል(ያው አንዱ መለስ ነው “መለስንም ነግሬአዋለሁ..በመሃላችን አንድ ሰው ብቻ ነው ያለው ብዬ….” ብለዋል ።መለስ እውነት ነው ብለውሃል!?…..መልስ የለም። ሌላኛው ሳሞራ ነው..ቂቂቂቀ ….እስቲ ክፉ አታናግሩኝ )..ከሁሉም የገረመኝ ግን እንዴት መሌ ዝም አሎት እና የት የመቀላለጃ ግዜ አግኝተው ነገሩት !? የሚለው ብቻ ነው!…በአጭሩ ሁለተኛ እንዳይለመዶት!..እስቲ ተካዎችም ንገሯቸው።በዚህ አይንት ንግግራቸው የሚስቁላቸው ጠላቶቻችሁ ኮካዎች ብቻ ናቸው።
በመጨረሻም ባለጌ አትበሉኝና እኔም ቢሆን አያቴ ገና በአስር አመቴ ወደፊት “ብሎገር” ትሆናለህ ብላኝ እንደነበር መግለጽ እፈልጋ፤ሁ። …ያው ያኔ ብሎገር የሚባል ነገር ባለመኖሩ “ባላገር ትሆናለህ” ያለችኝ መስሎኝ..አዲስአበባ ስገባ ትንቢቷን አከሸፍኩ ብዬ በጣም ነበር የሳኩባት…..(ጠሚያችን ንጉስ ትሆናለህ ሲባሉ ስርአቱ በሌለበት “እንዴት?” ያላሉት ለምን ይሆን !?….በዛ ላይስ ሰባተኛው ንጉስ ትሆናለህ ሲባሉ በኢሃዲግ ምሁራን ከ150 እስከ 3 ሺ አመት እድሜ ባላት አገር(ሎል) እኔ 7ኛ የምሆነው ከማን ጀምሮ ተቆጥሮ ነው ለምን አላሉም?…ወይስ እናትዬው ትንግሳለህ ያሏቸው ስዋዚላንድ ነው …?!
ለማንኛውም ነገ በሲሪየስ ፖስት እንገናኛለን።
እስከዛው
ይመቻችሁ
One Comment
loved it