Tidarfelagi.com

“ደግ አይበረክትም”

እስከ:ማዕዜኑ
..እስከ፡ማዕዜኑ
አነብር:ውስተ:ልብየ:ትካዘ
ዐሊውየ:ሕገ:ወትዕዛዘ:
ማርያም:ኩነኒ:መናዝዘ።

አቤል: በፀጋ : ርቆ ፣
በየዋህነት:ከመጠቀበት ፣
ቃዬል:በንፍገት:ከብሮ ፣
መቀመቅ:ከወረደበት፣

የዕጓለ መሕያው: ታሪክ ፣
ሲጀመር : የጠቆረበት .
እንውረድ:ብሎት:ወንድሙን ፣
እስትንፋሱን:የነጠቀበት ፣
ኃዘና ፣ ስምዒ:ወብካያ ፣
ለሃገሪትነ:ኢትዮጵያ ።
የሞት:ታሪክ:ሊዘከር
በአዝማናት:ማሀል:ሊነገር

የመጀመሪያው:መልአክ ፣
ታሪኩን:ሲፅፈው:እንደዚህ:ነበር። ….

ክልዔቱ: አኃው: መንገደ:ቀላይ :ወረዱ፣
እኒህ:ሁለት:ወንድሞች:ወደ:አዘቅት:የሄዱ፣
አንደኛው:ሟች:ሊሆን:ገዳይ:ሊሆን:አንዱ፣
አሃዱ:ተመይጠ፣ ወኢተመይጠ አሃዱ ፣

አንደኛው ሲመለስ
ሁለተኛው እዚያው የቀረ፣
ውረድ እንውረድ ያለው
ወንድሙ ገድሎት ነበረ።

ከዚህ የቀን፡ጎደሎ፡ነው ፣
ከዚህ፡ክህደት፡በኋላ፣
ከተራራው፡አናትና፡
ከግርጌ፡በቆመው፡ማሀል፡
መተማመኑ፡የላላ።

የአዳም፡የልጅ፡ልጅ፡ሁሉ
፡ምን፡ቢጀግን፡ምን፡ ቢያቅራራ፣
ምን፡ደግ፡ንግርት፡ቢያስነግር ፣
ምን፡ በማዕረግ፡ቢጠራ ፣
ይገሉኝ፡ይሆን፡እያለ፡ነው ፣
ውረድ፡ሲሉት፡ የሚፈራ ።
እናም፡መውረድ፡ሞቱ፡ነው፡
አንዴ፡ደርቡን፡ ከወጣ ፣
ውረድ፡ሲባል፡በመውረዱ፡ነው ፣
ወንድሙ፡ ሕይወቱን፡ያጣ።

በርግጥ፡ለምን፡ይወርዳል፡
መውረድስ፡ማንን፡ ጠቀመ ?
የወረደውን፡መግደሉ፡ለዘላለሙ፡ካልቆመ !
———-

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *