ልድገመውና …ከአንድ ክፍለዘመን በፊት በፈረንጆቹ 1936 አንዲት ማርጋሬት ሜሸል የተባለች አሜሪካዊት ጋዜጠኛ እግሯን ወለም ብሏት አልጋ ላይ ዋለች …ታዲያ ስብራቷን እያዳመጠች ከማለቃቀስ ይልቅ በደጉ ጊዜ አእምሮዋ ውስጥ የተጠራቀመውን የአገሯን የእርስ በርስ ጦርነት ታሪክ መፃፍ ጀመረች … እንዲሁ በደረቁ ሳይሆን እንደኛው ፍቅር እስከመቃብር ዳር ዳሩን በፍቅር ታሪክ ዘምዝማ …. በዛ መፅሃፍ የአሜሪካ የእርስ በእርስ ጦርነት ምን ያህል የአገቱን ኢኮኖሚ እንዳመሸከው …መኳንትና መሳፍንቱ እንኳን ይደርቡት ካባ ይጎትቱት ቀሚስ … ለመቀመጫቸውም መሸፈኛ እራፊ ማግኘት መከራ እንደሆነባቸው የጦርነት አስከፊን ገፅታ ቁልጭ አድርጋ አሳይታበታለች ….…(የሰው አገር ጋዜጠኛ ተሰብሮ እንኳን በጥበብ አገር ይጠግናል😀)
ቤተሰብ ብትንትኑ ሲወጣ የተፋቀሩ ሲለያዩ ሰዎች ሞራላቸው ሙቶ እንዲሁ የቁም ሬሳ ሁነው ሲንገላወዱ በዛም መዓት ውስጥ ቢሆን ፍቅርና ታማኝነት ግን ህያው ሁነው እንደዘለቁ ደራሲዋ አስር ዓመት በፈጀ በዚህ መፅሃፏ አሳይታበታለች “Gone With The Wind” ይባላል መፅሀፉ ! ለአገራችን አንባቢም አዲስ አይደለም ! ነብይ መኮነን በእስር ቤት ሁኖ ተርጉሞ አስነብቦናል ! ከነብይ መተርጎም በላይ አተረጓጓሙ ደግሞ ራሱ የራሱ ገድል ነበረው !! ታዲያ ነብይ ትርጉሙን “ነገም ሌላ ቀን ነው” አለው !! የአተረጓጎሙን ውበት ያው ነብይ ነውና አጀብ ነው ብለን እንለፍ!
ይሄን መፅሃፍ መሰረት አድርጎ 1939 ላይ በዚሁ እርእስ ፊልም ተሰራ… ፊልሙ ጥቃቅኑን ሽልማቶች ተውትና ታላቁን የኦስካር ሽልማት ጭምር ማሸነፍ የቻለ ፊል ነው! ታዲያ ከዓመት በፊት ይሄ ፊልም በማንኛውም ፊልም ሻጭና አከራይ ካምፖኒዎች እንዳይታይ ታግዷል … ለምን ? እሱን “ዛሬም ሌላ ቀን ነው” በሚል ርዕስ የፃፍኩትን ፅሁፍ ፈልጋችሁ ሙሉውን እንብቡ ለአሁኑ …ይሄ ድንቅ በመላው አለም በሽያጭም በኪናዊ ከፍታውም ሰማይ የነካ መፅሐፍ ከ32 ዓመት በኋላ እንደገና ታትሞ ገበያ ላይውሏል! Ephrem Jemal Abdu እንደገና ስላሳተምከው እጅ ነስተናል🙏ትላንታችንን መልሶ እንደማሳተም ነው ጓድ!