የሽግግር መንግሥቱ ትውስታ በጥቂቱ (1983-1987)

ትናንት በለጠፍኩት አንድ ጽሑፍ ግንቦት 19/1983 በለንደን ስለተከፈተው ኮንፈረንስ ተናግሬ ነበር። እስቲ አሁን ደግሞ የለንደን ኮንፈረንስ ቀጥተኛ ውጤት ስለነበረው የያኔው የኢትዮጵያ የሽግግር መንግሥት እናውጋ። ከግንቦት 19-20/1983 በተካሄደው የለንደን ኮንፈረንስ ላይ ዋነኛ ተሳታፊ የነበሩት አዲስ አበባን ጨምሮ አብዛኛውን የሀገሪቱን ክፍል የተቆጣጠረውማንበብ ይቀጥሉ…

EPDA – በመጨረሻው ሰዓት የተገኘ አደገኛ ድርጅት

የደርግ መንግሥትን ለመደምሰስ ሲታገሉ የነበሩ ከደርዘን በላይ የሚሆኑ ድርጅቶች ነበሩ። ኢህአዴግ፣ ኦነግ እና ኢህአፓን የመሳሰሉት የታጠቀ ሰራዊት አስከትተው ሲዋጉ ነበር። አንዳንዶቹ ግን ሰራዊት ሳይኖራቸው በደርግ መንግሥት ላይ አደገኛ ፕሮፓጋንዳዎችንና ስውር የውስጥ ጥቃቶችን ሲያካሂዱ ነበር። ከነዚህም ውስጥ በብዙዎች ዘንድ ልዩ ትዝታንማንበብ ይቀጥሉ…

የሼኽ ሙኽታር ምክር

በገለምሶ ዋናው መስጂድ ከ60 ዓመታት በላይ በኢማምነት ስላገለገሉት ሼኽ ሙኽታር ዐሊዪ ብዙ ጊዜ ጽፌአለሁ። ለዛሬ ደግሞ እሳቸው ያጫወቱን አንድ ግሩም ተረት ላካፍላችሁ። ተረቱ የሰው ልጅ ልኩን አውቆ እንዲኖር እና አላህ በሰጠው ኒዕማ አመሰጋኝ እንዲሆን የሚያስተምር ነው። በአንዲት መንደር የሚኖር አንድማንበብ ይቀጥሉ…

ቅዱስ ቁርኣን በአማርኛ ሲተረጎም (1961)

ቅዱስ ቁርኣን በአማርኛ እንዲተረጎም ትዕዛዝ ያስተላለፉት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሤ ነበሩ። ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሤ ትእዛዙን ያስተላለፉት ሐምሌ 18/1958 በተጻፈ ደብዳቤ ነበር። የንጉሡን ደብዳቤ በመንተራሰስ ስራው እንዲጀመር ያደረጉት ደግሞ በወቅቱ የትምህርት ሚኒስትር የነበሩት ዶ/ር ምናሴ ሃይሌ ናቸው። ዶ/ር ምናሴ በተርጓሚነት የመረጡት ከአል-አዝሃርማንበብ ይቀጥሉ…

የየመኒዎች ጨዋታ

በዚህ ወቅት የቅርብ ጓደኛዬ የመኒው ኮሎኔል ሙሐመድ አል ሐይደሪ ነው። ረመዳንን በአብዛኛው አንድ ቤት ነበር ያሳለፍነው። አሁንም አብረን ነው የምንውለው። በተለይ ከሰዓት አብረን ስንጫወት ነው የምናሳልፈው። በርካታ ቁም ነገሮችንም ከእርሱ እየተማርኩ ነው።  —- ጦርነትን ሸሽቶ ከሀገሩ የወጣው ሙሐመድ አል ሐይደሪማንበብ ይቀጥሉ…

ዐምር ኢብን ኣስ እና “ፉስጣጥ” (ክፍል ሁለት)

የጥንት ግብጻዊያን አንድ ልማድ ነበራቸው። በየዓመቱ ቆንጆ ልጃገረድ ይመርጡና ለአባይ ወንዝ (ኒል/ናይል) ይሰውለት ነበረ። እነዚያ ግብጻዊያን ናይል በየዓመቱ መስዋዕቱን ካላገኘ ውሃውን ይቋጥርብናል የሚል እምነት ነበራቸው። አምር ኢብን ኣስ ሀገሪቱን በያዘ በጥቂት ወራት ውስጥም ግብጻዊያኑ ለወንዙ መስዋእቱን ለማቅረብ እንደሚፈልጉ ነገሩት። አምርማንበብ ይቀጥሉ…

አምር ኢብን ኣስ እና “ፉስጣጥ”

በፎቶው ላይ የምትመለከቱት ለአፍሪቃ አህጉር የመጀመሪያ የሆነውን መስጊድ ነው። ይህ መስጊድ የተሰራው በ641 ሲሆን የሚገኘውም በግብፅ መዲና ካይሮ ውስጥ ነው። መስጊዱ የሚጠራው በመስራቹ በ“አምር ኢብን ኣስ” ስም ነው። ይሁንና አምር እና ጓዶቹ መስጊዱን የሰሩት በአል-ፉስጣጥ እንጂ በካይሮ አልነበረም። ታዲያ መስጊዱንማንበብ ይቀጥሉ…

ክርስቲያኗ ፍቅረኛዬ ናፈቀችኝ!

ረመዳን ሲመጣ ከማስታውሳቸው ሰዎች አንዷ ናት። በእድሜዋ ከኔ በሁለት ዓመት ታንሳለች። ከ1996-2004 በነበረው ዘመን የኔ ምርጥ ጓደኛ እርሷ ነበረች። ሌላ ሴት የመጋበዝ ባህል አልነበረኝም። እርሷን ግን ከፒያሳው ኡመር ኻያም ጀምሮ እስከ ውድ ሬስቶራንቶች ድረስ እየወሰድኳት እጋብዛት ነበር። እርሷም አጸፋዋን በመክፈሉማንበብ ይቀጥሉ…

“ለይለቱል በድር” እና “በርቲ በርቲ” በሀረር

ረመዳንን የሚጾም ሰው ስለ“ለይለቱል ቀድር” ማንነት በሚገባ ያውቃል ብዬ እገምታለሁ። “ለይቱል በድር”ን ግን ብዙዎቻችሁ ላታውቁት ትችላላችሁ። ስለዚህ በዛሬው የረመዳን ወጋችን “ሀረር ጌይ” በተሰኘው መጽሐፌ ስለ “ለይለቱል በድር” የጻፍኩትን አጋራችኋሁ። ***** “በድሪ” እና “በድሪያ” እኔ በተወለድኩበት አካባቢ በጣም ከሚታወቁት ስሞች መካከልማንበብ ይቀጥሉ…

ፍቅር ሁሉንም ያሸንፋል እብሪት ግን ለውድቀት ይዳርጋል

ጎሽ! ጎሽ! እሰይ —- ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድን በየእለቱ እየወደድኩት ነው። ለፕሬዚዳንት ኢሳያስ ያለኝ አድናቆትም እየናረብኝ ነው። ታዲያ አቶ ኢሳያስ ዛሬ ያደረገውን አስገራሚ ነገር ልብ ብላችኋልን? ፊርማውን ሲፈርም እኮ የባድመ ጉዳይ ከቁም ነገር ተቆጥሮ አልተነሳም። ድሮስ? ድሮማ “ባድመን ካላስረከባችሁን ድርድርማንበብ ይቀጥሉ…