ክፍል አራት፡ ትግሉን ለዓለም ማኅበረሰብ ማስተዋወቅ በጆርጅ ሐበሽ የሚመራው PFLP እስራኤልን በትጥቅ ትግል ብቻ ለመፋለም የወሰነ ድርጅት ነበር። በመሆኑም በወቅቱ ከስድስት መቶ ያልበለጡ ተዋጊዎቹን በማሰማራት በፍልስጥኤም ግዛቶች ወታደራዊ እንቅስቃሴዎችን ያደርግ ጀመር። በሊባኖስ፣ በዮርዳኖስ፣ በሶሪያ እና በሌሎች የዐረብ ሀገራት የተበተኑት ፍልስጥኤማዊያንማንበብ ይቀጥሉ…
ሶማሊ እና ኦሮሞ ወንድማማቾች ናቸው!
ታሪካችን የመረዳዳት እንጂ የግጭት አልነበረም። ታሪካችን የአብሮ መኖር እንጂ የመበላላት አልነበረም። ታሪካችን የመፋቀር እንጂ የመናቆር አልነበረም። እጅግ በሚገርም ሁኔታ አንዳችን ለሌላው መብትና ጥቅም መከበር ስንል አብረን ተዋግተናል። ህይወታችንን ሰውተናል። ለምሳሌ ታዋቂ የኦሮሞ አርበኞች የሆኑት ኤሌሞ ቂልጡ (ሐሰን ኢብራሂም)፣ እና ሁንዴማንበብ ይቀጥሉ…
የሁለት ዶክተሮች ወግ (ክፍል ሶስት)
ክፍል ሶስት፡ የአዲስ ግንባር ምሥረታ ጆርጅ ሐበሽ እና ዋዲ ሀዳድ ሶሪያን እንደ ዋነኛ ቤዝ በመጠቀም ትግላቸውን በማካሄድ ላይ ሳሉ በ1962 የባዝ ፓርቲ አፍቃሪ የሆኑ መኮንኖች በሳላህ አል-ቢጣር መሪነት የሀገሪቱን መንግሥት ገለበጡ። ይህም የሶሪያ መንግስት ይከተለው በነበረው ፖሊሲ ላይ ትልቅ ለውጥማንበብ ይቀጥሉ…
የሁለት ዶክተሮች ወግ (ክፍል ሁለት)
ቀዳሚው የትግል ምዕራፍ ዶ/ር ጆርጅ ሐበሽ እና ዶ/ር ዋዲ ሀዳድ በቀዳሚዎቹ ዓመታት አዲሱን ድርጅታቸውን በማስተዋወቅና አባላትን በመመልመል ላይ ነበር ያተኮሩት። በዚህ መሠረት በተለያዩ ሀገራት ወደሚገኙት የፍልስጥኤም ኮሚኒቲዎች ወኪሎቻቸውን እየላኩ የፖለቲካ ፕሮግራማቸውን አስተዋውቀዋል። አባላትን እየመለመሉ በድርጅቱ ህዋሳት ስር አዋቅረዋል። ከተለያዩ መንግሥታትማንበብ ይቀጥሉ…
የሁለት ዶክተሮች ወግ
ክፍል አንድ፡ የትግል ጅማሮ ይህ ተከታታይ ትረካ የሁለት ግለሰቦችን የትግል ጉዞ በአጭሩ ለማስተዋወቅ ታስቦ የተሰናዳ ነው። እነዚህ ግለሰቦች ፍልስጥኤማዊያን ናቸው። ሁለቱም ክርስቲያን ዐረቦች ነበሩ። ሁለቱም ከሀብታም ቤተሰቦች ነበር የተገኙት። ሁለቱም በተመሳሳይ ዩኒቨርሲቲ የህክምና ሳይንስ አጥንተው በዶክትሬት ዲግሪ ተመርቀዋል። ሁለቱም በዩኒቨርሲቲውማንበብ ይቀጥሉ…
የመውሊድ ትዝታዎቼ
የመውሊድ በዓልን እያከበርነው ነው። በዚህ ጽሑፌ ስለበዓሉ አከባበር የማወጋችሁ ነገር የለም። ከዚያ ይልቅ ያኔ በልጅ ወኔአችን ከሰራናቸው “አድቬንቸሮች” አንዳንዶቹን አጋራችኋለሁ። ***** በህዳር ወር 1980 ነው። በወቅቱ እኔ (አፈንዲ)፣ መሐመድ አብደላ (ማመኔ)፣ ጆሀር ሀጂ ዩሱፍ (ጀዌ)፣ አድናን ዑመሬ (አግሽ)፣ እና አሕመዶማንበብ ይቀጥሉ…
“ሌ ሚዝረብል” እና “ዣንቫልዣ”
=== እንደ መግቢያ === እነሆ የቪክቶር ሁጎ ታላቅ ስራ የሆነውን “Les Misérables”ን ልንዘክረው ነው። ይህ ድርሰት የፈረንሳይ ምድር ካበቀለቻቸው የፈጠራ ስራዎች መካከል በጣም ዝነኛው ነው። መጽሐፉ በዓለም ዙሪያ የሚታወቀው “Les Miserables” (ሌ ሚዝረብል) በተሰኘው የፈረንሳይኛው ርዕስ ነው። በበርካታ ቋንቋዎች ሲተረጎምምማንበብ ይቀጥሉ…
ጋሽ ታደሰ ኃይሌ- የአማራ ህዝብ ደግነት ምሳሌ
“ጂንኒ ጀቡቲ” የሚለውን አባባል ለመጀመሪያ ጊዜ የሰማሁበትን ሁኔታና ጊዜ ከዚህ በፊት አውግቼአችሁ ነበር። እነሆ ዛሬም መድገሙ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል። የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) የገለምሶ ከተማን የተቆጣጠረው ግንቦት 22/1983 ነበር። ኦነጎች ለሶስት ቀናት አካባቢውን ሲያረጋጉ ከቆዩ በኋላ እሁድ ግንቦት 25/1983 በፖለቲካማንበብ ይቀጥሉ…
ኦነግና ኢህአዴግ በአንድ ቀን ጦርነት (ክፍል አምስት)
(እውነተኛ ታሪክ) ያ የኦነግ ወታደር አስደንግጦኝ “ወደቤት” ስገባ ትቶኝ የነበረው ፍርሃት እንደገና ተቀሰቀሰብኝ። ልቤም እንደ ቃልቻ ድቤ “ድው ድው.. ድው… ድው….” ማለት ጀመረ። “ምን ዓይነት ቀን ነው?” አልኩ ለራሴ። የአክስቴ ልጆችም እንደኔው ተሸብረዋል። “ወዴት መሄድ ይሻላል?” በማለት መነጋገር ስንጀምር “ሙበጀል”ማንበብ ይቀጥሉ…
ኦነግና ኢህአዴግ በአንድ ቀን ጦርነት (ክፍል አራት)
(እውነተኛ ታሪክ) ረቡዕ ሰኔ 17/1984…. ከጧቱ 12፡30 ገደማ አክስቴ ከሁላችንም ቀድማ ነው ከእንቅልፏ የተነሳችው። እኔና ልጆቿ ከመኝታችን በመነሳት ላይ በነበርንበት ጊዜ ደግሞ እርሷ ወደ ሰፈር ሄዳ ወሬ ቃርማ መመለሷ ነው። “ምን ተፈጠረ?” አልናት። “ኢህአዴጎች ሳይጠበቁ በኦነግ ጦር ላይ ጥቃት ከፍተዋል?”ማንበብ ይቀጥሉ…