ኤሊቱ ብዙ ነው መዓቱ

ኤሊቱ ኤሊቱ ብዙ ነው መዓቱ – እኔ ጃዋር መሀመድን ጨምሮ ቀሪዎቹም ኤሊቶች የኦሮሞን ሕዝብ ይጠሉታል የሚል ድምዳሜ ላይ ከደረስኩ ቆይቻለሁ። የሚገርመው እንደሚጠሉት አያውቁም ወይም መቀበል አይፈልጉም። የራስህን ሕዝብ ካልጠላኧው በቀር፣ በድህነት መዶቀሱን እንደሌለ እውነታ እየከለልክ እንዴት የብሔር ጉዳይ ላይ ብቻማንበብ ይቀጥሉ…

ማፍረስ እንደ ባህል

(የመትከል ባህል የሌለው ሕዝብ እንትከል ስትለው አወዳደቁን እየተለመ ይስቃል) — ስሜነህ አያለሁ እና ቢኒያም ሲሳይ የፃፉት፣ «what is in a term? A historical and linguistic examination of the revolutionary terminology:yiwdem, “let it be demolished, down with,” 1974-1977» የሚል ወረቀት አለ።ማንበብ ይቀጥሉ…

የብሄር ፖለቲካ

አማራ የለም የሚለው ክርክር የሚያሳቅ ነገር አለው። ሌላውን ማንነት ተፈጥሯዊ የማድረግ የዋህ ተግባር ነው። የትኛውም ሕብረት ሰው ሰራሽ ነው። እንኳን አንድ ብሔር ሀገር እራሱ ከተለያዩ ምናልባቶች ውስጥ በአንዱ ምናልባት የተገነባ አንድ አጋጣሚያዊ ማንነት ነው። አዎ አማራ የሚባል ማንነት የለም። በዛውማንበብ ይቀጥሉ…

አያና ነጋ (የእስክንድር ነጋ ወንድም አይደለም ☺) 

ሰው ራሱን የተፈጥሮ ማእከል አድርጎ ይመለከታል፤ለተንኮል። ያልተመቸውን እየቀጠፈ፣ የተመቸውን እያገዘፈ ለመኖር። ለሰው ሲባል፣በሌሎች ፍጡራን የሚደረገው ብዙ ነው። ይሄን የመሰለው በዓል አንዱ መስኮት ነው። ዓመት በዓል ብዙ እንስሳት የሚገደሉበት ሰዋዊ ስነስርዓት ነው። ሰው ግን እንስሳትን ዝም ብሎ አይገልም። መጀመሪያ ህይወት እንጂማንበብ ይቀጥሉ…

የዘውግ ፖለቲካ እንደ ሀገር?

ወደ 25 ሀገሮች ፌደራሊዝምን ይከተላሉ ይላል አሰፋ ፍስሃ ስለ ፌደራሊዝም በፃፈው መፅሐፍ። ያዋጣቸውን አዋጥቷቸው ይሆናል። የኛ ግን የቆመበት መሰረት በራሱ «ፀብ ለሚሹ የሜዳ ጠረጋ» ስለሆነ አልተሳካም ብንል አያኳርፍም። የዘውግ ፖለቲካ አያዋጣም ሲባል እንዲሁ ሳስበው ደስ አይለኝም ከሚል የሚሻገር ሰበብ አለው።ማንበብ ይቀጥሉ…

የኔ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ!

ነፃነት ያልነካው ትዳር እና ሀገር መፍረሱ አይቀርም ብዬሻለሁ። አልሰማሽም። አለመስማት የአፍራሾች ምልክት ነው። የማይሰሙ መንግስታት ሀገራቸውን፣ የማይሰሙ ባለትዳሮች ትዳራቸውን ያፈርሳሉ። የቤቴ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ነሽ። ሲበዛ ትጠረጥሪኛለሽ። ጥርጣሬሽን ለማረጋገጥ ንብረቶቼን ያለፍቃዴ ትበረብሪያለሽ፣ ልብሶቼን ትፈትሻለሽ፣ ቴክስቶቼን ከፍተሽ ለማንበብ ትሞክሪያለሽ። የአስቸኳይ ጊዜማንበብ ይቀጥሉ…

የብሔር ጥያቄ

የታፈኑ ጥያቄዎች እና ፍላጎቶች ተብላልተው ጉልበት ሆነው ይመጣሉ እንጂ ተዳፍነው አይቀሩም! የብሔር ጥያቄም እንዲያው ነው። ከዘመነ ኃይለስላሴ በፊት ግዛቶች ራሳቸው በራሳቸው የማስተዳደር አንፃራዊ ነፃነት ነበራቸው።የሚያስተዳድራቸው የራሳቸው ሰው ነበር። ልዝብ ፌደራሊዝም አይነት ነበሩ። ኃይለስላሴ መጥተው ያንን ሰባበሩት። (ዶ/ር ፍስሃ አስፋው እናማንበብ ይቀጥሉ…

እኔም!

ስሜት አልባ ነህ ብለሽኝ፣ «አልነበርኩም» ብዬሻለሁ። እውነቴን ነው። የስሜቴን ጅረት ያደረቀችው ቀድማ የሄደችው ነበረች። ታሳዝኚኛለሽ። ያለፈ ህይወቴ ትመስይኛለሽ። ላፈቅርሽ ሞክሬያለሁ። ሳይሆንልኝ በራሴ እልፍ ጊዜ ተበሳጭቻለሁ። ትታኝ የሄደችውም እንዲህ የነበረች ይመስለኛል። «አፈቅርሃለሁ» ብላኛለች። ግን አታፈቅረኝም ነበር። ልታፈቅረኝ እየሞከረች እንደነበር ግን አውቃለሁ።ማንበብ ይቀጥሉ…

አንዳንድ አሟሟቶች

ሀበሻ አሟሟቴን አሳምረው ይላል። አሟሟት ትልቅ የክብር ሞት ላይ የተንጠለጠለች አላቂ እቃ ነች። የሚደነቅ አሟሟት እንዳለ ሁሉ ግራ የሆነ አሟሟት አለ። ላልቃሽ ቤተሰብ የሚቸግር የሚመስል። ከሞተ የገዘፈ የሚመስል ሰውን ሞት ተኩነስንሶ እና ተልከስክሶ አንሸራቶ ይጥለዋል። ከሞቱ አሟሟቱ አስብሎ ያሳዝናል። ጊዜውማንበብ ይቀጥሉ…

ታስፈሩኛላችሁ

ታስፈሩኛላችሁ አለ አስኮ ጌታሁን ታስፈሩኛላችሁ! ሳያድግ ያስረጃችሁት የጎሳ ፖለቲካ ውስጥ ገብታችሁ «የበለው በለው» ቅኝታችሁን ጥኡም ሙዚቃ ነው ስትሉ ታስፈሩኛላችሁ። «ሀገር ተዘረፈ ሲባል» ሆ ብላችሁ ስትተሙ ሳይ፣ለማስጣል የመሰለኝ መትመማችሁ አብሮ ለመዝረፍ መሆኑን ሳውቅ ታስፈሩኛላችሁ። በጥላቻ ጄሶ የታሸ የተበድለናል ለቅሶችሁ ውስጥ ያለውማንበብ ይቀጥሉ…