ይሄ የኔ ትውልድ

(የዚህ ፅሁፍ ባለቤት፣ እራሱን ከትውልዱ መገለጫዎች አልነጠለም፣ አይነጥልም። ፅሁፉም ፍፁም ጅምላ ምደባ አይደለም)  ይሄ የኔ ትውልድ የተካደ ትውልድ ነው። ከገዛ ዘመኑ ተገፍቶ ላለመውደቅ ፈፋ ዳር የሚውተረተር ምስኪን። ሀገር የሚያስረክቡት መስሎት ደጅ በመጥናት ሲንከራተት ቆይቶ ገሚሱ ወደ ሃይማኖት ቤት፣ ገሚሱ ወደማንበብ ይቀጥሉ…

እወድሻለሁ እኔም

«ምንድን ናት» ለሚል ጠያቂ ትርጉምሽን ባልፈታም «ሀገር ሃሳብ ብቻ ነው» የሚል ሞጋች ባልረታም ሀገሬ ሆይ እወድሻለሁ! እርግጥ፣ ሲበድሉሽ እንዳላየ፣ ሲገድሉብሽ እንዳልሰማ ሲተኩሱ እንዳልደማ ጌቶች ሲቆጡ ለስልሶ ጫን ሲሉ አፈር ልሶ ሲያስሩብሽ እንዳልታሰረ ሲመቱሽ እንዳልነበረ ሆኖ ማለፉን አውቃለሁ ቢሆንም እወድሻለሁ። «የህዝብማንበብ ይቀጥሉ…

ሀገርኛ በሽታ ይዞ፣ የባህር ማዶ መድሃኒት የመፈለግ ክፉ አባዜ

አንዳንድ ሰዎች አሉ፤ያልተማሩ የምናላቸው። ሲያማቸው ጎረቤታቸው ጋር ሄደው «ባለፈው እንዲህ እንደኔ ሲያምህ ሀኪም የሰጠህ መድሃኒት የቷ ነበረች? » ብለው ተቀብለው ያለምንም ምርመራ የሚውጡ፤ እቺን ሀገር የመሰሉ!! የውጭውን ሁሉ እያመጣን እላያችን ላይ ማራገፋችን ለዓመታት የሚከተለን ችግር ነው። እየተከተለ ይኮረኩማናል። አንሰማም። አንነቃም።ማንበብ ይቀጥሉ…

ሳንሱራም!

ሳንሱራሞችን አትከልክሏቸው፣ ብትከለክሏቸውም አይከለኩልም የሚል ያልተከተበ ህግ አለ መሰለኝ።ሰዉ ሳንሱራም ነው። ያንተ ሃሳብ በገዛ ሞዱ ልክክ ብሎ ካልገጠመለት፣ ይጎመዝዘዋል። ሊያጣጥለው ላይ ታች ይወርዳል። አይዞህ ብቻህን አይደለህም፤የብዙዎቻችን ችግር ነው። የገዛ ሃሳብን እያሽሞኖሞኑ፣ የገዛ ልጅ ነው ብለው ከነንፍጡ የሚወዱ ሰዎች የሌሎች ለየትማንበብ ይቀጥሉ…

ተሰቅለን ነበር…ወረድን!

ሳምን፣በእድሜው ማምሻው መቋሚያ ይዞ፣ቅድመ ግብዓተ መሬቱን እንደሚማጠን ሰው አልነበርኩም። ቀንበጥ እድሜያችን ገፅ ላይ የተፃፈው እየሱስ ብቻ ነበር።ጌታ ሆይ ብሎ ጀምሮ፣ጌታ ሆይ ብሎ የሚቋጭ (እንዲያውም አይቋጭም ነበር)…የሚዘልቅ! ,,, መቁረቢያ እድሜው ሲደርስ፣ «የእግርህ መርገጫ የሆነችው ምድር ላይ ስትመጣ፣እኔ ላይ እርገጥ» ብሎ እንደሚንጋለልማንበብ ይቀጥሉ…

አዲስ አምላክ መፍጠር ሲያምረን

የሰው ልጅ ትልቅ ሃይማኖት የመፍጠር ፎንቃ ያለው፣ሃይማኖታዊ ፍጡር ነው።እንደውም ሰውን ከእንስሳ የሚለየው ሃይማኖት ነው። ማሰቡ እንዳንል፣ጭንቅላቱን ለኮፍያ ማስቀመጫ ብቻ የሚያውል፣ ለሂውማን ሄሯ ማደላደያ የምታውል አይጠፉም። ግምቱን ነው። እንደ ፍሮይድ ሳይንስ በቅርብ ዓመታት ውስጥ ሃይማኖትን ይተካዋል የሚል ግብ አይመቴ መላምት አልሰጥም።ሰውማንበብ ይቀጥሉ…

ዳግማዊ ስቅላት

የመሲሁ ስቅየት ግርፊያ ስቅላቱ አምላክ ነኝ ስላለ በድምቀት ተሳለ የኛንስ ስቅላት ማነው ያስተዋለ? ተመልካች ጠፍቶ እንጂ ዐይን የሚቸረን እኛም መስቀል ላይ ነን፣ ቄሳራዊ ሚስማር ዘልቆ የቸነከረን ዘውትር ዱላ እና አሳር ዘውትር ችንካር ሚስማር የሚገዘግዘን የሚጠዘጥዘን እኛም ክርስቶስ ነን! ሺ ዱላማንበብ ይቀጥሉ…

ሰው ሳይቀና ሀገር አይቀናም

አንድ ሰው ራሱን በዘር መግለፁ ችግር ያለው አይመስለኝም። ችግሩ ዘረኛ መሆን ላይ ነው።ዘረኛ መሆንም ሃሳብ እንጂ ተግባር እስካልሆነ የከፋ ችግር አይሆን ይሆናል። ግን፣ዘረኝነት በልብ ይዘው የሚቆዩት ብቻ አይደለም። ካልወጣ፣ ሌሎች ካልጠላ፣ አጋጣሚውን ሲያገኝም ካልደቆሰ አስችሎት አርፎ መቀመጡን እንጃ! አንዳንድ አስተሳሰቦችማንበብ ይቀጥሉ…

ሁለት ስፍራ፣ ሁለት ዓለም!

አስፋልት ዳር ያለች አነስተኛ ዳስ! ሃይለኛ ዝናብ ይዘንባል። ሰማዩ የላስቲክ ቤቷ ውስጥ ያለው መከራ ያነሳት ይመስል፣ ተጨማሪ መከራ ያዘንባል። ውስጥ… አንዲት እናት ተኝተው ያቃስታሉ።ምን ማድረግ እንዳለበት ግራ የገባው የአስራ ሁለት ዓመት ልጅ አጠገባቸውቁጭ ብሏል።የደረቀ እንባ አሻራውን ጉንጮቹ ላይ ትቷል። ሴትየዋ፣ማንበብ ይቀጥሉ…

ሚስቴ ፓለቲከኛ ናት

ፓለቲካ አልወድም። የማልወደው፣ ሰዎች የሚያንቀሳቅሱት ሳይሆን ሰዎችን የሚያንቅሳቅሳቸው ስለሆነ ነው። ፓሊዮ እና ዚካ ተቀላቅለው የፈጠረቱ ይመስለኛል። የጠላሁት ቤቴ ገባ። አትግባ እንዳልለው፣ ይዛው የገባችው ባለቤቴ ናት። መች እንደጀመራት ሳላውቅ ፓለቲካ አተኮሳት። ቀጥሎ አነደዳት። ተቃጠለች። እሳቷ እሳቴ ሆነ። ፍቅር ከሰራን በኋላ ሁሉ፣የአደረግነውንማንበብ ይቀጥሉ…