( በማርች 8 ሰበብ ወዲህ የተሳበ።ሃሃሃ፣ ይሄን ሰፈር ባሰብኩት ጊዜ ለራሴ እድቃለሁ። አንዳዶች ይህ ፖስት ብልግና አለበት ይላሉ።ጭብጡ ብልግና አይደለምና አቋቋማችሁን አስተካክሉ። ከዛ ወደ ፅሁፉ…) **** የኟ ሰፈር “እናት ፌሚኒስቶ” አመፁ። የሚገርመው ማመፃቸው አይደለም፣ እሱን ሰፈሩ ለምዶታል። ድንገት ተነስተው ሁሉምማንበብ ይቀጥሉ…
ነገር ቶሎ አይገባኝም
ደም መላሽ እባላለሁ… ከደም ውጪ ታሪክ መዘገብ የሚከብደው ዓለም ላይ እኖራለሁ… አባቶቻችን ደማቸውን አፍሰው፣ አጥንቸውን ከስክሰው… ሲባል፣ ክርስቶስ በደሙ አዳነን( በደሙ ሃጢያታችንን አጠበልን) ሲባል፣ ያለምንም ደም፣ ኢትዮጵያ ትቅ”ደም” ሲባል ( ትቅደም የሚለው ቃል፣ አፈፃፀሙም ቃሉም “ደም” እንዳለበት ሳይ)… አይገባኝም። ዓለምማንበብ ይቀጥሉ…
አራት ነጥብ (።)
አራት ነጥብ (።) ከቤት ስወጣ የሰፈሬ ሰዎች ሁላ ከዚህ በፊት አይቼው በማላቅ አግድም ወንበር ላይ በብዛት ተደርድረው ፀሀይ ይሞቃሉ። ፊታቸው ላይ ደስታ ባራት እግሩ ቆሟል። የወንበሩ ቁመት ከዚህ በፊት አይቼ የማላውቀው አይነት ነው። ምቾቱም ሳይቀመጡ የሚገምቱት ነው። አንድ ቀን ቁጭማንበብ ይቀጥሉ…
“የማርያም ልጅ ነኝ”
ታክሲ የከተማችን መሲህ ይመስለኛል፣ አስራ ሁለት ሐዋርያቱን ይዞ የሚጓዝ በእግር ከመኳተን፣ በፀሐይ ከመጠበስ ሊያድነን የመጣ መሲህ። ታክሲ ውስጥ ነኝ፣ ጋቢና። ታስበው ይሁን ተሰብስበው የማይገቡኝን ጥቅሶች እያፈራረኩ ማየት ጀመርኩ _ እንደልማዴ። ጋቢናው በብዙ መላዕክት ስዕል ስለተሞላ መለስተኛና ተንቀሳቃሽ ቤተመቅደስ መስሏል። ከጥቅሶቹማንበብ ይቀጥሉ…
ለምን አትተኛም።
እሰከመቼ በአሳቻ ለሊት፣ በሀሰተኛ ዶሮ ጩኸት እየነቃህ!? አርፈህ አተኛም? አርፈህ አገሩን አትመስልም? ይልቅ እንካ ምክር፣ ሀሰተኛ ዶሮ በኳኮለ ቁጥር፣ የሚናድ፣ የሚጣስ የእንቅልፍህ አጥር መኖርህን አብዛ ከመተኛት ቅጥር። ** ተኛ። ብትችል አውቀህ ተኛ። “አውቆ የተኛን ቢቀሰቅሱት አይሰማም ” ይላል የተኚዎች ተረት።ማንበብ ይቀጥሉ…
ውልደትህን ከማይሻ…
ብዙዎች በሚወዱት ቀን፣ ብዙዎች የማይወዱትን ግጥም ብንለጥፍ… የሚወደን አምላክ ምን ይለናል? እሱ ምንም አይልም፣ የሱ ነን የሚሉት እንጂ… አዳም፣ በብዙ ምግብ መካከል አንዲቱን ቢከለከል እሷኑ አንክቶ በላ፣ ከእግዜር ጋር ፍቅራቸው ላላ። እኔ፣ በብዙ ምግብ መካከል፣ አንዲት ጉርሻ ተነፍጌ፣ በማይላላ የጠኔማንበብ ይቀጥሉ…
ሰጎች
ሰዎች ይመስሉኛል። በጎችም ይመስሉኛል። ሰዎች ብዬ ስጠራቸው አቤት ይላሉ። በጎች ብዬ ስጠራቸውም አቤት ይላሉ። ሰዎች ናቸው በጎች? በቡድን ነው የሚኖሩት። በቡድንን ይንቀሳቀሳሉ።እንደማንነታቸው ሁሉ አንዳቸውን ከአንዳቸው ለመለየት ከባድ ነው። ጠጋ ብዬ እረኛቸውን ጠየኩት። “አልገባኝም በጎች ናቸው ሰዎች? ” ፈገግ ብሎ መለሰልኝ፣ማንበብ ይቀጥሉ…
ስሚ!
ስሚ መስሚያ ካለሽ። ከሰማሽ ደሞ ተስማሚ፤ ወዲያ ሂጂልኝ እስቲ። ማነሽ እውነት ነኝ የምትይ፣ እስቲ ስሚን የስንቱን አለመስማት እንችላለን? መንግስት አይሰማን፣ ፈጣሪ አይሰማን፣ አንቺ አትሰሚን… ኸረ እስቲ አንቺ እንኳን?!! ማን ነበረ ስምሽ? “እውነት ” ነው አይደል? እውነቱን ልንገርሽ፣ በደረስኩበት ባትደርሺ ደስማንበብ ይቀጥሉ…
ሁለቱ ካድሬዎቹ
ሁለቱ ካድሬዎች የማነ እና ዳንኤል ካድሬዎች ናቸው። ይሁኑዋ ታዲያ! ካድሬ በበዛበትሀገር እነገሌ ካድሬ ናቸው ማለት ምንድነው? የማነ እና ዳንኤል ጓደኛሞችም ናቸው፤ ውሏቸው አንድ ላይ ነው፣ ወሬያቸውም አንድ ዓይነት። ስለ ልማቱ ያወራሉ፣ ያደጉትም፣ ያላደጉትም ፣የማያድጉትም ከኢትዮጵያ መውሰድ ሰላለባቸው ተሞክሮ ያወራሉ፣ አዲስማንበብ ይቀጥሉ…
የዚህ ትውልድ አባል ነኝ!
በመውደድ ወይ በመጥላት አልፍቀውም። ያለፈው ትውልድ ውላጅ ነኝ። የመጪው ትውልድ ወላጅ ነኝ። ያለፈው ትውልድ “አዬ ልጅ” እያለ ያሾፍብኛል፤ መጪው ትውልድ ይኮርጅኛል( ወደፊት “አይ አባት” ብሎ ይስቅብኝ ይሆናል -ግድ አይሰጠኝም) ለሁሉ ፈጣን ነኝ። ሁሉን በፍጥነት አይቼ በፍጥነት አልፋለሁ። ችክ ማለት አልወድም።ማንበብ ይቀጥሉ…