“እንዴት ዋልሽ?”

(መነሻ ሃሳብ፡ የሰርክ አለም መጋቢያው ‹‹አሮጌው ገንዘብ›› እና የሐና ሃይሌ ‹‹ሀው ወዝ ማይ ደይ›› አጭር ፊልሞች) ሥራ ውዬ እና የማታ ትምህርት አምሽቼ ሶስት ሰአት ከአስር ገደማ ቤቴ ገባሁ። ብቻዬን ከምኖርባት ሚጢጢ ቤቴ ገብቼ ከፍታ ካለው ጫማዬ ላይ ከመውረዴ ታላቅ ወንድሜማንበብ ይቀጥሉ…

አድዋ እና ‹‹ደማሟ ኢትዮጵያ››

ከውጫሌ ውል መፍረስ በኋላ፣ ኢጣሊያኖች አድዋን እና አክሱምን እንደያዙ እየገፉ መጡ። ፍልፈሎቹ የሀገራችንን መሬት እየቆፈሩ ገቡ። ‹‹በአምስት አመት ከባድ ረሃብ የተጎዳውን ችግረኛ ህዝቤ አላዘምትም›› ብለው ሲያቅማሙ የነበሩት ምኒልክ የነገሩን ገፍቶ መምጣት ሲመለከቱ ቀጥሎ ያለውን የክተት አዋጅ አወጁ። ‹‹…አገር የሚጠፋ፣ ሃይማኖትማንበብ ይቀጥሉ…

ኑሮ እና ብልሃቱ

የዘጠኝ አመቷን የጓደኛዬን ልጅ የአማርኛ ምሳሌያዊ ንግግር ላስተምር እየታተርኩ ነው። ሶስተኛው ላይ ነን። መፅሃፉ ላይ በተርታ ካሉት ውስጥ ለሷ የሚመጥነውን መርጬ አንብቢ አልኳት። ‹‹ሁለት ጉድጓድ ያላት አይጥ አትሞትም›› ጮክ ብላ አነበበች። ‹‹ጎበዝ! ምን ማለት ይመስልሻል?›› ‹‹እ….እ….›› አለች እያንጋጠጠች። ‹‹ቀስ ብለሽማንበብ ይቀጥሉ…

ቅርንጫፉ እንደ ዛፉ

የጋምቤላ ክልል የትምህርት ቢሮን ጨምሮ ዘጠኝ የክልሉ ‹‹ስራ አስፈፃሚዎች›› በሃሰተኛ የትምህርት ማስረጃ ሰበብ ተከስሰው መባረራቸውን ሰማን። በእውነቱ፤ በዚህ ዜና የሚገባውን ያህል ልደነግጥ ባለመቻሌ አዝኛለሁ። በስንቱ ልደንግጥ…? በተለይ በትምህርት ጉዳይ መደንገጥ ያቆምኩት፤ በዛ ዘሞን መንግስት እድሜ ጠገቡን ትምህርት ቤት ‹‹ለልማት›› ማፍረሱንማንበብ ይቀጥሉ…

ሸምበቆ እና ሸንኮሬ

አመት ከማይሞላው ጊዜ በፊት ለመስክ ስራ ወጣ ስል እግረ መንገዴን ‹‹የአባቴን ሀገር እና ዘመዶች ልይ›› ብዬ ከተወለደበት የገጠር መንደር ጎራ ብዬ ነበር። በቅጡ ያልወጠንኩት የእግረ መንገድ ጉዞዬ ወሬ አባቴ ዘመዶች ዘንድ ከብርሃን ፈጥኖ ደረሰና እኔን ለማስተናገድ ወጥነው ሲንገላቱብኝ ሰነበቱ። በተለይማንበብ ይቀጥሉ…

ዐልቦ – (ክፍል ሶስት)

(መነሻ ሃሳብ- ዘ ሚደል ተከታታይ ፊልም) “በሱ ቀሚስ ብታስነጥሺ የጡቶችሽ ጫፍ ሳይታዩ አይቀሩም›› አለኝ ቤሪ ከእስኩ ጋር ላለኝ የማታ ቀጠሮ ስበጃጅ። ትላንት ማታ ከተፈጠረው ነገር በኋላ ለቀልድ የሚሆን ፍቅር ስለቀረው አንጀቴን በላው። ፊቴን ባልለመደው አኳኃን ስቀባ እና ሳጠፋ፣ ስሰራ እናማንበብ ይቀጥሉ…

“ዐልቦ” – (ክፍል ሁለት)

(መነሻ ሃሳብ- ዘሚድል ተከታታይ ፊልም) ‹‹ቤቷ ብቻ ስንት ካሬ እንደሆነ ታውቃለህ…ሁለት መቶ ሃምሳ ! ሁለት መቶ ሃምሳ ካሬ አስበው…ከዚህ እስከ ደብረወርቅ ህንጻ ማለት ነው…ቤቷ ከእኛ ቤት እስከ ደብረወርቅ ህንጻ ነው….በዛ ላይ እቃዎቿ…ሶፋ ብትል…የእኛን አልጋ ሶስት እጥፍ የሚሆን ሶፋ…ፍላት ስክሪን ተቪ…የውጪማንበብ ይቀጥሉ…

“ዐልቦ”

መነሻ ሃሳብ – “ዘ ሚድል” ተከታታይ ፊልም “ፍ…ቅ…ር…ተ!” ስሜ በሴት ሲጠራ ሰማሁና እጆቼን አጎንብሼ ከሰል ከምጎለጉልበት ማዳበሪያ ሳላወጣ ቀና አልኩ። ሴት ናት። ለሰፈራችን ከልክ በላይ የለበሰች፣ ለተቦዳደሰ ኬር መንገዳችን ከሚመጥነው በላይ ሸላይ ጫማ ያደረገች፣ …ቂቅ ያለች ሴት ናት። ከመስታወት የተሰራማንበብ ይቀጥሉ…

የተበረገደ ልብ

ልቤ ድው ድው። አይኔ ቦግ ቦግ። ጆሮዬ ቆም ቆም። ምላሴ ዝርክርክ አለብኝ፡- ሃብሉን ሲሰጠኝ። ልብ እና ቁልፍ አንድ ላይ ያንጠለጠለ ሃብል ነው። አቤት ማማሩ። አቤት ማብረቅረቁ። ከዚያ ሁሉ ደግሞ አቤት ትርጉሙ! ‹‹የልቤ ብቸኛ ቁልፍ ያለው አንቺ ጋር ብቻ ነው ለማለትማንበብ ይቀጥሉ…

ቅንጥብጣቢ የካናዳ ወግ (ክፍል ሁለት)

የቶሮንቶ የህዝብ ጎርፍ ገባሩ ብዙ ነው። አለም አቀፍ ነው። የአባይ ልጆች። የቀይ ባህር ልጆች። የአትላንቲክ ዳር ልጆች። የህንድ ውቅያኖስ ልጆች። የጥቁር ባህር ልጆች… ጎላ ድስት የሆነ ከተማ ነው። ካርታ ላይ የሌለ ሀገር እዚህ ሀገር አውቶብስ ውስጥ ተሳፍሮ ይገኛል። በአስር ሺሆችማንበብ ይቀጥሉ…