‹‹ላግባሽ›› ብሎ ሲጠይቀኝ… አይኖቼ እንደ ስልሳ ሻማ አምፖል እየተንቦገቦጉ፣ የሰራ አከላቴ እየፋመ፣ ከንፈሬ መርበትበቴን ለማሳበቅ እየተንቀጠቀጠ፣ ሰውነቴ ያለ አግባብ እየተናወጠ… ይሄ ሁሉ አይሰሙ ደስታ እየተሰማኝ ፤ ቃላቶቼን መጥኜ፣ መፈንደቄን ደብቄ ቀዝቀዝ አልኩና፣ ረጋ አልኩና፣ በሴት ልጅ ወግ፤ ‹‹እሺ…›› አልኩት። ይወደኝማንበብ ይቀጥሉ…
የጓዳ ውስጥ ባሪያ እና የመስክ ላይ ባሪያ
(ይህ ፅሁፍ ከመጠነኛ ጭማሪ እና ቅናሽ በስተቀር ታዋቂው የጥቁር አሜሪካዊያን መብት ተሟጋች ማልኮም ኤክስ በአንድ ወቅት ያደረገው ንግግር ትርጉም ነው ሊባል ይችላል) ማልኮም ኤክስ በሰላሳ ዘጠኝ አመቱ በሰው እጅ ተገድሎ ከሞተ ሃምሳ አንድ አመታት አልፈዋል። በዚህ ንግግሩ ውስጥ ያለው ምሳሌማንበብ ይቀጥሉ…
የሞተን ፈረስ ጥቅም ላይ ስለ ማዋል
ሰሞኑን የምር የሚያሰለጥን ስልጠና ውስጥ ነበር የከረምኩት። ከትምህርቶቻችን አንዱ ፤ ‹‹የሙት ፈረስ አስተዳደር›› በሚል ርእስ የተቀመጠ ነበር። አስደማሚው አሰልጣኛችን ይህንን ትምህርት የጀመረው የሚከተለውን በመጠየቅ ነበር። ‹‹ፈረስ እየጋለባችሁ ነው እንበል። በፍጥነት እየጋለባችሁ ሳለ ፣ ፈረሱ ላይ እንዳላችሁ የፈረሱን መሞት ተረዳችሁ። በዚያችማንበብ ይቀጥሉ…
የቤት እመቤት በመሆን ውስጥ እመቤትነት አለ?
ላለፉት ጥቂት ቀናት ያገኘኋቸውን ወንዶች በሙሉ አንድ ጥያቄ ስጠይቅ ነበር፡፡ ‹‹የቤት እመቤት ምን ማለት ነው?›› ከአንድ ወይም ሁለት መልሶች ውጪ የተሰጡኝ ፍቺዎች በሚከተሉት ሀረጎች ሊጠቃለል ይችላል፡፡ ‹‹የማትሰራ ሴት›› ‹‹ስራ የሌላት ሴት›› ‹‹ገቢ የሌላት ሴት›› ‹‹ስራ አጥ ሴት›› ‹‹ስራ ፈት ሴት››ማንበብ ይቀጥሉ…
የነገን አልወልድም
“መላኩ ተፈራ፣ የእግዜር ታናሽ ወንድም የዛሬን ማርልኝ፣ የነገን አልወልድም” በቀይ ሽብር አመታት ልጆቻቸውን ለሞት መገበር ያንገፈገፋቸው እናቶች መላኩ ተፈራ ጎንደርን ያስተዳድር በነበረበት ዘመን ይሉት የነበረ ግጥም ነው። የአማርኛ ፊልሞችን አያለሁ። አረረም መረረ አይታክተኝም…በትጋት አያለሁ። የውድቀታችን ባንዲራ ለመሆን በተርታ ከተሰለፉ ፊልሞቻችንማንበብ ይቀጥሉ…
ሰማዕታትን አንረሳቸውም
ከሰማኒያ አመታት በፊት ኢትዮጵያዊያን ዘማቾች አይተው የማያውቁትን የአውሮፕላን ድብደባ የገለፁበት ግጥም እንዲህ ይላል። ‹‹በትግራይ ቢመጣ መቼ ይገባ ነበር፣ በጎንደር ቢመጣ መቼ ይገባ ነበር፣ በሸዋ ቢመጣ መቼ ይገባ ነበር፣ በጎጃም ቢመጣ መቼ ይገባ ነበር፣ በሰማይ ላይ መጣ በማናውቀው አገር….›› ጣልያኖች በማናውቀውማንበብ ይቀጥሉ…
የፍቅረኞች ቀን
የፍቅረኞች ቀንን የማልወደው ፍቅርን ስለማልወድ አይደለም፡፡ ፍቅርን የሚዘክር ቀንን ስለምጠላም አይደለም፡፡ የፍቅረኞች ቀንን የማልወደው ከፍቅረኞች ቀን ይልቅ የጥቅመኞች ቀን እየሆነ ስለመጣ ነው፡፡ ‹‹ከወደድከኝ የፍቅረኞች ቀን እለት ግሎባል ሆቴል ውሰደኝ›› የሚል ማስታወቂያ በየቦታው ተለጥፎ ሳይ፣ ‹‹እኔ ዘንድሮ እንደአምናው በቸኮሌት አልሸወድልህም…ዘንድሮ የምፈልገው የኢቴልኮንማንበብ ይቀጥሉ…
ሀገሬ
‹‹ሀገሬ…›› (መነሻ ሀሳብ ፤ ‹‹ ዘ ሬቬናንት›› ፊልም) በከባድ ንፋስና ዝናብ ሰአት ትልልቅ ዛፎችን አይታችሁ ታውቃላችሁ? የቅጠሎቹን ሳያቋርጡ መርገፍገፍ፣ የቅርንጫፎቹን መንቀጥቀጥ ስታዩ ‹‹ይሄ ዛፍ ካሁን ካሁን ወደቀ፣ ካሁን ካሁን ተገነደሰ ››ብላችሁ ሰግታችሁ ይሆናል፡፡ ቅርንጫፎቹ ቅንጥስ እያሉ ቢወድቁም፣ ቅጠሎቹ ባንድነት ቢረግፉም፣ ግንዱንማንበብ ይቀጥሉ…
“አልወለድም!” (ክፍል ሁለት)
እየተደናበረች በመሮጥ ላይ ሳለች እንቅፋት መትቷት በሙሉ ሰውነቷ ው-ድ-ቅ ስትል ሁለቱም ተናወጡ፡፡ ዘፈንኑን በድንገት አቆመ፡፡ ‹‹ራበኝ!›› አለች በእንቅፋት የተነደለ አውራጣት ጥፍሯን እያሻሸች፡፡ መድማት ጀምሯል፡፡ ‹‹እኔም ርቦኛል…እማ›› ብሎ መለሰላት፡፡ ዝም ብላ ቁስሏን እና ረሃብዋን ስታስታምም ትንሽ ጊዜ ጠበቀና፤ ‹‹እማ…ደሃ በመሆንሽ ታሳዝኚሻለሽ…ነገር ግን ለኔማንበብ ይቀጥሉ…
“አልወለድም!” (ክፍል አንድ)
‹‹አልወለድም!›› የደራሲ አቤ ጉበኛ እጅግ ታዋቂ ስራ ነው፡፡ የሚከተለው ድርሰት በአመዛኙ በአቤ ጉበኛ አልወለድም መፅሃፍ ጭብጥ፣ ገፀባህርያትና ምልልልሶች ላይ በደንብ ተመስርቼ የፃፍኩት የአልወለድም ዘመነኛ እና አዲስ ገፅ ነው፡፡ የትረካው አቅጣጫ፣ የገፀባህሪዎቹ ገለፃ እና ምልልሶች ግን በአመዛኙ ተለውጠዋል፡፡ ‹…ግን ከተመረጡ ሃብታሞችማንበብ ይቀጥሉ…