….አቤት የቤተሰብ ፎቶዋችን ማማሩ! የጥርሳችንንጣቱ! የሳቃችንድምቀቱ! አባዬ እበርበት ይመስል እኔን ጥብቅ አድርጎ አቅፏል፡፡ እማዬ ይበርባት ይመስል ናሆምን ጥብቅ አድርጋ አቅፋለች፡፡ እኔ እና ናሆም ያለን ጥርስ ሁሉ እስኪታይ ስቀን ከእናትና አባታችን ስር እንደጉልቻ ቁጭ ቁጭ ብለናል፡፡ የሚያስቀና አራት ጉልቻ፡፡ እዩት የእማዬንማንበብ ይቀጥሉ…
ሄሊ እና የመንዝ ወርቅ
በዚያ ሰሞን ለአጭር ጊዜ ስራ የተቀጠርኩበት አንድ ቢሮ ፈረንጅ አለቃዬን ልተዋወቃት ቢሮዋ ሄድኩ፡፡ ‹‹ኦው!አዲሷ ኮንሰልታንት! ማነው ስምሽ?›› አለችኝ አየት አድርጋኝ፡፡ ‹‹ሕይወት እምሻው›› እኔን ሳይሆን የምታገላብጠውን የወረቀት ክምር አያየች ‹‹ኦህ…አጠር አድርጊውና ንገሪኝ ›› አለችኝ ፡፡ ግራ ገባኝ፡፡ ‹‹ይቅርታ ምን አልሽኝ?›› አልኳትማንበብ ይቀጥሉ…
ላምብ፤ የበግ ለምድ ለብሶ የመጣው ተኩላ ፊልም
ዘ ጋርዲያን <<ያሬድ ዘለቀ የሀገሩን ባህልና ወግ በሚያስደንቅ ሁኔታ አይቶ ያሳየበት ድንቅ ፊልም›› ብሎ ያወደሰው ላምብ ወይም ዳንግሌ በካን ፊልም ፌስቲቫል የ 68 አመት ጉዞ ለመጀመሪያ ጊዜ በይፋ ተመርጦ የታየ የኢትዮጵያ ፊልም ነው፡፡ ትላንት ፊልሙ በኤድና ሞል ሲኒማ እየታየ መሆኑንማንበብ ይቀጥሉ…
ስለ እኔ እና የመጀመሪያው ፍቅሬ
(ክፍል አንድ) ‹‹እጅ ወደ ላይ!›› ሎጋ ቁመናው ተስተካክሎ፣ ፍቅሩ የሚስብ አይኑ አባብሎ፣ …ላፈጣጠሩ እንከን የለው፣ አረ እንዴት አርጎ ነው የሰራው አረ እንዴት አርጎ ነው የሰራው›› ድምፃዊት ሂሩት በቀለ ከአሰልቺ የጎበዝ ተማሪነት ቀናት በአንዱ…. ለስምንት ሰአት ሃያ ጉዳይ ገደማ ከዶርም ወጥቼማንበብ ይቀጥሉ…
ሸሌ ነኝ
‹‹ነይ እዚህ ጋር ልብስሽን አውልቀሽ ውስጥ ሳትገቢ…ብርድልብሱ ላይ ተኚ›› ሲለኝ፤ ልማድ ሆኖብኝ መግደርደር ዳድቶኝ ነበር፡፡ ድሮ፤ ልጃገረድ እንዳለሁ ጊዜ መሽኮርመም፡፡ ሰው እንጂ ሴት ያልሆንኩ መስሎኝ፡፡ ስጋ ሸጬ እንጀራ ልገዛ ያልመጣሁ መስሎኝ፡፡ ገንዘብ ተቀብዬ ደስታን ልሰጥ ያልመጣሁ መስሎኝ፡፡ አንገቴን እንደሰበርኩ ወደማንበብ ይቀጥሉ…
ማሂ ድንግሏ
ልጃገረድነት ሰልችቶኛል፡፡ ቦይፍሬንድ አምሮኛል፡፡ ‹‹የኔ ፍቅር›› መባል፣ ‹‹የኔ ቆንጆ›› ተብሎ መጠራት አሰኝቶኛል፡፡ እስከዛሬ ድረስ ‹‹ትምህርቴን በስርአት ለመከታተል››፣ ‹‹ከአልባሌ ቦታ ለመራቅ››፣ ‹‹መቅደም ያለበትን ለማስቀደም›› ፤ የከጀሉኝን በአልገባኝም እየሸወድኩ፣ የጠየቁኝን እምቢ እያልኩ፣ ስንት የተቀበረ የወንድ ፈንጂ በጥንቃቄ አልፌ፤ ልጃገረድ ሆኜ ቆይቻለሁ፡፡ ኮሌጅማንበብ ይቀጥሉ…
ዶሮ ብቻ ያልሆነው የዶሮ ወጥ
የዛሬ አመት አካባቢ ኬንያ ለስራ በቆየሁበት ወቅት የአመት በአላችን ንኡስ ምግብ፣ የገበታችን ንግስት ዶሮ ፤ከ ‹‹ማዘር ቤት›› እስከ አምስት ኮከብ ሆቴል አንዴ በሩዝ፣ አንዴ በኡጋሊ እየታጀበች፤ ከቀን ላብ አደር እስከ ቁንጮ ፖለቲከኛ አፍ እንደዋዛ በየእለቱ ስትገባ ገርሞኝ ነበር፡፡ ይሄን አይቼማንበብ ይቀጥሉ…
የቴዎድሮስ “ራዕይ”
በጌትነት እንየው ፀሃፊነትና አዘጋጅነት የቀረበውን ‹‹የቴዎድሮስ ራዕይ›› ቲያትር ለመመልከት ትላንት ብሔራዊ ቲያትር ሄድኩ፡፡ ሞቶ በክብር የመኖር ተምሳሌት የሆኑት የአጤ ቴዎድሮስ ታሪክ የማይመስጠው ኢትዮጵያዊ ማን አለ! ቲያትር ቤቱ ቲያትሩ ከመጀመሩ አንድ ሰአት በፊት ሞልቷል፡፡ ቲያትሩ ዛሬ ዛሬ ከጌትነት እንየው ብቻ ልንጠብቀውማንበብ ይቀጥሉ…
የአድዋ ድል በአል ሲከበር
ልጅ ሆኜ የአድዋ ድል በአል ሲከበር ያለው ሸብ-ረብ ስለምን እንደሆነ አይገባኝም ነበር፡፡ ለምን? የድሉን ዋጋ የመገመቻ እውቀት ስላልነበረኝ፡፡ የካቲት 23 መጥቶ በሄደ ቁጥር በአንዱ ጆሮዬ ጥልቅ ብለው በሌላው የሚወጡት ቃላትና ግጥሞች ብቻ ትዝ ይሉኛል፡፡ ‹‹አጤ ምኒልክ›› ‹‹የውጫሌ ውል›› ‹‹ እቴጌማንበብ ይቀጥሉ…
የሁለት እህትማማቾች ወግ
የዛሬ ወር ተኩል ገደማ ለሳምንታት ቆይታ ወደ አሜሪካ ሄጄ ነበር፡፡ የጉዞ ሃሳቤን የሰሙ እዚህም አዚያም ያሉ ዘመድና ወዳጆቼ እኔ ‹‹ልዋጭ ልዋጭ›› የምለውን የእቃ ውሰጂና አምጪልን ጥያቄያቸውን ጀመሩ፡፡ በርበሬና ሽሮን በጋላክሲ ስልክና በሌቫይስ ጅንስ የመለወጥ ጥያቄ፡፡ ቡላና ኮሰረትን በናይኪ ስኒከርና በሬይባንማንበብ ይቀጥሉ…