ያለ ተጨማሪ ጥቅማጥቅም ለተከታታይ ቀናት በግብዣ ያጣድፍሻል። በስጦታ ያንበሸብሽሻል። ምንም ነገር ውድ ነው ከማይል ወንድ ጋር መሆን ምንኛ ያስደስታል? ያየሽውን ሁሉ በሁለትና በሶስት አባዝቶ፣ ያማረሽን ሁሉ በጅምላ ገዝቶ የሚሰጥ ወዳጅ እንዴት ያረካል? ብለሽ ታስቢያለሽ። የቁርስ-ብረንች-ምሳ- እራት ግብዣዎቹ ያልለመድሻቸው አይነት ናቸው።ማንበብ ይቀጥሉ…
ከባልሽ ሐብታሙን ሽማግሌ የመረጥሽ እለት
ከአስራ ሶስት እህት ድርጅቶቹ በአንዱ ውስጥ ጀማሪ የማርኬቲንግ ሰራተኛ ነሽ። ድካሙ ብዙ፣ ደሞዙ ትንሽ ነው። አግብተሻል። የሁለት አመታት ባልሽ ከአመት በፊት ከስራ ከተቀነሰ ወዲህ ስራ ለማግኘት ሳያሳልስ ደጅ ቢጠናም አልሆነለትም። ብዙ ነገር አይሆንለትም። ግንባር ብቻ ሳይሆን ራእይም የለውም። የሚሰራውን ሰርቶ፣ማንበብ ይቀጥሉ…
ዝክረ- ኳራንታይን (ክፍል ሁለት)
ውበት የውበት ሳሎኖች እንደ መድሃኒት መደብሮች፣ የምግብ መሸጫ ሱቆች እና የህክምና ጣቢያዎች ሁሉ ‹‹አንገብጋቢ አገልግሎት አቅራቢ›› ተብለው መመደብ እንደነበረባቸው ያየንበት ጊዜ ነው- ኳራንታይን። የሴቶች ትክክለኛ የጠጉር ቀለም (በአብዛኛው ሽበት) ፣ ትክክለኛው ኪንኪ ጠጉርን (ሂውማንሄር ለረጅም ጊዜ በካውያ ሳይሰራ ሲቀር ተሳስሮማንበብ ይቀጥሉ…
ዝክረ- ኳራንታይን
ከወረርሽኙ መባቻ አንስቶ፤ ‹‹ብትችሉ ከቤት ንቅንቅ አትበሉ›› ከተባለ ጀምሮ፣ መደበኛ የቢሮ ስራቸውን በቢጃማ፣ ቢያሻቸው ሶፋቸው፣ ቢላቸው አልጋቸው፣ ሲያምራቸው መሬት ተቀምጠው በርቀት እንዲሰሩ ከተፈቀደላቸው፣ እድል ከቀናቸው ጥቂት አዲስ አበባዊያን መሃል ነኝ። እግሮቼን ከሰፈር ሳልርቅ ለማፍታታት ወጣ ከማለት፣ ወጥ ወጥ፣ ቤት ቤትማንበብ ይቀጥሉ…
‹‹እግዚአብሔር ለሚረሱት ሁልጊዜ ማስታወሻ ይልካል››
ብዙዎቻችን፣ ከልጅነታችን አንስቶ ‹‹ የጭንቅ ጊዜ ሳይመጣ በጉብዝናችሁ ወራት ፈጣሪያችሁን አስቡ›› ብንባልም አንደበታችን ለፀሎት፣ ጉልበታችን ለስግደት የሚዘጋጀው መከራ ከፊታችን ሲደቀን ብቻ ነው። አመዛኙ ፀሎታችን ‹‹ከዚህ ፈተና አውጣኝ››፣ አብዛኛው ልመናችን ‹‹ይሄን የመከራ ጊዜ በድል አሻግረኝ›› ነው። ሲጎድለን ‹‹ይሄን ጨምርልኝ›› ክፍተት ሲታየንማንበብ ይቀጥሉ…
ታዛ
አይ የሰው ኑሮ መለያየት!
ካናዳ የሚገኘው የመስሪያ ቤታችን ቅርንጫፍ ባልደረባ ለስራ ጉዳይ የኢሜል መልእክት ልካልኝ ምን ብላ ጀመረች? ‹‹እንዴት ይዞሻል? አዲስ አበባ ያላችሁ ሰራተኞች ከቻላቸሁ ከቤት እንድትሰሩ እንደተመከራችሁ ሰማሁ። እኛ ያው በግድ፣ በመንግስት ትእዛዝ ቤት ታሽገን ተቀምጠን ልናብድ ነው። ወላ ሬስቶራንት ሄዶ መብላት የለ፣ማንበብ ይቀጥሉ…
መፋቀር አጋባን፣ መፋቀር አኖረን
ሰሞኑን ‹‹ከእገሌ ዘር አትግቡ…የተጋባችሁም ተፋቱ›› መባሉን ስሰማ ይህችን ላካፍላችሁ መጣሁ። የእኔ እና የባለቤቴ ሰርግ ብዙዎቹን አግልሎ ያስቀየመ፣ በሃያ ሁለት ሰዎች እንግድነት (ሁለቱ በወሬ ወሬ ሰምተው ራሳቸውን ጋብዘው ነው) ብቻ የተፈፀመ ነበር። ደህና ቤት በደህና ዋጋ ለመከራየት ከሰፈር ሰፈር እየተንከራተትን መቶዎችንማንበብ ይቀጥሉ…
የዛሬ አክቲቪስት የማይነግርህ ዘጠኝ አንኳር ነገሮች
1. ‹‹ ክፋቱ አዶልፍ ሒትለርን የዋህ የሚያስብል ነው ፣ ጭካኔው እና ግፉ ከግራዚያኒ የበለጠ ነው፣ ተንኮሉ ከሳጥናኤል የረቀቀ ነው፣ ሴራው ከቀኝ ገዢ የተወሳሰበ ነው…ይሄ ዘር ታሪካዊ ጠላትህ ነው….ያኛው ዘር መቼም የማይተኛልህ ነው፣ ካላጠፋኸው ሊያጠፋህ ነው…ካልቀደምከው ሊቀድምህ ነው›› እያለ የሚነግርህ…እዚያ…ከጋራው ማዶ…ማንበብ ይቀጥሉ…
ትዳርን ከነ ብጉሩ
አንድ፡ ‹‹ወሲብ በአርባዎቹ›› ጥር የሰርግ ወር አይደለ? የትዳር መጀመሪያ…? ያንን ይዤ ትዳርን ሀ ብለው ለሚጀምሩም፣ ትንሽ ለዘለቅንበትም፣ ገና ዳር ዳር ለሚሉም ቁምነገር አይጠፋውም ብዬ ‹‹ትዳርን ከነብጉሩ›› የሚገልፁ እውነተኛ ታሪኮችን ፍለጋ ባለትዳሮችን ማነጋገር ጀምሬ ነበር። አሁንም ከዜሮ እስከ አርባ አመታት የትዳርማንበብ ይቀጥሉ…