ስኳር መች ይጣፍጣል?!

በዚህ እጅ ያልነካው ወዳጅ በማይገኝበት ክፉ ዘመን ሰላሳ አራት አመት እስኪሞላት ድረስ የማንም እጅ ሳይነካካት ከወር በፊት የተሞሸረች ልጃገረድ ወዳጅ አለችኝ። ‹‹ያላገባኝ አይነካኝም!›› ብላ…. ‹‹ወንድ ልጅ ወተቱን በነፃ ካገኘ ላሚቱን አይገዛም›› ብላ… ስንቱን የወንድ ፈንጂ በጥንቃቄ እንጣጥ ብላ፣ ስንቱን አማላይናማንበብ ይቀጥሉ…

‹‹ስቀና….››

የታሪክ ሃሳብ፡ ዶርቲ ፓርከር ‹‹The Sexes› (1926) አኩርፌዋለሁ። ሳሎኔ እንደገባ ‹‹ተቀመጥ›› ብለውም ሶፋዬ ላይ አኩርፌ በተቀመጥኩበት ቁልቁል ያየኛል።ፈራ ተባ ይላል፣ አይኑ አይኔን ይሸሻል። ከገባ ከሁለት ቃል በላይ ደፍሮ ማውጣት ተስኖታል። ፈርቶኛል። ይሄንን ታላቅ የኩርፊያ ደመና በምን እንደሚበትነው ስለጨነቀው ፈርቶኛል። የልብማንበብ ይቀጥሉ…

ፉት ሲሉት ጭልጥ

ግንቦት ሃያ ተመልሶ መጣ። ከሶስት አመታት በፊት የግንቦት ሃያ አረፋፈዴን እንደዚህ አውግቻችሁ ነበር ። ።።።።።።።።።።።።   ዛሬ.. ግንቦት 20 ማለዳ 1.45 ከበራፌ ላይ ቀጭን እና ስለታም ድምፅ ‹‹ልዋጭ! ልዋጭ!›› እያለ ሲጮህ ነቃሁ። የዚህ ሰውዬ ድምፅ በዛሬ ቀን ከነገር ሁሉ ቀድሞማንበብ ይቀጥሉ…

‹‹ግን…. ባይሆንስ?››

  ቴድ ቶክ ማየት በጣም ደስ ይለኝ የለ? ከምሳ ሰአቴ ቀንሼ ነው የማየው…አፌን በምግብ፣ አእምሮዬን ደግሞ በጥሩ የቴድ ቶክ ተናጋሪዎች ታሪክ ስሞላ ፍስሃ ይሰመኛል። በሁለት በኩል መመገብ ነዋ! ዛሬ ያየሁት የዳያንን ነው። ዳያን ቮን ፈርነስተንበርግ (ስሟ መርዘሙ፣ ደግሞ ማስቸገሩ).. ዳያንማንበብ ይቀጥሉ…

የኩባያ ወተት ወይስ የኩባያ ውሃ?

ስመጥሩ የእስልምና ታሪክ ተመራማሪና ፀሃፊ አህመዲን ጀበል ለ‹‹ከመጋቢት እስከ መጋቢት›› በተቀረፁት አጭር ቪዲዮ ላይ የተጠቀሟት ታሪክ ደስ አለችኝና አመጣሁላችሁ። ታሪኳ እንዲህ ትላለች። አንድ መሪ ህዝቡ ምን ያህል እንደሚወደው ለማውቅ ፈለገና አደባባይ ላይ ትልቅ በርሜል አስቀምጦ ህዝቡን እንዲህ ብሎ አዘዘ። ‹‹የሚወደኝማንበብ ይቀጥሉ…

‹‹አብሮ አይሄድም››

  ለስብሰባ ከመጣች ኖርዌያዊት የስራ ባልደረባዬ ጋር የባጥ የቆጡን እየቀባጠርን ነበር። ኢትዮጵያንም አፍሪካንም ስታይ የመጀመሪያዋ ነው። ምሳ ደረሰና ቡፌው ጋር ስንሄድ፣ ገበታው የጸም እና የፍስክ በሚል መከፈሉን ስታይ ተከታታይ ጥያቄዎች አዘነበችብኝ። ‹‹ብዙ ሰው ይጾማል?›› ‹‹ምን ያህሉ ሰው ኦርቶዶክስ ነው?›› ‹‹ምንማንበብ ይቀጥሉ…

‹‹የድሬ ሰው ነፍሴ››

  የሚያንገረግበውን የድሬ ሙቀት መብረድ ጠብቄ አመሻሹን ሻይ ልጠጣና በእግሬ ወዲህ ወዲያ ልል ከሆቴሌ ወጣሁ።  ለብ ባለው ንፋስ እየተደሰትኩ፣ ቱር ቱር በሚሉት ባጃጆች ካለጊዘዬ ላለመቀጨት እየተጠነቀቅኩ ከተዘዋወርኩ በኋላ ለሻይ አንዲት ትንሽ ቤት ቁጭ አልኩና ምን ይምጣልሽ ስባል ‹‹ቀጭን ሻይ›› ብዬማንበብ ይቀጥሉ…

‹‹እታባዬ…እታባዬ!›› 

ባለፈው ሰሞን አንድ ቀብር ሄጄ ነው። ሟች፣ እታባ ጠና ያሉ ሴት ነበሩ። የእኛ ሰው ቀጠሮ የሚያከብረው ቀብር ሲሆን ብቻ አይደል? ምን ማክበር ብቻ? ቀድሞ ይጀምራል እንጂ! ያጣድፈዋል..ያዋክበዋል እንጂ! ስለዚህ ለስድስት ሰአት ቀብር መንገድ ተዘጋግቶብኝ እንዳላረፍድ ሰግቼ ከአምስት ሰአት በፊት ከቢሮማንበብ ይቀጥሉ…

‹‹በሃገር ነው››

ጎረቤቴ ካለው ቤተክርስትያን የሚመጣው የቅዳሴ ዜማ እና የወፎች ዝማሬ አነቃኝ። እንዴት ውብ አነቃቅ ነው! በሰላም አሳድሮ ይሄንን አዲስ ቀን ስላሳየኝ ምንኛ የታደልኩ ነኝ? ዛሬን ከማያዩት ስላልደባለቀኝ ምንኛ አድለኛ ነኝ? አልጋዬ ውስጥ እንዳለሁ ተንጠራራሁ። ሌላ ጊዜ ቅዳሜ እንደማደርገው አልጋ ውስጥ ስንደባለልማንበብ ይቀጥሉ…

‹‹ ባይተዋር›› (ክፍል ሁለት)

ምንድነው የሚያደርገው? ቀጥታ ወደ ኩሽና ሄዶ ከቢላዎች መሃል ትልቁን ቢላ መርጦ እየተምዘገዘገ አጠገቧ ደርሶ አትክልቶቿ ፊት እንደ አትክልት ይከትፋታል? የኔ አንጀት እንዲህ ነው የተበጠሰው ብሎ በቢላው አንጀቷን በጥሶ ያሳያታል? ልጆቿ /ልጆቻቸው ፊት ይገድላታል? አያደርገውም፡፡ ፊትለፊቱ የተቀመጠውን ትልቅ መስኮት የሚያህል ቴሌቪዥንማንበብ ይቀጥሉ…