(የታሪክ መዋቅር እና ሃሳብ- የቼታን ባጋት ‹‹ዋን ኢንዲያን ገርል››) እንደ እህቴ ቆንጆ አይደለሁም። ሕይወቴን ሙሉ በተደጋጋሚ የሰማሁት አንድ ነገር ቢሆን እንደ እህቴ ቆንጆ ያለመሆኔን ነው። የሁለት አመት ታላቄ ናት። ትምህርት ቤት እያለን ጀምሮ የአባትና የአያታችንን ስም ሰምቶ እስኪያረጋግጥ፣ አንድ ቤትማንበብ ይቀጥሉ…
ለእኔ ያላት እንጀራ (ክፍል ሁለት)
አንዱን ቅዳሜ መስፍኔ ቤት አድሬ ካልጋ ላለመውጣት እገላበጣለሁ። ጥሎኝ ሲወጣ ተገርሜ፣ – በናትህ ዛሬ እንደ ሮማን እና ፀጋዬ አልጋ ውስጥ እንበስብስ አልኩት። የበአሉ ግርማ በተለይ የኦሮማይ ፍቅሩ ሌላ ነው። ከአስራ አምስት ጊዜ በላይ እንዳነበበው ከአስራ አምስት ጊዜ በላይ ነግሮኛል። አልጋማንበብ ይቀጥሉ…
‹‹ለእኔ ያላት እንጀራ››
ሰው አይወጣልኝም። በሰላሳ ሰባት አመቴ ሕይወቴ ከጥቂት ሰዎች የተሰራ ነው። ሁለት በሰላሳዎቹ እድሜዬ ያገኘኋቸው የልብ የማይባሉ ጓደኞች፣ እናቴ፣ አባቴ፣ አንድ ግማሽ እህት (አባቴ ከእናቴ በፊት የወለዳት) እና ጊዜያዊ ወዳጆች። እግዜር ከሰጠኝ ሰዎች ውጪ የእኔ ብዬ ያቆምኩትና የፀና የረጅም ጊዜ ግንኙነትማንበብ ይቀጥሉ…
‹‹ዛሬ ቀኑ ምንድነው?››
(የታሪክ መነሻ ሃሳብ- የካሊድ ሆሴኒ ‹‹ዘ ካይት ረነር›› አንዲት ዘለላ ታሪክ (The Kite Runner- Khaled Hosseini) ተንበርክኬ ነበር። በዚያ የጥቅምት ውርጭ፣ ከምሽቱ አራት ሰአት ተኩል ላይ ከሰማይ በላይ እሪታዬን እያቀለጥኩ፣ ቀዝቃዛው አስፋልት ላይ ተንበርክኬ ነበር። በብርድ በሚንጫገጩ ጥርሶቼ መሃከል እጮሃለሁ።ማንበብ ይቀጥሉ…
‹‹ፀዲ››
(መነሻ ሃሳብ- የጁኖ ዲያዝ ‹ዘ ቺተርስ ጋይድ ቱ ላቭ›› አጭር ልቦለድ) ሰው ሁሉ ‹‹ፀዲና ሙሌማ ይጋባሉ። ተጋብተው አራት ልጅ ይወልዳሉ። አብረው ያረጃሉ። ተለያይተው መኖር ስለማይችሉ አንዳቸው ከሞቱ በነጋታው ሌላኛቸው ይከተላሉ›› የምንባል አይነት ነበርን። እኔና ፀዲ። ከተለያየን ሁለት ወራት ሞላን። መጀመሪያማንበብ ይቀጥሉ…
ወንጀል እና ቅጣት (ክፍል ሶስት)
አሳዘነችኝ። በጣም አሳዘነችኝ። ግን ደግሞ አስርባ ሄርሜላን እንድበላ ያደረገችኝ እሷ ናት በሚል ወልጋዳ ይሁን ትክክለኛ ሰበብ ፀፀት ሳይሰማኝ ቀረ። ገፍትራ ሄርሜላ ጉድጓድ የከተተችኝ እሷ ናት….ምናምን እያልኩ በመናገሬ ሳልፀፀት ዝም ብዬ የምትሆነውን አየሁ። ምናልባት የማላውቀው የልቤ ክፍል ለትዳር ዝግጁ ባለመሆኔ አላገባህምማንበብ ይቀጥሉ…
‹‹ፌዴራል ነፍሴ››
ረቡዕ አምስት ሰአት ገደማ ነው። ከጥንቃቄ እና ምቾት መዘነጥ በልጦብኝ ክፍትና ስፒል ጫማ አድርጌ …ቂቅ ብዬ ቀጠሮዬ ቦታ ደረስኩና ከመኪና ወረድኩ። ሲዘንብ አይደል ያረፈደው? የምሄድበት ህንጻ ውስጥ ለመግባት ጎርፉ እንዴት ያሳልፈኝ! በቀኝ ጎርፍ። በግራ ጎርፍ። ፊት ለፊቴ ጎርፍ። በጀርባዬማንበብ ይቀጥሉ…
‹‹ወንጀልና ቅጣት›› (ክፍል ሁለት)
…ኦ…ሄርሜላ! ለድርጅቱ በገንዘብ ያዥነት የተቀጠረች ሳይሆን ለኔ በፈተናነት የመጣች ትመስል ነበር። የሆነች እንከን አልባ ነገር። ሹ…ል እና ትልልቅ ጡቶች። ሙትት ያለ አንጀት። በቀጭን ወገቧ እህህህ…እያለች በመከራ የምትጎትተው ትልቅ ቂጥ። ስስ ግን ሳሙኝ፣ ግመጡኝ የሚል ከንፈር። ሄርሜላ…. ፈተናዬን ሲያበዙት ፊልድ በሄድኩማንበብ ይቀጥሉ…
‹‹ወንጀልና ቅጣት›› (ክፍል አንድ)
እትዬ ሌንሴ ፊት ነሱኝ። ለወትሮው ከፊልድ ምናምን ስመለስ እንኳን ኬሻ ሙሉ ከሰል፣ ሶስት አራት ኪሎ ቲማቲም ወይ ሽንኩርት ወይ ደግሞ ጎመን ምናምን ይዤ መጥቼ የመኪናዬን ጲጵ ሲሰሙ ጠብ እርግፍ ብለው ያስተናግዱኝ ነበር። ቤት ያፈራውን ጭኮ፣ ቅንጬ ወይም ፍርፍር በፍጥነት አቅርበውማንበብ ይቀጥሉ…
‹‹መልካም ጋብቻ››
ከጓደኞቼ ማህደርና እስከዳር ጋር፣ ያቺ በረባሶ ከሚሰራበት ጎማ ጫማ ሰርታ ሸጣ እስካሁን በማይገባኝ ፍጥነትና ሁኔታ ሚሊዮነር የሆነችው ሴትዮ…ማነው ስሟ ? እ……ቤተልሄም… እሷ አዲስ ከከፈተችው ዘናጭ ካፌ ቁጭ ብለን ውድ ማኪያቶ እየጠጣን ነበር። ማኪያቶው አሪፍ፣ ጨዋታው ደማቅ ነበር። መርዶዬን እስኪነግሩኝ…‹‹ናሆምና ማርታማንበብ ይቀጥሉ…