ትላንት ማታ ክፉ ነገር ተፈጠረ። መልከ መልካሙ እና ገራገሩ እጮኛዬ ላይ ማገጥኩበት። ያች በልጣጣ ጓደኛዬ ትዕግስት ናት እዚህ ሁሉ ጣጣ ውስጥ የከተተችኝ። ሁሌም ለሰኔ ሚካኤል ቤቷ ድል ያለ ድግስ ታዘጋጃለች። የምታውቀውን ሰው ሁሉ ትጋብዛለች። ከልክ በላይ ታበላለች። ከመጠን በላይ ታጠጣለች።ማንበብ ይቀጥሉ…
ስንት ጊዜ ሆናችሁ?
መሃል አዲስአባ…ሸገር ላይ እያላችሁ.. የእንቁራሪቶች ድምፅ በደንብ ከሰማችሁ በክር የታሰረ ጢንዚዛ ካያችሁ የማርያም ፈረስን መንገድ ካገኛችሁ በእፉዬ ገላ ‹‹ያዘኝ አትያዘኝ›› ከተጃጃላችሁ… ስንት ጊዜ ሆናችሁ? ሱዚ የሚዘሉ ፔፕሲ የሚራገጡ ሸክላ እየፈጩ በርበሬ ነው የሚሉ ሙሽራ ሙሽራ – እቃ እቃ እቃ እቃማንበብ ይቀጥሉ…
አንድ ላይ ብንሆንም ተለያይተናል…
ትላንት ከአንዷ ጓደኛዬ ጋር ምሳ ለመብላት አንዱ ምግብ ቤት ቁጭ ብለናል። ምግቡን እየጠበቅን የተገናኘንበትን ብርቱ ጉዳይ ስንወያይ፣ አራት አለባበሳቸውና ነገረ ስራቸው ሁሉ ሃያዎቹን ከጀመሩ እንዳልቆዩ የሚያሳብቅባቸው ወጣቶች መጡና አጠገባችን ያለውን ጠረጰዛ ከበው ተቀመጡ። በእነሱና በእኛ መሃከል ያለው ርቀት በጣም ቅርብማንበብ ይቀጥሉ…
“ሌጋሲዬ”
እስቲ ዛሬ በጥያቄ ልጀምር። ከመሬት ተነስቼ “ አልፍሬድ ኖቤል” ብል መጀመሪያ ወደ አእምሯችሁ የሚመጣው ምንድነው? ለብዙዎቻችን መልሱ ‹‹ዝነኛው የኖቤል ሽልማት ነዋ!›› ይሆናል ብዬ እጠረጥራለሁ። ከዚያ ሁሉ በፊት ግን ይሄ ገናና ሽልማት በየአመቱ በስሙ የሚሰጥለት አልፍሬድ ኖቤል ስራው ምን ነበር? መተዳደሪያውስ?ማንበብ ይቀጥሉ…
‹‹የኤንሪኮ ኬክ ፍርፋሪዎች…››
አራት ኪሎ ሮሚና ተቀምጬ ኮካዬን ስመጠምጥ የሚያስደነግጥ ነገር አየሁ። ጌትሽ! ጌትሽ አምሮበት። ጌትሸ ከሌላ ሴት ጋር እጅ ለእጅ ተያይዞ አየሁት። የድሮ ፍቀረኛዬ ነው። እየወደድኩ የተለየሁት። ተለይቼ እቅፉን፣ ገላውን፣ ፍቅሩን እየናፈቅኩ የምኖር የድሮ ፍቅረኛዬ። በፍቅረኛ ደንብ ሶቶ ለሶቶ ተያይዘው ወደ ተቀመጥኩበትማንበብ ይቀጥሉ…
እጅ በጆሮ
ማምሻውን ነው። ዝናብ ያረሰረሰውን የሰፈራችንን ኮብልስቶን መንገድ በጥንቃቄ እየረገጥኩ ወደ ቤቴ አዘግማለሁ። በድንጋዮቹ መሃከል የፈሰሰው ውሃ በረገጥኩት ቁጥር ፊጭ ፊጭ ይላል። ዘንቦ ማባራቱ ስለሆነ ይበርዳል። ፊጭ ፊጭ እያደረግኩ መራመዴን ስቀጥል፣ ከዚህ በፊት አይቼ በማላውቀው ሁኔታ በመንገዴ ላይ ከሰል አቀጣጥለው፣ በቆሎማንበብ ይቀጥሉ…
የኬዱክ እጆች
( ማሳጅ በባሊ፣ ኢንዶኖዢያ) -የቱሪስት ሃገር ስለሆነ ኑሮ እሳት ነው…እኔ ደግሞ ደሞዜ በጣም ትንሽ ነው። በወር ሁለት ነጥብ ሶስት ሚሊዮን ይከፍሉኛል ግን አይበቃኝም…የቤት ኪራይ ዘጠኝ መቶ ሺህ እከፍላለሁ… ኬዱክ ናት እንዲህ የምትለኝ። ኬዱክ በስመጥሩ ሆቴል ውስጥ ያለ ዝነኛ የስፓ አገልግሎትማንበብ ይቀጥሉ…
”የቱ ይበልጣል?“
ዛሬ ነው። የቀጠርኩት ሰው እስኪመጣ ፣ ከከተማችን ቅንጡ የገበያ ማዕከሎች በአንዱ ውስጥ ያለ ግብ እዞራለሁ። ለድሪቶነት ለሚቀርብ ሱሪ የሃምሳ ኪሎ ጤፍ ሂሳብ የሚያስከፍሉ ሞልቃቃ ቡቲኮች። ርካሹ ኬክ በ 40 ብር የሚሸጥባቸው ካፌዎች። አምስት ካሬ የማይሞላ የቄንጠኛ የግድግዳ ወረቀት ጥቅልን በሺህማንበብ ይቀጥሉ…
ባለ ከረሜላው ሰውዬ
ቢሮ ሆኜ ከስራ ፋታ ሳገኝ ማረፊያዬ ዩ ቲዩብ ነው። የድሮ ዘፈን እየጎረጎርኩ አዳምጣለሁ። ዛሬ ጠዋት የ80ዎቹ እና 90ዎቹን አር ኤንድ ቢ ሙዚቃዎች እየሰማሁ ሳለ የልጅነት አእምሮዬ ላይ ተነቅሶ ከቀረ አንድ ዘፈን ጋር ተገናኘን። ርእሱ ‹‹ካንዲ ሊከር›› ዘፋኙ ማርቪን ሴስ ይባላል።ማንበብ ይቀጥሉ…
“ይሸታታል”
ለምኖርበት ህንፃ የፅዳት ተጠሪ ስለሆንኩ በየወሩ እየዞርኩ ለሠራተኞች የሚከፈለውን ደሞዝ መዋጮ እሰበስባለሁ። ቅዳሜ እንደተለመደው እየዞርኩ የአንዷን ጎረቤቴን አፓርትማ አንኳኳሁ። ከፈተች። ከእሷ ቀድሞ ከቤቷ ውስጥ የወጣው ትኩስ እንጀራ ሸታ አወደኝ። የትኩስ እንጀራ ነገር አይሆንልኝም። ቁንጣን ይዞኝ ‹‹ማር እንኳን አልልስም›› ብዬማንበብ ይቀጥሉ…