ከእኔ በፊት ሁለት ሚስት አግብቶ እንደነበር ሳላውቅ አይደለም ያገባሁት። አውቅ ነበር። ለሁለቱም ሚስቶቹ ልክ ከእኔ ጋር እንዳደረገው የሀብት ውርስ ኮንትራት አስፈርሟቸው እንደነበርም አልደበቀኝም ነበር። በፍቅሩ ነሁልዬ ከእኔ በፊት የነበረው ህይወቱ ገሀነም እሳት ጭስ ሳይሸተኝ ቀርቶም አይደለም። ወይም ፍቅሬ አቅሉን አስቶትማንበብ ይቀጥሉ…
ሰይጣን ወይ እግዜር የጀመሩት… እኔ የቀጠልኩት (ክፍል አንድ)
«ሞቼ ቢሆን ኖሮ ደስ ይልሽ ነበር አይደል?» አለኝ በወጉ ማሽከርከር ያልለመደውን ዊልቸር እየገፋ ወደሳሎን ብቅ እንዳለ። ፊቱ ምሬት ወይ ጥላቻ በቅጡ ያልለየሁት ስሜት ይተራመስበታል። ዝም ያልኩት መመላለሱ ልቤን ስለሚያደክመኝ ነበር። በጎማው እየተንቀራፈፈ አጠገቤ ደርሶ « ንገሪኛ ደስ ይልሽ ነበር አይደል?»ማንበብ ይቀጥሉ…
“መዶሻህን ብላው”
ወዳጄ (Netsanet) እንደነገረኝ ሰውዬው እሁድ ቀን እቤቱ ጋደም ብድግ ሲል ይቆይና ግድግዳው ላይ የተነቀለች ሚስማር አይቶ ሊመታት ቢፈልግ መዶሻ ያጣል። ጎረቤቱን ሊጠይቀው በሩጋ ከደረሰ በኋላ «ተኝቶ ቢሆንስ» ብሎ ይመለሳል። እቤቱ ከመድረሱ በፊት ግን «እህ የተኛ እንደሆነስ? መዶሻውን ከሰጠኝ በኋላ ተመልሶማንበብ ይቀጥሉ…
የጥልቁ ትንታኔ
በቀደም ስለሉሲፈር ፊልም በፃፍኩት ፅሁፍ ስር አንዱ “ትውልዱን በማር የተለወሰ መርዝ እያስነበብሽው ነው” ብሎኝ ሳቅቼ ሞተውት። እናውራ እንዴ? የትኛውን ትውልድ? ይሄ ትውልድ ቲክ ያላደረገው የሉሲፈር ስራ አለ ነው የምትሉኝ? ይሄ የኔ ዘር አይደለህም ብሎ ወንድሙን ዘቅዝቆ የሚሰቅለው ትውልድ ሉሲፈር እሩቁማንበብ ይቀጥሉ…
“lucifer”
በራሴ ጉዳይ ተንበርክኬ የፀለይኩበት ቀን በጣም እሩቅ ነው። እውነት ለማውራት ከጠየቅኩት በላይ የማይገባኝ ሁላ የተሰጠኝ ሰው ነኝና ብዙም ጥያቄ የለኝም! ከፍቶኝ ፊቱ የቀረብኩባቸውንም ቀናት formal ፀሎት የፀለይኩባቸው ቀናት በጣም ድሮ ናቸው። አጠገቤ ሆኖ እንደሚሰማኝ እነጫነጫለሁ። «ከዚህ በላይ መሸከም እንደማልችል አታውቅም?ማንበብ ይቀጥሉ…
የቀይ ልክፍት
“ጥሬ ስጋ በቀይ ወይን ምሳ ልጋብዝሽ” ብሎ ነው የጀመረኝ። “በደስታ” አልኩኝ። ጥሬ ስጋ ነፍሴ እንደሆነ ማንም ያውቃል።…… “ምሳ በልቼ አሁን መጣሁ” ብዬ ከቤት ወጥቼ የሚቀጥለውን ቀን ምሳ በልቼ ተመለስኩ። በቁርጥ ሰበብ ስንቋረጥ ዓመት ሆነ።…… “ሜዬ ገብቶልሻል ይሄ ልጅ! “ይሉኛል ጓደኞቼ……ማንበብ ይቀጥሉ…
ሁለቱ ባሎቼን ላስማማ እያሸማገልኳቸው ነው (ክፍል 11 – የመጨረሻ ክፍል)
ሁለቱ ባሎቼን ላስማማ እያሸማገልኳቸው ነው (ክፍል 11 የመጨረሻ ክፍል) እንደዛ ከደነፋ ከቀናት በኋላ የተመራቂ ተማሪዎች ፓርቲ አዘጋጅተን ዝግጅቱ የነበረው ከተማ ነበር። ልንመረቅ ሁለት ወር ነበር የቀረን። እኔን ብሎ ደግሞኮ ተተራማሽ። መግቢያ ትኬት ምናምን እየሸጥኩ ስተራመስ ከርሜ የፓርቲው ቀን ጠዋት ከጓደኞቼጋማንበብ ይቀጥሉ…
ሁለቱን ባሎቼን ላስማማ እያሸማገልኳቸው ነው (ክፍል አስር)
14ማለትሽ አይቀርም ነበር። በእርግጥ እንደወሰለተ ነው እንጂ የነገራት ሌላ ጣጣችንን አልነገራትም። መፅሃፍ ቅዱሱ እንኳን ፍቺን የሚፈቅድበት ብቸኛ ምክንያት ውስልትና መሆኑን እያወቀች። እሱን አልፋ ስለይቅርታ ስትሰብከ አመሸች። “ውይ አንጀቴን በላው! ሌላ መሄጃ የለኝም …. ጉዴን ልንገርሽና እንደፈለግሽ አርጊኝ ብዬ ነው አንቺጋማንበብ ይቀጥሉ…
ሁለቱን ባሎቼን ላስማማ እያሸማገልኳቸው ነው (ክፍል ዘጠኝ)
ከሁሉም ከሁሉም ምኑ ያስጠላል መሰለሽ? ራስሽን ባልሽ ካባለጋት ሴት ጋር ማነፃፀር …… መድቀቅ የምትጀምሪው እዚህጋ ነው …… ራስሽን ከሆነ ሰው ጋር ማነፃፀር ስትጀምሪ በራስ መተማመንሽ እየተምዘገዘገ ይፈጠፈጣል። ከዛ በፊት ከማንም በልጣለሁ ወይም ከማንም አንሳለሁ ብዬ ራሴን ከማንም አወዳድሬ አላውቅም እራሴንማንበብ ይቀጥሉ…
ሁለቱን ባሎቼን ላስማማ እያሸማገልኳቸው ነው (ክፍል ስምንት)
‘ጊቢ ግቡ’ እስኪባል ድረስ ምን መወሰን እንዳለብኝ ግራ ገባኝ። ማንም FBE በLAW እንደማይቀይረኝ እያወቅኩ ሞከርኩ። ላለመማርም አስቤያለሁ። ከዛ ልጄን ይዤ የሆነ ቦታ እልም ብዬ መጥፋት ……. ማንም የማያውቀኝ ቦታ ሄጄ ከዜሮ መጀመር። በእኔ እልህ ልጄን ማስከፈል የማይታሰብ ነው። እጅ መስጠትምማንበብ ይቀጥሉ…