“ከእኔና ከርሷ ምረጥ ብትባል?” “ደሞ ጀመረሽ …. ተይ ኤዱ እረፊ…. ” “ንገረኝ… ምን መስማት እንደምፈልግ ታውቃለህ!! … ንገረኝ!!” እጮሃለሁ … በጥፍሬ ቆዳውን እጫነዋለሁ …. ሚስቱ(እህቴ) ሰውነቱ ላይ ምንም ምልክት እንድታገኝበት አይፈልግምኣ … “አንቺ!!.. አንቺ ትበልጫታለሽ!” ይለኛል። ከሚስቱ ንፁህ ልብ እናማንበብ ይቀጥሉ…
አልወዳትም እንጂ አልጠላትም (ክፍል አንድ)
ሞታ የለቅሶ ድንኳኗ ውስጥ የተነጠፈው ፍራሽ ላይ ተቀምጬ ሊቀብሯት በሳጥን አሽገው ጥጉ ላይ አስቀምጠዋት ሲላቀሱ የማስበው ‘አልወዳትም እንጂ አልጠላትም’ …. የሚለውን ነው… በሃሳቤ መሃል ከቤተሰብ ወይ ከወዳጅ አንዱ ሲያፈጥብኝ “ወይኔ እህቴን .. ወይኔ እህቴን … ትተሺኝ አትሂጂ ..” እሪታዬን አቀልጠዋለሁማንበብ ይቀጥሉ…
እኔን የሆነው ማነው?
አመድ አፋሽ መሆኔን ነግሬያችኃለሁ?🤣 የምሬን ነው ያበደርኩት ሰው ‘ብሩን ከምፈልገው ሰዓት ሶስት ደቂቃ ዘግየብኝ’ ብሎ የሚቆጣኝ ሰው ነኝ 🤣 ሰርጉን: ውልደቱን… ደስታውን ሁሉ ከሌሎች ወዳጆቹጋ ሲፈነጥዝ ያላስታወሰኝ ወዳጅ ‘ለሀዘኔ ያነባሽው እንባ ሀያ ስድስት የእንባ ዘለላ ከግማሽ ነው.. በደንብ አላላቀስሽኝም’ ብሎማንበብ ይቀጥሉ…
የአባዬ መደረቢያ
ያኔ …ከዛ ከኛ ቤት ከባሰ አመዳም ደሃ ጎረቤታችን ቦቸራ ሳረግዝ…… ለአባዬ ውርደቱ ሆንኩ። በየሴሚስተሩ አንደኛ እየወጣች ስሙን የምታስጠራው ልጁ በአንድ ቀን ስህተት አፈር ከድሜ ገባች። … ወራት ነጎዱ… ትምህርቴን ከ11 ተውኩት። ልጄን ገጠር አክስቴጋ ሄጄ ወለድኩ።…… የአባዬ ውርደት የነበረው ሌባውማንበብ ይቀጥሉ…
ሞካሪና አስሞካሪ
(ማስጠንቀቂያ …. አልባሌ ነገር የማትወዱ ሰዎች አታንብቡ … ኡኡኡኡኡ .. 🙆🏻♀️🙆🏻♀️ይሄን አልፋችሁ ካነበባችሁ እንዳትመክሩኝ) “ከንፈር መሞከር ፈልጋለሁ።” አልኩት “እስከዛሬ ተስመሽ አታውቂም።?” “እስከዛሬ ፈልጌ አላውቅም።” ከንፈሩን አቀበለኝ። ወራት ነጎዱ…… “ድንግል መሆን አልፈልግም።” አልኩት “ገናኮ 18 ዓመትሽ ነው ማሬ። ለምን ትንሽ አንቆይም?ማንበብ ይቀጥሉ…
ባሌ እንዳመነዘረብኝ ባወቅኩ ጊዜ (ክፍል ሰባት)
“አልቻልኩም። …. አልቻልኩም!” ሁለት እጆችዋን ጨብጣ ደረቴን እየደበደበች ታለቅሳለች። ጉንጮቿ እና ከንፈርዋ ይንቀጠቀጣሉ። አንጀት የራቀው ሆድዋ ይርበተበታል። እየደጋገምኩ “እሺ” ከማለት ውጪ የምለው አጣሁ። ድብደባዋን ስታበቃ ንፁህ ያልሆነው መሬት ላይ በነጭ ሱሪዋ ተቀመጠች። “ላናግርህ እፈልጋለሁ” ብላ ሱቋ ጠርታኝ ነው ሱቁን ዘግታማንበብ ይቀጥሉ…
ባሌ እንዳመነዘረብኝ ባወቅኩ ጊዜ… (ክፍል ስድስት)
“እስክትወስን እጠብቃታለሁ።” ይለኛል። ሁሌም የምንገናኝበት ቦታችን ‘የምናውራው አለ’ ብሎኝ ተገናኝተኝ የጀበና ቡናችንን እየጠጣን። “እኔስ? በፍቅርህ የነሆለለ ጅል ልቤስ? ምን ላድርገው? እስከመቼ ጠብቅ ልበለው? ከሚስቱ እስኪታረቅ ልበለው እስኪለያይ? ንገረኝ የቱን ነው የምጠብቀው?” እንባዬ የአይኔን ድንበር አልፎ ተንዠቀዠቀ። ይሄን ያልኩት ብዙ ስለሷማንበብ ይቀጥሉ…
ባሌ እንዳመነዘረብኝ ባወቅኩ ጊዜ… (ክፍል አምስት)
“እናውራ? ማውራት አለብን!” አለኝ አምስት ለሊቶች ሳይነካካኝ አቅፎኝ ካደረ በኋላ። አምስት ጠዋቶች ከንፈሬን ሳይስመኝ ደህና ዋዪ ካለኝ በኋላ። አምስት አመሻሾች ደረቱ ላይ አቅፎ ግንባሬን ሳይስመኝ እንዴት ዋልሽ ካለኝ በኋላ…. “Finally” አልኩኝ ይህን እንዲለኝ ስጠብቅ እንደነበር በደንብ እያሳበቅኩ “እንዴ? እንድናወራ እየጠበቅሽማንበብ ይቀጥሉ…
ባሌ እንዳመነዘረብኝ ባወቅኩ ጊዜ… (ክፍል አራት)
ባሌን እንዲህ እፍፍፍ ያስደረገችውን ሴት ለማየት “የተለመደ” ቦታቸው ባሌን ተከተልኩት። ከስራ እኔን እቤት ካደረሰ በኋላ ነው የወጣው። የጀበኛ ቡና የሚሸጥበት ቤት? ይሄ ነው የተለመደ ቦታቸው? መኪናውን አቁሞ ወረደ። ታክሲውን አስቁሜ በዓይኔ ተከተልኩት። ከተቃራኒ አቅጣጫ እየመጣች ከነበረች ሴት ጋር በፈገግታ ተጠባበቁ።ማንበብ ይቀጥሉ…
ባሌ እንዳመነዘረብኝ ባወቅኩ ጊዜ… (ክፍል ሦስት)
“ልጅ ልሰጥሽ ስለማልችል ትተይኛለሽ?” አለኝ “ስንጋባም መውለድ እንደማትችል ታውቅ ነበር?” “አዎ ” “ለምን አልነገርከኝም?” “እንዳላጣሽ ፈርቼ። ብነግርሽ ኖሮ ታገቢኝ ነበር?” “ምርጫ አልሰጠኸኝምኮ! ከልጄና ከፍቅርህ እንድመርጥ ምርጫ አልሰጠኸኝም! ራስህን ራስህ መረጥክልኝ!! ” “እኔ ብሆን ልጅ አልሰጠሽኝም ብዬ አልተውሽም! ይሄን የሚሻገር ፍቅርማንበብ ይቀጥሉ…