ራሴው ማበዴ ነው (ክፍል ሰባት)

“ይሄ ኬዝ እንዲህ ቀልብሽን የሳበው የትኛው ነጥብ ነው? ግልፅ ማስረጃ ነው የተያዘባት። ራሷም ድርጊቱን መፈፀሟን አምናለች።” “ፍትህ ሰዎቹን ፈራሃቸው እንዴ?” “በፍፁም ፈርቼ አይደለም። ከእነሱ ጋር ስለመያያዙም ገና መላምት ነው ያለሽ።” ከፍትህ ጋር ሻይ እየጠጣን እየተነጋገርን ያለነው ስለትዝታ ነው። ትዝታ የ23ማንበብ ይቀጥሉ…

ራሴው ማበዴ ነው (ክፍል ስድስት)

እናቴ ከመሞቷ በፊት ልውልላት የምችለው አንድ ውለታ አባቴ እንዲያገኛት ማድረግ ነው። ቢያንስ የዘመናት ፍቅሯን እጁን ዳብሳ ደስተኛ ሆና ትሞታለች። እናቴን ማጣት ማሰብ አልፈልግም። የባሰው ደግሞ ስትለየኝ ማን መሆኔን እንኳን ሳታውቅ እብደቷ ተነስቶባት መሆኑን ማሰብ ያሳብደኛል። ያ እንዲሆን አልፈልግም። የቀራትን ጊዜማንበብ ይቀጥሉ…

ራሴው ማበዴ ነው (ክፍል አምስት)

“ራሔል ከዚህ በላይ እናትሽን እቤት ልታቆያቸው የምትችዪ አይመስለኝም። አደገኛ ነው የሚሆነው።” “ዶክተር በፍፁም ሆስፒታል እንደማልተዋት ቃል ገብቼላታለሁ። አይሆንም!! ታውቅ የለ ምን ያህል እንደምትጠላ?” “ራሔል እስቲ ተቀመጪ።” አለኝ ወንበሩን እያሳየኝ። በእማዬ ምክንያት ከማውቀው ልምድ በዶክተሮች አባባል ‘እስኪ አረፍ በይ፣ እስኪ ተቀመጪ፣ማንበብ ይቀጥሉ…

ራሴው ማበዴ ነው (ክፍል አራት)

“ልትነግሪኝ የምትፈልጊው ነገር አለሽ?” “ማለት? ስለምን?” “እኔ እንጃ ቦስ አባትሽ እዚህ ቢሮ እግራቸው ከረገጠ ቀን ጀምሮ ላለፉት ሁለት ሳምንታት ፍፁም ልክ አይደለሽም። ያዘንሽ ያዘንሽ ፣ የተከፋሽ ፣ የሆነ ነገር ያደከመሽ አይነት ነው የምትመስዪው።” ሲለኝ ለቅፅበት ያደከመኝን ሁሉ ልነግረው ዳድቶኝ ነበር።ማንበብ ይቀጥሉ…

ራሴው ማበዴ ነው (ክፍል ሦስት)

ከሀያ ዓመት በላይ የሆናቸው በወጣትነቷ ውዷ ከፃፈላት ደብዳቤዎች ዛሬም ድረስ አብረዋት ያሉ እያንዳንዱን በቃሏ የምታውቃቸው 23 የፍቅር ደብዳቤዎች አሏት። ሁሉንም ከነተፃፉበት ቀን ሳይቀር እኔም በቃሌ አውቃቸዋለሁ። እንደዚህ ከፍ ያለ ፍቅር መቋጫው እንዴት አስከፊ መለያየት እንደሆነ ሳስብ ይገርመኛል። እሷ ዛሬን ማሰብምማንበብ ይቀጥሉ…

ራሴው ማበዴ ነው (ክፍል ሁለት)

“አቤት?” አልኩት ለሰላምታ የዘረጋውን እጁን ችላ ብዬ ወንበሬ ላይ እየተቀመጥኩ። ፀጉሩ አልፎ አልፎ ከመሸበቱ ውጪ ብዙም አልተለወጠም። “ደህና ነሽ ሚሚሾ?” “ምን ፈልገህ ነው የመጣኸው? ደህና መሆኔ አሳስቦህ አይሆንም መቼም!! የልጅህ ሰርግ ጥሪ ወረቀት እንደደረሰኝ ለማረጋገጥ ከሆነ ደርሶኛል። እማም ደርሷታል። ጨርቄንማንበብ ይቀጥሉ…

ራሴው ማበዴ ነው

“ተሳፋሪዎቻችን ይህ የበረራ ቁጥር 206 ነው… … ” ጭንቅላቷ እየሸወዳት እንደሆነ የማውቀው እንዲህ ማለት ስትጀምር ነው። በግልቡ እብደቷ እየጀመራት ነው ማለት ነው። እናቴ ናት!! ይሄን ሀረግ ማለት ከጀመረች ትርጉሙ የዛሬ 20 ዓመት ወደ ኋላ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሆስተስ የነበረችበት ዘመንማንበብ ይቀጥሉ…

እኔና አንቺ

“አንተ ሴሰኛ አይደለህም።” ትዪኛለሽ። ሴሰኝነት ‘ስሜ’ መሆኑን አንቺም፣ እኔም፣ ከጎኔ የሚሻጡት ሴቶችም፣ እኔን የሚያውቁኝም ሁሉ እናውቃለን። ለራሴ ‘ያለማወቅሽን እና የዋህነትሽን’ ነገርኩት። ላንቺ ግን ዓይኖቼንም ልቤንም የጠለፈውን ህልም የመሰለ ውበት ያለው አካልሽን እያየሁ ጥርሴን ለመግለጥ ከንፈሬን አሸሸሁልሽ …….. ሚስጥር አዘል ወጋገንማንበብ ይቀጥሉ…

አባቴ አክተር ነው!!

“ሜዬ በናትሽ እኔ ልብላው? እሷ ታባክነዋለች።” እንዲህ የምትለኝ እህል እንዳይመስላችሁ። ወንድ ጓደኛዬን ነው። አቢቲ የወንድ ቀበኛ ናት። ‘እሷ’ ያለቻት ሀይሚን ነው። ሀይሚ አብራን የምትኖር የእኔም የእሷም የጋራ ጓደኛችን ናት። አቢቲ ደግሞ የአክስቴ ልጅ ናት። አቢቲ እንደምትለው ሀይሚ ወንድ ታባክናለች። እናምማንበብ ይቀጥሉ…

የመጨረሻው የአድዋ ውሎ

እየቆየ ዝነኛ የሆነውና በኢትዮጵያም ታሪክ ውስጥ ምናልባት ከሁሉም የላቀው የአድዋ ጦርነት የተጀመረው በመጋቢት 1 ቀን 1896 ዓ.ም (እ.ኤ.አ) ከማለዳው ላይ ነበር። በዚህ ጦርነት የተሰለፉት ዋና ዋና ጀግኖች ራሱ ንጉሠ ነገሥት ምኒልክ፣ ንግሥት ጣይቱ፣ ፊታውራሪ ገበየሁ፣ ንጉስ ተክለ ሀይማኖት፣ ራስ ወሌ፣ማንበብ ይቀጥሉ…