ግጥምና ገድል (ቅፅ 1)

“ከመዳኒት ፍቱን ወሸባና ኮሶ ከሰው መልካም ባልቻ : ከፈረስም ነፍሶ” ከላይ የጠቀስኩት ለስመጥሩው አርበኛ ለደጃዝማች ባልቻ ከተዘመሩት ግጥሞች አንዱ ነው። አዝማሪው ባልቻን ሲያሞጋግስ እግረመንገዱን ስለኖረበት ዘመን የህክምና ታሪክ ነግሮናል ። ስለኮሶ ምንነት ለማብራራት የሚጠበቅብኝ አይመስለኝም። “ወሸባ ” የሚለውን ቃል ትርጉምማንበብ ይቀጥሉ…

እኔም!

ስሜት አልባ ነህ ብለሽኝ፣ «አልነበርኩም» ብዬሻለሁ። እውነቴን ነው። የስሜቴን ጅረት ያደረቀችው ቀድማ የሄደችው ነበረች። ታሳዝኚኛለሽ። ያለፈ ህይወቴ ትመስይኛለሽ። ላፈቅርሽ ሞክሬያለሁ። ሳይሆንልኝ በራሴ እልፍ ጊዜ ተበሳጭቻለሁ። ትታኝ የሄደችውም እንዲህ የነበረች ይመስለኛል። «አፈቅርሃለሁ» ብላኛለች። ግን አታፈቅረኝም ነበር። ልታፈቅረኝ እየሞከረች እንደነበር ግን አውቃለሁ።ማንበብ ይቀጥሉ…

“ኦሮማይ” እና በዓሉ ግርማ

ኦሮማይ ከልቡ መጽሐፍ ነው። በአማርኛ ልብ-ወለድ መጻሕፍት (Novel) ታሪክ በጣም አነጋጋሪውና አከራካሪው መጽሐፍ ነው። እስከ አሁን ድረስ የህዝብ ፍቅር ካልተነፈጋቸው ጥቂት መጻሕፍት አንዱም ነው። በህይወቴ ብዙ ጊዜ እየደጋገምኩ ካነበብኳቸው መጻሕፍት መካከልም በመጀመሪያው ረድፍ ይሰለፋል። ይሁንና ሰዎች ለዚህ መጽሐፍ ያላቸው አድናቆትማንበብ ይቀጥሉ…

Butterfly Effect

ተተንባይ ኑረት የሌላቸውን ሁነቶች የሚተነትነው ሒሳባዊ ንድፈ-ሃሳብ Chaos Theory ይባላል… ትወራው በዚህ ስም ከመጠራቱ በፊት መገለጫ ባሕሪያቱን ለመተንተን የመጀመሪያ ነው የሚባልለት የሒሳብ ሊቅ Henri Poincaré ይባላል… ፈረንሳዊ ነው… “It may happen that small differences in the initial conditions produce veryማንበብ ይቀጥሉ…

ችግሩን ከመሠረቱ ለመፍታት ስንት ወልድያ ያስፈልገናል?

የጸጥታ ኃይሎች በወልድያ ነዋሪዎች ላይ የፈጸሙት ግድያ በምንም ዓይነቱ መመዘኛ ከውግዘት የሚያመልጥ አይደለም። በአንድ በኩል ‹ጸረ መንግሥት ዝማሬ ያሰሙ ነበር›፣ በሌላ በኩል ደግሞ ‹ድንጋይ ይወረውሩ ነበር› የሚሉት ምክንያቶች የጸጥታ ኃይሎች በሕዝብ ላይ ጥይት እንዲተኩሱ የሚያበቁ ሕጋዊና ሞራላዊ ምክንያቶች አይደሉም። ማንኛውምማንበብ ይቀጥሉ…

ከያስተሰርያል በላይ እንደሚወደን አሳይቶናል

The other side of Teddy Afro >Leadership Quality ….ከያስተሰርያል በላይ እንደሚወደን አሳይቶናል #ባህር_ዳር የዛሬ አራት አመት አዲስ አበባ ላይ እንዲህ ብሎን ነበር ቴዲ:- #ግዮን_ሆቴል ህዝብ ያስተሰርያል እንዲዘፈን የነበረውን ጉጉት አይቶ ቴዲ እንዲህ ብሎ ጠይቆ ነበር “ያስተሰርያል ስድብ ነው እንዴ ? ” ቴዲማንበብ ይቀጥሉ…

ሰሙነኛው

አንድ በገጠር የሚኖር እረኛ አባቱን ትምህርት ቤት እንዲያስገባው ይጠይቀዋል። አባትየው ደግሞ ልጁ ከብት እንዲያግድ እንጂ ትምህርት እንዲገባ አልፈለገም። ታዳጊው አባቱን በተደጋጋሚ ቢጨቀጭቅም ሊሳካለት አልቻለም። በኋላ ላይ አንድ ዘዴ መጣለት ‘ጥሩ ከብት ጠባቂ አይደለም’ ለመባል ሲል፤ ቀኑን ሙሉ ግጦሽ ላይ አሰማርቶማንበብ ይቀጥሉ…

‹‹ነገ ዛሬ ይሆን››

እንግዲህ ጅማሬው ከሆነ ከአንጀታችሁ ‹‹እናዳምጣለን….ንገሩን›› ካላችሁ… የይስሙላ፣ የእድሜ ማራዘሚያ፣ የጥገና እና ተንፏቃቂ ለውጥ አንፈልግም። ጉልቻው እንዲቀያየር፣ ሽንቁር የበዛበት ግድግዳ ቀለም ፣ አሳማው ሊፕሰቲክ እንዲቀባ አንሻም። ባረጀ እና ያፈጀው ‹‹ተሃድሶ›› ሀረግ ዳግም መደለል፣ ዳግም መታለል አንፈልግም። የ‹‹ተጨፈኑ ላሞኛችሁ›› ፖለቲካ አንገሽግሾናል። የዘመናት‹‹እድሳትማንበብ ይቀጥሉ…