ስሚ!

ስሚ መስሚያ ካለሽ። ከሰማሽ ደሞ ተስማሚ፤ ወዲያ ሂጂልኝ እስቲ። ማነሽ እውነት ነኝ የምትይ፣ እስቲ ስሚን የስንቱን አለመስማት እንችላለን? መንግስት አይሰማን፣ ፈጣሪ አይሰማን፣ አንቺ አትሰሚን… ኸረ እስቲ አንቺ እንኳን?!! ማን ነበረ ስምሽ? “እውነት ” ነው አይደል? እውነቱን ልንገርሽ፣ በደረስኩበት ባትደርሺ ደስማንበብ ይቀጥሉ…

የዚህ ትውልድ አባል ነኝ!

በመውደድ ወይ በመጥላት አልፍቀውም። ያለፈው ትውልድ ውላጅ ነኝ። የመጪው ትውልድ ወላጅ ነኝ። ያለፈው ትውልድ “አዬ ልጅ” እያለ ያሾፍብኛል፤ መጪው ትውልድ ይኮርጅኛል( ወደፊት “አይ አባት” ብሎ ይስቅብኝ ይሆናል -ግድ አይሰጠኝም) ለሁሉ ፈጣን ነኝ። ሁሉን በፍጥነት አይቼ በፍጥነት አልፋለሁ። ችክ ማለት አልወድም።ማንበብ ይቀጥሉ…

በመጨረሻም…

በመጨረሻም ራሴን ላጠፋ ነው። ቃሉ ራሱ ደስ ሲል! ራስን ማጥፋት!! ፓለቲከኞች “የራስን ዕድል በራስ መወሰን ” እንደሚሉት ነው። ከህይወት ምን ቀረኝ? ምንም! አንድ የቀረኝ ነገር ራሴን የማጥፋት ድርጊት ብቻ ነው። ከዛ በኋላ ሀገሬ ሞት ነው። ከሞት ግድግዳ ወዲህ ምንም የሚጎትተኝማንበብ ይቀጥሉ…

ላንቺ ግጥም እየፃፍኩ ነበር!

የሆነ የዓለም ጥግ ላይ ህፃናት በረሃብ ሲያልቁ እኔ ላንቺ ግጥም እየፃፍኩ ነበር። ሁሉም ሲያድጉ አንቺን ማግኘት እንደማይችሉ ስለገባችው እንደሚያለቅሱ ይሰማኝ ነበር። እንደዚህ እያሰብኩ ግጥም እየፃፍኩልሽ ነበር። ፈጣሪ ዓለም የሚያጠፋት በቁጣ ነው ሲሉኝ እገረማለሁ። ፈጣሪ ዓለምን ካጠፋ አንቺ ስትሞቺ በሚደርስበት ሀዘንማንበብ ይቀጥሉ…

ይሰለቻል

በመጀመሪያ እግዜር ብቻውን ነበር። ብቸኝ ት ሰለቸው። ብቸኝነት ሰለቸውና ዓለምን ፈጠረ። የፈጠረውን አይቶ ደስ አላለውም፣ ሰለቸው እንጂ። የሰለቸውን ዓለም ትቶ ሌላ አዲስ ነገር ፍለጋ ሄደ። ዓለምም ከዛን ወዲህ መሰልቸት ወለል ላይ ሆና የአምላኳን መምጣት በጥፍሯ ቆማ ትጠብቃለች። እኔ የዓለም አካልማንበብ ይቀጥሉ…

ቤት ሰራሽ ጦርነት

በአንዲት ሀገር ላይ ጨለማና ብርሃን ክፉኛ ተጣሉ አሸናፊ እስኪለይ ድብድብ ቀጠሉ የጨለማን ግንባር-አናቱን ሊበሳ ብርሃን ይጥራል የጨረራ መዓት ጨለማን ለመምታት ተግቶ ይወረውራል እውሩ ጨለማ መርግ መርግ ፅልመት ከአካሉ ያነሳል ድቅድቅ አሰልፎ ብርሃን ላይ ያፈሳል ተው ባይ በሌለበት ሃይ ባይ በጠፋበትማንበብ ይቀጥሉ…

የተደገሙ ወላጆች!

(ልጆቻችሁ፣ ልጆቻችሁ አይደሉም?) ካህሊል ጅብራን “The Prophet” በተባለ ስራው “ስለ ልጆች ንገረን” ለሚል ጥያቄ በነብዩ አንደበት ይናገራል። “your children are not your children” ምን? ልጆቻችሁ ልጆቻችሁ አይደሉም? እና የኛ ካልሆኑ የማን ናቸው? ነው ወላጆቻችን ናቸው? አትቀልዳ ካህሊል። እስቲ ትንሽ አብራራው።ማንበብ ይቀጥሉ…

አማርኛ እንዳበጁሽ አትበጂም

“ ያስለቅሳል እንጂ ይህስ አያሳቅም ግንድ ተደግፎ ዝንጀሮ ጫት ሲቅም” (አማርኛ እንዳበጁሽ አትበጂም) እህህ…..ኡህህ…..ውይይ….. አማርኛ ተኝታ ታቃስታለች። የሀገር ውስጥ እና የዓለም ትልልቅ ቋንቋዎች በዙሪያዋ ተሰብስበዋል። ጥቂት የቋንቋ ምሁራንም አሉ። “ኡውይይ…. ኸረ አልቻልኩም፣ ቆረጣጥሞ ሊገለኝ ነው!” “ አይዞሽ…. አይዞሽ… እኛም እኮማንበብ ይቀጥሉ…

ምክንያት በጠና ታማለች

ምክንያት በጠና ታማለች:: ምን እንደነካት ማንም አያውቅም:: አሉባልታ ግን አለ:: እነ ባህል; ዕድር; ሃይማኖት…መርዘዋት ነው የሚሉ አሉ:: ፍልስፍናም ይህን አሉባልታ ሰምቷል:: ሳይንስ ናት የነገረችው:: ባሉባልታ አያምንም:: ባያምንም ሰምቷታል:: ሁሉም በምክንያት ዙሪያ ቁጭ ብለዋል:: ፍልስፍና ያዘነ ይመስላል- ፊቱ ስለማይነበብ በእርግጠኝነት መናገርማንበብ ይቀጥሉ…

አንድ ጨለምኛ ግጥም፣ ለአንዲት ጨለምተኛ ሀገር

*** አንቺ ሃሳበ ብዙ፣ አንቺ ጓዘ ብዙ አቅም የሚፈትን፣ጉልበት የሚያጣምን ከህይወት ዋጋ ይልቅ በሞት ከሚያሳምን ከዚህ ትግል ጉዞ የሚገላግሉ- ልጆችሽ እያሉ የት እንዲያደርስሽ ነው ሰርክ መባተሉ? “ሁሉ ነፃ አይደለም፣ ውደቁ ተነሱ ቆፍሩ አፈር ማሱ” የሚሉ ቂሎችን ከጆሮሽ አርቂ ለማይረባ ነገርማንበብ ይቀጥሉ…