ታክሲው!

ታክሲው እየሄደ ነው። ወዴት እንደሚሄድ አናውቅም። ሾፌሩ ያውቀዋል ብለን እናምናለን። የኛ ስራ መሳፈር ነው። የሾፌሩ ደግሞ መንዳት። ሾፌሩ ይነዳል። እኛ እንነዳለን። መንገዱ ጭር ብሏል፣ ይህ ከታክሲዎች ሁሉ የዘገየው ሳይሆን አይቀርም። ከሾፌሮች ሁሉ ሰነፉ ጋር ተሳፍረን ሊሆን ይችላል። መንገዱ ገጭ ገጭማንበብ ይቀጥሉ…

በባህሩ እና “በባህር ዳር”መካከል…

በባህሩ እና “በባህር ዳር”መካከል… (የዘረኝነት መንቻካ ልብሶችን እናጥባለን!) ባህሩ ውስጥ ነኝ:: እልፍ ሰዎች ከባህሩ ወጥተው ዳር ላይ ተኮልኩለዋል:: ጥንት ዳሩ መሀል ነበር:: አሁን ዳሩ ወደ መሀል ገብቷል! ባህሩ ሰውነት ነው:: የባህሩ ዳር ዘረኝነት- የሰውነት ደረቅ መሬት! ባህሩ ውስጥ ነኝ:: ባህሩማንበብ ይቀጥሉ…

ይወለዱና በፈረንጅኛ የሸበረቁ

ይወለዱና በፈረንጅኛ የሸበረቁ ከ”ኦ ማይ ጋድ” ውጭ ፀሎት አያዉቁ ይወለድና ምሁር የሚባል ባህር ተሻግሮ ታሪክ ያርማል ይወለድና ለዕለት አሳቢ ሆኖ ይቀራል ኪራይ ሰብሳቢ ይወለድና ኒዎሊበራሉ ጠረ-ልማት ነው ካገሩ ሁሉ ይወለድና እልፍ ሞዛዛ ግብር አይከፍል ወይ ቦንድ አይገዛ ይወለድና የEtv አይነቱማንበብ ይቀጥሉ…

ሄይይ…. ንቃ አንተ!

አንተ! ንቃት መሃል የተኛህ! ጩኸት መሃል የምትናውዝ! ቀውጢ መሃል የምታንኮራፋ ንቃ!! እዛ… በዘረኝነት ጠባብ አልጋ ላይ ተኝተህ የምትናውዝ ንቃ! እንደምን እንቅልፍ ወሰደህ ብለህ ስንደነቅ ደንገጥ እንኳን ሳትል እንክልፍህን መለጠጥ?? ኸረ ንቃ!! የመታከት አየር እየሳብክ፣ መታከት የምትተነፍስ አንተ ንቃ! አይንህን ግለጥ!ማንበብ ይቀጥሉ…

ድንግልና ድንግል ነው?

ብር አምባር ሰበረልዎ ጀግናው ልጅዎ” ይባላል:: ጉድ እኮ ነው:: ስስ ስጋ የሰበረው የዓለምን ሪከርድ ከሰበረው እኩል ይዘፈንለታል:: ወንድ የጀግንነት እጩ; ሴቷ የጀግንነት ማሳያ መዋጮ አድርጎ ይነግረናል:: አሁን ድንግልና ለሴቷ ምኗ ነው? ለሰው ልጅ ምኑ ነው? ምን ይጨምርለታል ምን ያጎድልበታል? ምንማንበብ ይቀጥሉ…

አንድ ጨለምኛ ግጥም፣ ለአንዲት ጨለምተኛ ሀገር

*** አንቺ ሃሳበ ብዙ፣ አንቺ ጓዘ ብዙ አቅም የሚፈትን፣ጉልበት የሚያጣምን ከህይወት ዋጋ ይልቅ በሞት ከሚያሳምን ከዚህ ትግል ጉዞ የሚገላግሉ- ልጆችሽ እያሉ የት እንዲያደርስሽ ነው ሰርክ መባተሉ? “ሁሉ ነፃ አይደለም፣ ውደቁ ተነሱ ቆፍሩ አፈር ማሱ” የሚሉ ቂሎችን ከጆሮሽ አርቂ ለማይረባ ነገርማንበብ ይቀጥሉ…

ማነሽ ?!

ከእለታት በአንዱ፣ በቅዱስ እርጉም ቀን መንገድ ያገናኘን ድንገት የተያየን አንቺ አልፈሽኝ ስትሄጅ፣ እዛው ያስቀረሽኝ! …ላይሽን ሸፍኖት ጥቁር ጨለማ ጨርቅ ዐይንሽን ብቻ እንጂ፣ ሌላሽን የማላውቅ ማነሽ አንቺዬዋ? ማንነትሽ ማነው? አቅል እያሳተ፣ መንገድ የሚያስቀረው? ወንድን እንዳታስት ትጀቦን፣ ትሸፈን-ይሉትን የሰማሽ አይታይ አካልሽ ውዴማንበብ ይቀጥሉ…

“ከገዳይ ጋር ፍቅር”

አይጥ የድመቱ ነገር ግራ ገብቷታል። በተደጋጋሚ ፍቅሯን ልታሳየው ብትሞክርም ሊገባው አልቻለም። ከጉድጓዷ ስትወጣ አምራ እና ተኳኩላ ትወጣች። ድመቱ እንደ ሁል ጊዜ ከጉድጓዷ ፊት ለፊት ሆኖ ታገኘዋለች። አማላይ እንቅስቃሴ ልታሳየው ትሞክራለች። በፍቅር ዓይን ታየዋለች። እሱ ፍንክች የለም። እንዲህ መውደዷን ልታሳየው እየሞከረችም፣ማንበብ ይቀጥሉ…

የሕዝብ ችኩል ምን ይነክሳል?

…… ወሩን ሳስበው ፆም ነው፡፡ፆም ስለሆነ፣ አንድ ሆቴል ገብቼ ቅቅል በላሁ፡፡ …..ቅቅል የበላሁት ስላማረኝ ብቻ አይደለም የበላሁት፣ ፆም ስለሆነም ነው፡፡ ብዙዎች ከሚያደርጉት በተቃራኒ ማድረግ ደስ ስለሚለኝ ነው፡፡ ለነገሩ እውነቱን እናውራ ከተባለ፣ ቅቅል አልበላሁም፡፡ በዚህ ቅቅል ኑሮ፣ ቅቅል መብላት እራስን መቀቀልማንበብ ይቀጥሉ…

ማሞና ማሚቱ

<<ማሞና ማሚቱ በሉ ዳቦ ቆሎ ሮጡ ወደቁ ተነሱ በቶሎ>> /ቃላዊ ግጥም/ ማሞና ማሚቱ፣ ጠኔ እየጣላቸው፣ ነብስ የሚያነሳቸው ሌሎች እኮ አይደሉም፣ እኔና አንተ ናቸው፡፡ ቶሎ እየወደቅን ቶሎ የምንነሳ ቀለባችን ቆሎ ኑሯችን አበሳ ማሞና ማሚቱ፣ እኛ ነን አትርሳ፡፡ ከህይወት ግብግብ፣ እየሮጡ ገብተውማንበብ ይቀጥሉ…