ነግሬህ ነበረ

በድንገት ከኋላዬ መጥተህ አትንካኝ ብዬህ ነበር፡፡
ያጠብኳቸውን ብርጭቆዎች አንድ በአንድ እያደረቅኩ ከጀርባዬ መጥተህ ስትጎነትለኝ ጩኸቴን ለቀቅኩት፡፡
በድንጋጤ የወረወርኩት ብርጭቆ ወለሉ ላይ አርፎ ሲበተን አንዱ ስባሪ እግሬ ላይ ተሰካ፡፡ማንበብ ይቀጥሉ…

አክስቴ አክሊል

አክስቴ አክሊል በመላው ቤተሰብና ዘመድ አዝማድ ዘንድ የምትታወቅበትና የምትፈራበት አንድ ባህርይ አላት፤ ሽሙጧ! የአክስቴ አክሊል ማሽሟጠጥ ግን ዝም ብሎ ማሽሟጠጥ ብቻ አይደለም፡፡ ከባድ ጥበብ አለው፡፡ ቂቤ የምትቀባ መስላ በኩርኩም ታነድሻለቸች፤ ያሞገሰች መስላ ትሞልጭሃለች፡፡ በአንድ ሰበብ ዘመድ በተሰበሰበ ቁጥር ከእነ ረጅምማንበብ ይቀጥሉ…

ሰወርዋራ

ያገባሁት ሰው እንዴት እንዴት ብሎ ሕይወቴን ብልሽትሽት እንዳደረገው፣ በእድሜዬ ጢቢ ጢቢ እንደተጫወተ ልንገራችሁ። እንዴት የሰው ልጣጭ፣ የሰው ቁሩ እንዳደረገኝ፣ በረቀቀ ዘዴ ቀስ በቀስ ከሰው ሁሉ እንደነጠለኝ፣ እንዴት ዋጋ ቢስ ነኝ ብዬ እንዳስብ፣ብቸኛ፣ ፈሪ፣ ጠርጣራና በእሱ ላይ ብቻ ጥገኛ እንድሆን እንዳደረገኝማንበብ ይቀጥሉ…

ደረሰ

ሕይወት አዲሱ ቦይፍሬንዷ ደረሰ ቤት ናት፡፡ ግንኙነታቸው የወራት ግን በፍጥነት እየጠበቀ ያለ ነው፡፡ ለወትሮው የአማካሪነት ስራውን በአመዛኙ ከቤቱ የሚሰራው ደረሰ ዛሬ ከጓደኞቹ ጋር ቁርስ ሊበላ በጠዋት ወጥቷል፡፡ ከጠዋቱ አምስት ሰዐት ቢሆንም እስካሁን በፒጃማ ስትንጎማለል የቆየችው ሕይወት የቤት ውስጥ ቢሮው ገብታማንበብ ይቀጥሉ…

ጎስቋሎቹ

የማለዳ ጀምበር ጣሪያዬን ማሞቅ ሳትጀምር በፊት የአንድ ክፍል ቤቴ በር በእርጋታ ተንኳኳ። አባባ ናቸው፡፡ ክረምት በጋ ሳይሉ ዘወትር የሚለብሱትን አሮጌ ካፖርት ለብሰው ደጄ ቆመዋል፡፡ ካፓርቱ ከወትሮው የሰፋቸው ይመስላል፡፡ እንደዚህ ቀረብ ብዬ ባየኋቸው ቁጥር ከሲታ ሰውነትና ፊታቸው ይበልጥ ተጎሳቅሎ ይታየኛል፡፡ እንደሁልጊዜውማንበብ ይቀጥሉ…

ሰይጣን ወይ እግዜር የጀመሩት… እኔ የቀጠልኩት (ክፍል ሃያ ሁለት)

(የመጨረሻው ክፍል) «ዶክተር ራሴን ሀኪም ቤት ካገኘሁት አልድንም ይብስብኛል እመነኝ! ትንሽ ቀን አይተኸኝ ከባሰብኝ ቃል እገባልሃለሁ ራሴው ሄዳለሁ» አልኩት። ከህክምና ጣቢያ ህክምናዬን መከታተል እንዳለብኝ ሲነግረኝ እቤቱ ይዞኝ ሄደ። በዚህ ጊዜ እንዳለፈው ለማላውቀው ጊዜ ያህል ጨለማና ፍርሃቴ ውስጥ አልነከርም!! አስፈሪው ደቂቃማንበብ ይቀጥሉ…

ሰይጣን ወይ እግዜር የጀመሩት… እኔ የቀጠልኩት (ክፍል ሀያ አንድ)

ፅፎ እስኪጨርስ እረፍት አጣሁ። አስሬ ላይብረሪ እመላለሳለሁ። ጣቶቹ አሁንም 100% ስላልሆኑ ቀስ ብሎ ነው የሚፅፈው። «እሺ የፃፍከውን ላንብበውና ትቀጥላለህ?» እለዋለሁ። «አይሆንም ህፃን አትሁኚ!» ይለኛል። «ጮክ ብለሽ አታንብቢልኝ! የምትጠይቂኝ ነገር ከሌለ በቀር! ለራስሽ አንብቢው» ብሎኝ ሶፋው ላይ አጠገቡ እንድቀመጥ በእጁ እየመታማንበብ ይቀጥሉ…

ሰይጣን ወይ እግዜር የጀመሩት… እኔ የቀጠልኩት (ክፍል ሀያ)

እና ሰዓት ብላችሁ ከመነጫነጫችሁ በፊት ይቅርታ ብያለሁ!! ሜሪ ፈለቀ ከማይታይ ፊርማጋ ) «ትናንትህ ላይ በበደሉህ ሰዎች ነው ዓለምን በሙሉ እየዳኘህ ያለኸውኮ! በዙሪያህ ያሉ ሰዎች በሙሉ እንደእነሱ ናቸው ማለት አይደለም! በተቃራኒው የሆኑ ሰዎች አሉ። አንተ ያደረግከው ለማንም ምንም እድል አለመስጠትን ነው።»ማንበብ ይቀጥሉ…

ሰይጣን ወይ እግዜር የጀመሩት… እኔ የቀጠልኩት (ክፍል አስራ ዘጠኝ)

«ማዕረጌን ከጎኔ አድርጌ የተጋበዝነውን እራት ልንታደም ስንሄድ ዘውድ እንደተደፋለት ልዑል አንገቴን ቀና አድርጌ በኩራት ነበር። ምንም የጎደለኝ ነገር አልነበረም። ማዕረጌ ከጎኔ ነበረቻ!! ከሶስት ሳምንት በኋላ እሷ እንደተመኘችው በሷው አባባል <እልልልልልልል በተባለለት ሰርግ> ወዳጅም ጠላትም ምስክር ሆኖ ባደባባይ የእኔ ልትሆን ነዋ!!ማንበብ ይቀጥሉ…

ሰይጣን ወይ እግዜር የጀመሩት… እኔ የቀጠልኩት (ክፍል አስራ ስምንት)

«ታውቂያለሽ የአዕምሮ ክፍላችን እድገት በ25 ዓመታችን እንደሚያበቃ? ከዛም ውስጥ ከ80% በላዩ የሚያድገው እስከ 5 ዓመት አካባቢ ባለው እድሜያችን ነው። ጥናቶች እንደሚያሳዩት የሰው ልጅ ከ25 ዓመቱ በፊት በሚያዳብረው ልምድ ፣እውቀት ፣ ባህል ፣ ሀይማኖት ……. Whatever ነው የሚቀረፀው። ልክ አለመሆኑን ቢያውቅማንበብ ይቀጥሉ…