ሰርጉ የራሴ ሆኖ ፣ በሰው ሰራሽ ፋብሪካ የተመረተ ሮቦት ይመስል ዘመድ አልባ ባል ላገባ የተዘጋጀሁት እኔ ሆኜ ሳለሁ፣ ሰርጉ ላይ ሚዜ እንኳን የሚሆን ጓደኛ የሌለው ባል ለማግባት ራሴ አምኜ ………. ምን ይሉ ይሆን ብዬ የምጨነቀው ለቤተሰብ ፣ ሰርጉ እንከን እንዳይኖረውማንበብ ይቀጥሉ…
ሰይጣን ወይ እግዜር የጀመሩት… እኔ የቀጠልኩት (ክፍል ስድስት)
የዛን ቀን …….. እንኳን ዶክመንተሪ ፊልሙን አይተን ስንጨርስ በሙቀቱ ወዝቶ ቅባት የተቀባ የመሰለውን ጠይም ፈርጣማ ደረቱን እጄ ሲንቀለቀል ሄዶ የነካው ቀን……… እጄን ደረቱ ላይ በእጁ ደግፎ እንዳላንቀሳቅሰው ይዞት «እርግጠኛ ነሽ?» «ቨርጅን አይደለሁምኮ።» «አውቃለሁ!! በኋላ የፀፀትሽ ምክንያት መሆን አልፈልግም።» እያለኝ ትንፋሹማንበብ ይቀጥሉ…
ሰይጣን ወይ እግዜር የጀመሩት… እኔ የቀጠልኩት (ክፍል አምስት)
«እኔ ደስ የሚለኝ ጓደኛሞች ብንሆን ነው።» አልኩት እቤቱ ይዞኝ የሄደ ቀን «እረፊ! እኔ አንዴ ልብስሽን አውልቄ ጭንቅላቴ ውስጥ ስዬሻለሁ። ጓደኛሞች እንሁን ብልሽ ውሸቴን ነው። ገና ሳይሽ የቀሚስሽን ሶስት ትንንሽዬ ቁልፎች ፣ ቀጥሎ ዚፑን …….. ወደታች ባወልቀው ወይ ወደላይ የቱ ይፈጥናል?ማንበብ ይቀጥሉ…
ሰይጣን ወይ እግዜር የጀመሩት… እኔ የቀጠልኩት (ክፍል አራት)
ለመጀመሪያ ጊዜ በተያየን በአስረኛው ደቂቃ ነው <ላግባሽ> ያለኝ። የሶስተኛ ታናሼን ሰርግ ልታደም አንደኛው የከተማችን ሆቴል ነበርኩ። የምሳ ቡፌ ከተነሳ በኋላ ማንም ሳያየኝ ከአዳራሹ ውልቅ ብዬ እዛው ህንፃ ላይ ያለ ሬስቶራንት ውስጥ ገባሁ። ቢያድለኝኮ የአክስቶቼን ውግምት የሆነ ዓይን መሸሼ ነበር። ገናማንበብ ይቀጥሉ…
ሰይጣን ወይ እግዜር የጀመሩት… እኔ የቀጠልኩት (ክፍል ሁለት)
ከእኔ በፊት ሁለት ሚስት አግብቶ እንደነበር ሳላውቅ አይደለም ያገባሁት። አውቅ ነበር። ለሁለቱም ሚስቶቹ ልክ ከእኔ ጋር እንዳደረገው የሀብት ውርስ ኮንትራት አስፈርሟቸው እንደነበርም አልደበቀኝም ነበር። በፍቅሩ ነሁልዬ ከእኔ በፊት የነበረው ህይወቱ ገሀነም እሳት ጭስ ሳይሸተኝ ቀርቶም አይደለም። ወይም ፍቅሬ አቅሉን አስቶትማንበብ ይቀጥሉ…
ሰይጣን ወይ እግዜር የጀመሩት… እኔ የቀጠልኩት (ክፍል አንድ)
«ሞቼ ቢሆን ኖሮ ደስ ይልሽ ነበር አይደል?» አለኝ በወጉ ማሽከርከር ያልለመደውን ዊልቸር እየገፋ ወደሳሎን ብቅ እንዳለ። ፊቱ ምሬት ወይ ጥላቻ በቅጡ ያልለየሁት ስሜት ይተራመስበታል። ዝም ያልኩት መመላለሱ ልቤን ስለሚያደክመኝ ነበር። በጎማው እየተንቀራፈፈ አጠገቤ ደርሶ « ንገሪኛ ደስ ይልሽ ነበር አይደል?»ማንበብ ይቀጥሉ…
ሠማየ ውድውድ (ምዕራፍ፡፫)
እና፥በእዚህ፡አስደናቂ፡ጎዞ፡ወቅት፡ነው፥ለተረት፡የማይመስል፣ለዕውን፡የሚያስፈራ፣ለግምት፡የቸገረ፡`ኣጋጣሚ`፡ከፊት፡ለፊታችን፡የተደቀነብን።የሆነው፡ስለ፡ሆነ፡እና፤መዝገብ፡የሙያ፡ግዴታዬ፡በመሆኑም፤አነሆኝ፤ገጠመኙን፡እንደሚከተለው፡ከትቤዋለሁ።ትርጉም፥የግል፣ዕምነትም፡የተጸውዖ፡ናቸው፡እና፥እንደመሰላችሁ፡ተረዱት።ማንበብ ይቀጥሉ…
የቀይ ልክፍት
“ጥሬ ስጋ በቀይ ወይን ምሳ ልጋብዝሽ” ብሎ ነው የጀመረኝ። “በደስታ” አልኩኝ። ጥሬ ስጋ ነፍሴ እንደሆነ ማንም ያውቃል።…… “ምሳ በልቼ አሁን መጣሁ” ብዬ ከቤት ወጥቼ የሚቀጥለውን ቀን ምሳ በልቼ ተመለስኩ። በቁርጥ ሰበብ ስንቋረጥ ዓመት ሆነ።…… “ሜዬ ገብቶልሻል ይሄ ልጅ! “ይሉኛል ጓደኞቼ……ማንበብ ይቀጥሉ…
ሁለቱን ባሎቼን ላስማማ እያሸማገልኳቸው ነው!! (ክፍል ሁለት)
የሳመኝ ቀን “በናትህ ይሄን ነገር በምስክር ፊት አድርግልኝ” ብለው ደስ ባለኝ። ስሜ መራራ ነዋ። ሳመችው እንጂ ሳማት አይባልልኝማ! እርግጥ የሳመኝ እለት ያልኳችሁ ቀን ማለት በዋዛ የተገኘ እንዳይመስላችሁ “ጌታ ሆይ ይሄ ሰው በወንድምነት ይሁን በባልነት ፍቅር የሚወደኝ መለየት የምችልበት ፀጋ ስጠኝ!ማንበብ ይቀጥሉ…
ሁለቱን ባሎቼን ላስማማ እያሸማገልኳቸው ነው!!
ግርምታችሁን እና እርግማናችሁን ከማዥጎድጎዳችሁ በፊት ትንፋሽ እየሰበሰባችሁ ከመጀመሪያው ልጀምርላችሁና ሁለቱንም ላስተዋውቃችሁ። የመጀመሪያው ባሌ “ባለቤቴ ነው ተዋወቂው!” ብዬ ያስተዋወቅኳት ጓደኛዬ “ወየው በፈጣሪ ባልሽ ሲያምር አጣብሺኝ!” ያለችለት ውብ ነው። የገዛ እናቴ ልክ እንደጠበስኩት ስታውቅ “ውይ ልጄ የልጁን ህይወት አታበልሺ አጉል ታደርጊዋለሽ !ይቅርብሽማንበብ ይቀጥሉ…
