“እጅ እድፉን ያየበትን አይን ጉድፍ ያፀዳል” ተቆራኝተው የኖሩት የአካል ክፍሎቻችን በእድሜ ብዛት ሲወራረሱ “እጅ አይንን ተክቶ፥ አይን ግን እጅን ይተካ ዘንድ አይቻለውም” ስል ያሰብኩት ዛሬ በምተርክላችሁ ገጠመኜ ነው። ለፊልም ስራ ባህርዳር ከተማ ዙሪያ በነበርኩበት ወቅት እንዲህም ሆነ። ፊልሙ – የገጠርማንበብ ይቀጥሉ…
የመታወቂያው ጉዳይ
“ግራጁዬት ሎየር ነኝ” ድንቄም በግድ የተፃፈብኝን የመታወቂያዬን ብሔር ስያሜ ወደ ኢትዮጵያዊ ለማስቀየር ዛሬ ሶስተኛ ቀን ሙከራዬን ቀጥዬ ውያለሁ። ባለፈው ሳምንት የክፍለ ከተማውን ኃላፊ ሰኞ ወይ ማክሰኞ መጥቼ እንዳነጋግር ተቀጥሬ ነበር ትረካዬን ያቆምኩት። እነሆ የዛሬ ውሎዬ፡- የክፍለ ከተማው የወሳኝ ኩነቶች ሀላፊማንበብ ይቀጥሉ…
ካልፎሂያጁ ማስታወሻ የተቀነጨበ
አሪፍ የፍቅር ግጥም ጽፌ ለመለጠፍ አስቤ ነበር። ግን ብለው ብሠራው “ እኔ እምልሽ ውዴ” ከሚለው ቃል ውጭ ጠብ ሊልኝ አልቻለም። እኔ እምልሽ ውዴ! ብለው ሳይጀምሩ- ስለፍቅር መጻፍ አይቻልም እንዴ? አንዳንድ ባለንጀሮቼ በውስጥ መሥመር ይሄን ድብርታም ዘመን እንዴት እያሳለፍከው ነው ምናምንማንበብ ይቀጥሉ…
የመታወቂያው ጉዳይ
የቀድሞው ቀበሌያችን አሁን አድጎ ወረዳ ሆኗል። ከጠዋት ጀምሮ እስከ አሁን መብራት የለም ስለተባለ የመታወቂያ እድሳት ጉዳይ ለዛሬ አይሳካም ተብሎ ተመልሻለሁ። ጥያቄዬን ግን ለተረኛው ሹም “ብሔር – ኢትዮጵያዊ የሚል መታወቂያ ይሰጠኝ” ስል አቅርቤ በፈገግታ እና በአግራሞት ሳቅ “ቅፁ ላይ ካለው ወይማንበብ ይቀጥሉ…
ሰው ሳይቀና ሀገር አይቀናም
አንድ ሰው ራሱን በዘር መግለፁ ችግር ያለው አይመስለኝም። ችግሩ ዘረኛ መሆን ላይ ነው።ዘረኛ መሆንም ሃሳብ እንጂ ተግባር እስካልሆነ የከፋ ችግር አይሆን ይሆናል። ግን፣ዘረኝነት በልብ ይዘው የሚቆዩት ብቻ አይደለም። ካልወጣ፣ ሌሎች ካልጠላ፣ አጋጣሚውን ሲያገኝም ካልደቆሰ አስችሎት አርፎ መቀመጡን እንጃ! አንዳንድ አስተሳሰቦችማንበብ ይቀጥሉ…
ምክር እስከመቃብር
የሆነ ጊዜ ላይ ባንድ እውቅ ሆስፒታል ውስጥ ያማካሪነት ሥራ እሠራ ነበር። የሥልጠና መርሐችን ከአሜሪካኖች በቀጥታ የተኮረጀ ስለነበር ምክራችን ድሐን መሠረት ያደረገ አልነበረም። ከእለታት አንድ ቀን አንዱ ጎስቆል ያለ ሰው ወደ ቢሮየ መጥቶ ምርመራ ተደረገለት። ውጤቱን ተመልክቸ በደሙ ውስጥ ሻይረሱ እንደተገኘበትማንበብ ይቀጥሉ…
ሕዝብን የሚያዳምጥ መንግሥት፤ መንግሥትን የሚያዳምጥ ሕዝብ
ሀገር ሰላም እንድትሆን፤ ሰላም ሆናም በብልጽግና ጎዳና እንድትራመድ ከታሰበ ሁለት ነገሮች የግድ ያስፈልጓታል። ሕዝብን የሚያዳምጥ መንግሥትና መንግሥትን የሚያዳምጥ ሕዝብ። ማዳመጥ ከመስማት ይለያል። መስማት ጆሮ ለተፈጠረለት ሁሉ የሚቻል ነው። ይህን ጽሑፍ ስናነብ እንኳን ስንትና ስንት ድምጾችን ፈልገንም ሳንፈልግም እንሰማለን። ማዳመጥ ግንማንበብ ይቀጥሉ…
“ወዜን አልሸጥም”
በካን ፊልም ፌስቲቫል ላይ ይፋዊ የዕይታ ተሳትፎ በማድረግ የመጀመሪያ ኢትዮጵያዊ ፊልም ሆኖ የተመረጠው የያሬድ ዘለቀ ዳንግሌ (Lumb) ተንቀሳቃሽ ምሥል ላይ የነበረኝን የሥራ ቆይታ አስታውሼ፣ ከቀረፃው በፊት ስለነበረው የአልባሳት ግዢ ቆይታ ላጫውታችሁ። ህሊና ደሳለኝ የፊልም ሥራ ውስጥ በአልባሳት ዲዛይነርነት እየታወቀች የመጣችማንበብ ይቀጥሉ…
ሆያ ሆዬ ድሮና ዘንድሮ
ዘንድሮ እንዲህም ሆነ…….. ሆያ ሆዬ የሚጨፍሩ የዘመኑ ነጋዴ ህፃናት ባላቶሊ ቁርጣቸውን በቄንጥ ተቆርጠው ፣ ደመወዜን የሚያሸማቅቅ ኤር ናይክ ተጫምተው ፣ ዱላቸውን ይዘው ወደ ተቀመጥኩበት ድድ ማስጫዬ መጡ ‹እስቲ ሆያ ሆዬ ጨፍሩልኝ?› ብዬ ስጠይቃቸው ‹ባለስንት?› ብለውኝ በደህንነቶች እንደተከበበ የተቃዋሚ ፓርቲ ቢሮማንበብ ይቀጥሉ…
ሕመም አንድም ለትምህርት አንድም ለሞት
ጥንታውያን የአብነት ሊቃውንት ‹ሕመም አንድም ለትምህርት አንድም ለሞት ነው› ይላሉ። መታመሙን ላወቀ፣ መድኃኒቱን ለፈለገ፣ መድኃኒቱንም በትክክል ለወሰደ፣ ወስዶም ለዳነ ሰው ሕመም ለትምህርት ይሆነዋል። ሦስት ነገር ይማርበታልና። አንድም ዳግመኛ እንዳይዘው ጥንቃቄን፣ አንድም ቢይዘው ሊትርፍ የሚችልበትን መፍትሔን፣ አንድም ደግሞ ለሌላው የሚመክረው ልምድንማንበብ ይቀጥሉ…