*** አንቺ ሃሳበ ብዙ፣ አንቺ ጓዘ ብዙ አቅም የሚፈትን፣ጉልበት የሚያጣምን ከህይወት ዋጋ ይልቅ በሞት ከሚያሳምን ከዚህ ትግል ጉዞ የሚገላግሉ- ልጆችሽ እያሉ የት እንዲያደርስሽ ነው ሰርክ መባተሉ? “ሁሉ ነፃ አይደለም፣ ውደቁ ተነሱ ቆፍሩ አፈር ማሱ” የሚሉ ቂሎችን ከጆሮሽ አርቂ ለማይረባ ነገርማንበብ ይቀጥሉ…
ማነሽ ?!
ከእለታት በአንዱ፣ በቅዱስ እርጉም ቀን መንገድ ያገናኘን ድንገት የተያየን አንቺ አልፈሽኝ ስትሄጅ፣ እዛው ያስቀረሽኝ! …ላይሽን ሸፍኖት ጥቁር ጨለማ ጨርቅ ዐይንሽን ብቻ እንጂ፣ ሌላሽን የማላውቅ ማነሽ አንቺዬዋ? ማንነትሽ ማነው? አቅል እያሳተ፣ መንገድ የሚያስቀረው? ወንድን እንዳታስት ትጀቦን፣ ትሸፈን-ይሉትን የሰማሽ አይታይ አካልሽ ውዴማንበብ ይቀጥሉ…
ህዳሴው የማይነካቸው፣ ህዳሴውን የማይነኩ የሰፈሬ ወጣቶች
አንዳንዴ በግድ መገረብ ያለባቸው ፖስቶች አሉ ብለው እናምናለን። አምነንም እንገርባለን… ******* ህዳሴው የማይነካቸው፣ ህዳሴውን የማይነኩ የሰፈሬ ወጣቶች (ይሄ ፓስት ህዳሴው ትክክለኛ ነው፣ አይደለም ብሎ አይነታረክም) ‹‹‹‹‹‹ ››››››› እዚህች ሰፈር ነው ያደኩት፡፡ አድጌ “እግሬን ከመፍታቴ” በፊት ዓለም ከዚህች ሰፈር አትበልጥም ነበርማንበብ ይቀጥሉ…
ጎሬ-ቤቶች!
(ፀሀፊው፣ እኔ) ***** ጎረቤታሞች ናቸው፡፡ ከአጠራቸው ውጪ ግን ምናቸውም አይገናኝም። የአንዷ ኑሮ ቅንጦት የሌላኛዋ እጦት ነው፡፡ ያችኛዋ የምትበላው የላትም። ይህችኛዋ የማትበላው የላትም። አንድ ቀን… ያቺ የድህነት አቅም ማሳያዋ ሴት….ወሰነች! “የምበላው አጥቼ፣ ገርጥቼ ነጥቼ ከምሞት… አንድ ቀን እንኳን ጀመበር እስክትጠልቅ አጊጬ፣ተውቤማንበብ ይቀጥሉ…
ለቃልህ ታምኜ…
በአንዲት እርጉም ቀን ልቤ ፅድቅ ሻተ; ከመፅሐፍህ መሃል “ግራህን ቢመቱ ቀኝ ስጥ” የሚል ቃል ለነብሴ ሸተተ; እልፍ ጠላቶቼ መንገዴን ተረዱ; በእፀድቃለሁ ሰበብ መስከኔን ወደዱ ; መጡ ተሰልፈው:- ግራዬን ነገሉ; ከቀኙም አንድ አሉ ወገሩኝ ደጋግመው ክንዳቸው እስኪዝል; ሁሉን ዝም አልክዋቸው ፅድቅህማንበብ ይቀጥሉ…
አንበሳ ዙሪያችን ሚዳቅዋ ልባችን!
አንበሳ ዙሪያችን ሚዳቅዋ ልባችን! (የአንበሳ ልብ ቢጠፋ፣ በአንበሳ ጫማ ሮጦ የማምለጥ ሀገራዊ ጥበብ) ********* እስቲ ዙሪያችሁን ተመልከቱት? ሁሉ ነገር አንበሳ ነው!! ተረታችን ሲጀምር፣ “አንድ አንበሳ ነበረ…” ብሎ ነው፡፡ አውቶብሳችን አንበሳ ነው፡፡ ጫማችን አንበሳ ነው፡፡ ዘፈናችን “ቀነኒሳ አንበሳ”፣ “አንበሳው አገሳ” …ማንበብ ይቀጥሉ…
የእንባ አውራ ጎዳኖች
ይሄውልሽ እምዬ፡- በሆዴ የያዝኩት የብሶቴ ክምር ብዙ ሲናገሩት-አብዙት ሲፅፉት፣ መስሎሽ ባዶ `ሚቀር- እንዳትታለዪ ይብሱን ነው `ሚያድግ፣ እጅጉን ነው `ሚንር ይቀለኛል ብዬ በነገርኩሽ ቁጥር፡፡ ከወደቁ ኋላ መፈረጋገጡ፣ ውጤቱ መላላጥ እንደሆን አውቃለሁ ግን ከዝም በላይ አይጎዳኝምና ስሚኝ ነግርሻለሁ! እዚህ ካንቺ ግቢ፣ እዚሁማንበብ ይቀጥሉ…
የሴቶች ካቴና!
ይህች ፅሁፍ ባለፈው ዓመት “በአዲስ አድማስ” ጋዜጣ ላይ ወታ ነበር፡፡ በጊዜው ትንሽ ተነካክታ ስለነበር ኦርጅናል መልኳን እንዲህ አቅርበናል፡፡ የሴቶች ካቴና! ሰልችተውኛል፡፡ አንዷ ከአንዷ በቁመት፣ በመልክ፣ በሰውነት ቅርፅ ቢለያዩ እንጂ በአዕምሮ አንድ ሆነውብኛል፡፡ ብዙ ሴቶችን አይቻለሁ፡፡ ያው ናቸው፡፡ ለፍቅር ስሱ ነኝ፡፡ማንበብ ይቀጥሉ…
እኛ ማን ነን…!
አውቀን የተኛን ነን፡፡ ቢቀሰቅሱን የማንሰማ! ከከተሳካልን ቀስቃሾቻችንንም አሰልችተን የምናስተኛ! …ሰውነታችን ጣምኖ ጮማ ከምንቆርጥ ይልቅ፣ ያለምንም ልፋት የምናገኛትን ጎመን እየላፍን፣ “ጎመን በጤና” የምንል ዘመናዮች ነን፡፡ ታሪክ ዳቦ አይሆንም ብለን፣ ታሪክ የማይሆን ዳቦ እየገመጥን ያለን በልቶ አደሮች ነን፡፡ ነፃታችንን ከባርነት እግር ስርማንበብ ይቀጥሉ…
ስለ ሴቶች
ተከርክሞ የተገረበ፣ ቧልትና ቁምነገር!! “ስለ ሴቶች“ ( ስለ ወንዶች ደግሞ እነሱ ይፃፉ) ከአፈጣጠር እንጀምር፤ በኔ እምነት፣ ሴቶች የተፈጠሩት፣ ወንዶች በተፈጠሩባት ቅፅበት ነው፡፡ እንደ መጥሐፉ ከሆነ፣ ሴት የተፈጠረችው ሁለተኛ ነው፡፡ በደንብ ካየነው ግን እኩል ነው የተፈጠሩት፡፡ ወንድ ሲፈጠር፣ እንትን ነበረው አይደል?ማንበብ ይቀጥሉ…