ስሚ መስሚያ ካለሽ። ከሰማሽ ደሞ ተስማሚ፤ ወዲያ ሂጂልኝ እስቲ። ማነሽ እውነት ነኝ የምትይ፣ እስቲ ስሚን የስንቱን አለመስማት እንችላለን? መንግስት አይሰማን፣ ፈጣሪ አይሰማን፣ አንቺ አትሰሚን… ኸረ እስቲ አንቺ እንኳን?!! ማን ነበረ ስምሽ? “እውነት ” ነው አይደል? እውነቱን ልንገርሽ፣ በደረስኩበት ባትደርሺ ደስማንበብ ይቀጥሉ…
ባትሄጂ ኖሮ…!
ባትሄጂ ኖሮ፣ ብትሆኝ ከኔ እቅፍ እዚህ ከፃፍኩት ላይ፣አንድም መስመር አልፅፍ፡፡ አቤት ባትሄጂ! ግን አንቺ አልቆምሽም መጓዝ አልደከምሽም፡፡ ይሄዋ፡- ከሄድሽ በኋላ ዐይኔም አይታየው፣ ጆሮዬም አይሰማ ልቤም ደም የሚረጭ፣ ባንቺ ስለደማ፡፡ አንቺ በመሄድሽ፤ ያለህይወት በህይወት ተነጥላኝ ነብሴ፣ ያው አለሁ ሙት ሆኜ፣ ለሰዉምማንበብ ይቀጥሉ…
ቤት ሰራሽ ጦርነት
በአንዲት ሀገር ላይ ጨለማና ብርሃን ክፉኛ ተጣሉ አሸናፊ እስኪለይ ድብድብ ቀጠሉ የጨለማን ግንባር-አናቱን ሊበሳ ብርሃን ይጥራል የጨረራ መዓት ጨለማን ለመምታት ተግቶ ይወረውራል እውሩ ጨለማ መርግ መርግ ፅልመት ከአካሉ ያነሳል ድቅድቅ አሰልፎ ብርሃን ላይ ያፈሳል ተው ባይ በሌለበት ሃይ ባይ በጠፋበትማንበብ ይቀጥሉ…
ድርብርብ ስቅላት
የመሲሁ ስቅየት ግርፊያ ስቅላቱ አምላክ ነኝ ስላለ በድምቀት ተሳለ የኛንስ ስቅላት ማነው ያስተዋለ? ተመልካች ጠፍቶ እንጂ ዐይን የሚለግሰን መውረድ እንደናፈቅን እኛም መስቀል ላይ ነን:: ዘውትር ዱላ እና አሳር ዘውትር ችንካር ሚስማር የሚገዘግዘን የሚጠዘጥዘን እኛም ክርስቶስ ነን እኔም ታዝቤያለሁ… ሺ ዱላማንበብ ይቀጥሉ…
ወጣትነቴን ያያችሁ
አላያችሁም አውቃለሁ! መጠየቅ፣ ልማድ ሆኖብኝ፣ ቁጭቴ ብሶት ጭኖብኝ የሄደች ወጣትነቴን፣ ያያችሁ…ያያችሁ እያልኩ፣ ባታዩም እጠይቃለሁ፡፡ * * * * ያያችሁ ወጣትነቴን? አፍለኛ፣ ማራኪ ወቅቴን? በጫት ጉዝጓዝ አፍኜ፣ ከፍኜ የገደልኳትን በማይገባኝ የፈረንጅ አፍ፣ አደንቁሬ የጣልኳትን ወጣትነቴን ያያችሁ፣ ሳልጨብጥ ያበረርኳትን፡፡ * * *ማንበብ ይቀጥሉ…
ጨዋታው ፈረሰ ዳቦው…
ጨዋታው ፈረሰ ዳቦው ተቆረሰ የሚል ተረት ይዘን በባዶ ሆዳችን ጨዋታ ማፍረስ ነው-ትልቁ ትልማችን የዳቦ መቆረስ በጨዋታ መፍረስ ታጅቦ ከመጣ ደህና ሁን ጨዋታ-ከሀገራችን ውጣ! ሆዷን በመብሰክሰክ ለሞላች እቺ ሀገር ከጨዋታው ሳይሆን ዳቦው ነው ቁምነገር ይህንን በማመን… ስንት ዓይነት ጨዋታ ግብ እንደናፈቀማንበብ ይቀጥሉ…
ክፈት በለው በሩን…የጌታህን
ክፈት ጌታው ክፈት ደብድበን, ወጋግረን, ሰብረነው ሳንዘልቅ; ክፈት በለው በሩን- ክፈት በሩን ልቀቅ:: ሕዝቡን ዘግተውበት; ነስተውት ማለፊያ ንገረው ለጌታህ እዚህ ያለውን ግፊያ! በክፋት ተገፍቶ የዘጋውን ሳንቃ ጥበቃችን ሳትመሽ ትዕግስታችን ጠልቃ ክፈት በለው በሩን, ክፈት በሩን ክፈት! ይህ ምስኪን ሕዝባችን; ልቡንማንበብ ይቀጥሉ…
ዘመን ሆይ ማን ልበል?
ምን ዓይነት ዘመን ነው፣ የዘመን ጉንድሽድሽ ባንዳ እያከበረ፣ ጀግናን የሚያንቋሽሽ? ኸረ መን ዘመን ነው፣ የዘመን ቅራሪ ኮብል የሚያስጠርብ የጊዜያችን ዲግሪ ምን ዓይነት ዘመን ነው፣ የዘመን እግረኛ ስደት የሆነበት ብቸኛው መዳኛ ምን ዓይነት፣ ምን ዓይነት ምን ዓይነት ዘመን ነው፣ ዘመንን ለመስደብማንበብ ይቀጥሉ…
ይወለዱና በፈረንጅኛ የሸበረቁ
ይወለዱና በፈረንጅኛ የሸበረቁ ከ”ኦ ማይ ጋድ” ውጭ ፀሎት አያዉቁ ይወለድና ምሁር የሚባል ባህር ተሻግሮ ታሪክ ያርማል ይወለድና ለዕለት አሳቢ ሆኖ ይቀራል ኪራይ ሰብሳቢ ይወለድና ኒዎሊበራሉ ጠረ-ልማት ነው ካገሩ ሁሉ ይወለድና እልፍ ሞዛዛ ግብር አይከፍል ወይ ቦንድ አይገዛ ይወለድና የEtv አይነቱማንበብ ይቀጥሉ…
ማሞና ማሚቱ
<<ማሞና ማሚቱ በሉ ዳቦ ቆሎ ሮጡ ወደቁ ተነሱ በቶሎ>> /ቃላዊ ግጥም/ ማሞና ማሚቱ፣ ጠኔ እየጣላቸው፣ ነብስ የሚያነሳቸው ሌሎች እኮ አይደሉም፣ እኔና አንተ ናቸው፡፡ ቶሎ እየወደቅን ቶሎ የምንነሳ ቀለባችን ቆሎ ኑሯችን አበሳ ማሞና ማሚቱ፣ እኛ ነን አትርሳ፡፡ ከህይወት ግብግብ፣ እየሮጡ ገብተውማንበብ ይቀጥሉ…