የሳመኝ ቀን “በናትህ ይሄን ነገር በምስክር ፊት አድርግልኝ” ብለው ደስ ባለኝ። ስሜ መራራ ነዋ። ሳመችው እንጂ ሳማት አይባልልኝማ! እርግጥ የሳመኝ እለት ያልኳችሁ ቀን ማለት በዋዛ የተገኘ እንዳይመስላችሁ “ጌታ ሆይ ይሄ ሰው በወንድምነት ይሁን በባልነት ፍቅር የሚወደኝ መለየት የምችልበት ፀጋ ስጠኝ!ማንበብ ይቀጥሉ…
ሁለቱን ባሎቼን ላስማማ እያሸማገልኳቸው ነው!!
ግርምታችሁን እና እርግማናችሁን ከማዥጎድጎዳችሁ በፊት ትንፋሽ እየሰበሰባችሁ ከመጀመሪያው ልጀምርላችሁና ሁለቱንም ላስተዋውቃችሁ። የመጀመሪያው ባሌ “ባለቤቴ ነው ተዋወቂው!” ብዬ ያስተዋወቅኳት ጓደኛዬ “ወየው በፈጣሪ ባልሽ ሲያምር አጣብሺኝ!” ያለችለት ውብ ነው። የገዛ እናቴ ልክ እንደጠበስኩት ስታውቅ “ውይ ልጄ የልጁን ህይወት አታበልሺ አጉል ታደርጊዋለሽ !ይቅርብሽማንበብ ይቀጥሉ…
ከነጋሪት ጉሰማ፤ወደ ጉማ
ኢትዮጵያ ዘመም ስትልና ስትቃና የኖረች አገር ናት፤ በነዋሪዎቿ መካከል ያለው አንድነት ባንዱ ዘመን ይታመማል፤ በሌላው ዘመን ይታከማል። ዛሬ ጋብ ባለ ጦርነት እና መልኩ ባልታወቀ መጭ ዘመን መሀል ቆመናል፤ ተደባበረናል፤ ተጠማምደናል ፤ “ እንገንጠል” “ ይገንጠሉ “ የሚሉ የቃላት ልውውጦች አየሩንማንበብ ይቀጥሉ…
ከምነቴ ጋር ቀረሁ
አውቃለሁ ! አታምኝም በማምነው ያንደኛው ሰው መንገድ – ለሌላው ገደል ነው። ቢቀና ጎዳናው -ቢወለወል አስፋልት አብሮ ከማያልም -አብሮ መሄድ ልፋት ያንደኛው ሰው እግር -ለሌላው እንቅፋት። ባልጮህ ባደባባይ ምኩራብ ባልገነባ-መዝሙር ባላሰማ ከጥላየ በቀር ባይኖረኝ ተከታይ በቃል ወይ በዜማ ተገልጦ ባይታይ በልብማንበብ ይቀጥሉ…
ማሸነፍ ፤ መሸነፍ እና መበሻሸቅ
ከልጅነታችን ባንዱ ቀን፤ እኔ ከማ አቡኔ ቤት ጠላ ገዝቼ ወደ ቤቴ ስመጣ ፤ ሌላው እኩያየ ደሞ ላምባ ገዝቶ ወደ ቤቱ ሲሄድ መስቀልኛ መንገድ ላይ እንገናኛለን ፤ ከዩንበርሱ በጥቂት አመት የሚበልጥ ጥንታዊ ድንጋይ ላይ የተቀመጠ ቦዘኔ ጎረምሳ ይጠራንና “ ትቸለዋለህ?” ይለናል፤ማንበብ ይቀጥሉ…
አልወዳትም እንጂ አልጠላትም (ክፍል 10-11)
(በተጋባዥነት) ክፍል 10 ማን እንደሆነች አላወቅኩም።ለምን “ማቲ” ብላ ስሜን እንደወዳጇ እንዳቆላመጠችኝ ጭምር። ደግሞስ እንደሷ ያለችን ቆንጆ ለመወዳጀት የሚያበቃ ወኔ ከየት አግኝቼ? ደግሞስ ኤዶምን የምታውቃት ከሆነ አሁን “ማቲ” መሆኔን ካመንኩላት ለእህቴ ተናግራ ልፋቴን ሁሉ ገደል ብትከተውስ?”ይቅርታ የኔ እህት ተሳስተሻል ማቲ አይደለሁም”ማንበብ ይቀጥሉ…
አልወዳትም እንጂ አልጠላትም (ክፍል 8-9)
(በተጋባዥነት) ክፍል 8 በቀጣዩ ቀን በጠዋት ተነሳሁ። የERAን ‘Divano’ የተሰኘ ሙዚቃ እየሰማሁ በሞቀ ውሀ ሰውነቴን አስደበደብኩ።ሙዚቃውና የውሀው እንፋሎት ተደማምሮ የሆነ ስርየት የመስጠት ስሜት አለው። እንደከባድ ፀሎት ሁሉ ልቤ ፍርስ ይላል።ከየት እንደመጣ የማላውቀው የእጣን ሽታ አፍንጫዬን ያውደዋል።ልቤ ወደህፃንነቴ ይሸፍትብኛል። ደጓ አክስቴማንበብ ይቀጥሉ…
የነቃና የታጠቀ
ፖለቲካ ለመጻፍ አስብና “ አንተ በርገርህን እየገመጥህ ድሃውን ህዝብ ታበጣብጣለህ “ እንዳልባል እሰጋለሁ፤ ተዋናይና ሼፍ ዝናህብዙ የሚሰራውን ጭልፋ የሚያስቆረጥም ሽሮ እየበላሁ እንደማድር ብናገር ማን ያምነኛል? አድምጡኝ፤ ከዛሬ ሃያ አመት በፊት ለአመት በአል ሜዳ ላይ ለተሰበሰበ ህዝብ የሚቀርቡ ጭውውቶቸ ትዝ ይሉኛልማንበብ ይቀጥሉ…
አልወዳትም እንጂ አልጠላትም (ክፍል 6-7)
(በተጋባዥነት) ክፍል 6 ከለቅሶው ድንኳን ባሻገር ቁጭ ብዬ በግድ የምታለቅሰዋን ትንሿን እህቴን አያታለሁ። “ኤዱዬ አይዞሽ!” ብለው በደጋገፏት ሰዎች መሀል ሆና ፊቷ ላይ የማየው ህይወት አልባነት እናታችንን አስታወሰኝ። ለመጨረሻ ግዜ እናቴን ያየኋት የሞተች እለት ነበር።የአስራ አራት አመት ጎረምሳ ሆኜ። የመጀመሪያም የመጨረሻምማንበብ ይቀጥሉ…
አልወዳትም እንጂ አልጠላትም (ክፍል አምስት)
“ኤደን ምን ይሰማሻል?” “ምንም” (ዝም ተባብለን ሰዓቴ አልቆ እመለሳለሁ::) በሌላኛው ቀንም …….. “ኤደን ዛሬስ ለማውራት ዝግጁ ነሽ?” “አይደለሁም!! ማውራት አልፈልግም!” (ዝምምምምም….. ሰዓቱ ያልቃል) ደግሞ በሌላኛውም ቀን “ኤደን ዛሬስ ለመጀመር ዝግጁ ነሽ?” “ምኑን?” ” ማውራት ትፈልጊያለሽ?” “እኔ ምንም የማድረግ ፍላጎት የለኝም!!”ማንበብ ይቀጥሉ…