(በመጀመሪያ ከላይ የተጠቀሰውን ርእስ ከሁለት ታላላቅ ደራሲዎች የተዋስኩት እንደሆነ ለመግለጽ እፈልጋለሁ።”የቀበሌ 01 የመጨረሻዋ ድንግል” የሚለውን ሀረግ ከአዳም ረታ መጽሃፍ የተዋስኩት ሲሆን “እንደምን” የሚለውን ቃል ደግሞ “ጃፓን እንደምን ሰለጠነች?” ከሚለው የከበደ ሚካኤል መጽሃፍ የወሰድኩት ነው።”አረገዘች” የሚለው ቃል እና የጥያቄ ምልክቱ(?) ግንማንበብ ይቀጥሉ…
እንቁጣጣሽ
ራሴው ማበዴ ነው (የመጨረሻ ክፍል)
[አልነገርኩትም። የማላውቀው ሰው የሆስፒታሉ መግቢያ በርጋ ጠብቆኝ የትዝታን ጉዳይ ማነፍነፍ ካላቆምኩ ከምወዳቸው ሰዎች አንዳቸውን እንደማጣ እንዳስጠነቀቀኝ አልነገርኩትም። ብዙ ነገር አልነገርኩትም። እንዲያውም ምንም አልነገርኩትም። እማዬ ከዚህ በኋላ ህክምና የሚፈይድላት ነገር ስለሌለ ወደቤቷ ወስደናት ዓይን ዓይኗን እያየሁ የምትሞትበትን ቀን መጠበቅ ትኩስ ቁስልማንበብ ይቀጥሉ…
የኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር
ራሴው ማበዴ ነው (ክፍል አሥር)
የገዛ ሚስትህ በአደባባይ አብረሃት እየሄድክ ጡቶቿን የከለላቸውን ጨርቆች ገፋ ሳምልኝ ብትልህ ብልግና ይሆንብሃል። በሷ ድርጊት አንተ ትሸማቀቃለህ። መኝታ ቤታችሁ ውስጥ ራቁቷን ሆና ያንኑ ነገር ብትልህ ለቦታው የሚገባ ቅድስና አድርገህ ልትቆጥረው ትችላለህ። ምናልባትም ከዛ በላይ ‘ስድ’ ብትሆንልህ ያምርሃል። በመንፈሳዊው ዓለም የመጀመሪያውማንበብ ይቀጥሉ…
ራሴው ማበዴ ነው (ክፍል ዘጠኝ )
“አገኘሁት! ራሁ አገኘሁት!” ይለኛል የሆስፒታሉ ኮሪደር መሃል እየደነሰ “ምኑን? እስኪ አንዴ ዳንስህን አቁመህ ንገረኝ!” “የትዝታን ፍቅረኛ አገኘሁት!” “በጣም ጥሩ! የሚጠቅም መረጃ አገኘህ?” “ገና ነው። ደቡብ አፍሪካ ነው ያለው። ከሀገር እንዲወጣ ያደረገው ማን እንደሆን ገምቺ? የትዝታ አጎት! አስፈራርተውት ነው ከሀገር እንዲወጣማንበብ ይቀጥሉ…
ራሴው ማበዴ ነው (ክፍል ስምንት)
በሰላሳ አንድ ዓመቴ ማንም ወንድ ነክቷት የማታውቅ ድንግል ሴት መሆን የሚያኮራ ነገር ይሁን የሚያሳፍር አላውቅም። (‘ድንግል’ የሚለውን ቃል እጠላዋለሁ። ቃሉን እንጂ ነገርየውን አይደለም። በእርግጥ ነገርየውንም ልውደደው ልጥላው እርግጠኛ አይደለሁም። ቃሉ ግን የሆነ አፍ ላይ ሲባል ራሱ ድንግል፣ ደናግል፣ ድንጉላ……… ድንዝናማንበብ ይቀጥሉ…
ድልድዮቹን ተውልን
እመሃል ላይ ተገምሰው ማዶ ለማዶ የሚያተያዩን ሰባራ ድልድዮች እየበዙ ነው… አንዳንዶቹን ሆን ብለን ሰብረናቸዋል… አንዳንዶቹ በሌሎች ሰንኮፎቻችን ዳፋ ተሰብረዋል… ሌሎቹን ግን መሰበራቸውን እንኳ አልተረዳንም… ~ አንዳንዶች የሚሰብሩትን ድልድይ ፋይዳ በወቅት ስሜታቸው ትኩሳት ውስጥ ብቻ ስለሚመዝኑ የሰባሪነት ወኔ እንጂ የአስተዋይነት ስክነትማንበብ ይቀጥሉ…
ራሴው ማበዴ ነው (ክፍል ሰባት)
“ይሄ ኬዝ እንዲህ ቀልብሽን የሳበው የትኛው ነጥብ ነው? ግልፅ ማስረጃ ነው የተያዘባት። ራሷም ድርጊቱን መፈፀሟን አምናለች።” “ፍትህ ሰዎቹን ፈራሃቸው እንዴ?” “በፍፁም ፈርቼ አይደለም። ከእነሱ ጋር ስለመያያዙም ገና መላምት ነው ያለሽ።” ከፍትህ ጋር ሻይ እየጠጣን እየተነጋገርን ያለነው ስለትዝታ ነው። ትዝታ የ23ማንበብ ይቀጥሉ…
ራሴው ማበዴ ነው (ክፍል ስድስት)
እናቴ ከመሞቷ በፊት ልውልላት የምችለው አንድ ውለታ አባቴ እንዲያገኛት ማድረግ ነው። ቢያንስ የዘመናት ፍቅሯን እጁን ዳብሳ ደስተኛ ሆና ትሞታለች። እናቴን ማጣት ማሰብ አልፈልግም። የባሰው ደግሞ ስትለየኝ ማን መሆኔን እንኳን ሳታውቅ እብደቷ ተነስቶባት መሆኑን ማሰብ ያሳብደኛል። ያ እንዲሆን አልፈልግም። የቀራትን ጊዜማንበብ ይቀጥሉ…