እኛ ማን ነን…!

አውቀን የተኛን ነን፡፡ ቢቀሰቅሱን የማንሰማ! ከከተሳካልን ቀስቃሾቻችንንም አሰልችተን የምናስተኛ! …ሰውነታችን ጣምኖ ጮማ ከምንቆርጥ ይልቅ፣ ያለምንም ልፋት የምናገኛትን ጎመን እየላፍን፣ “ጎመን በጤና” የምንል ዘመናዮች ነን፡፡ ታሪክ ዳቦ አይሆንም ብለን፣ ታሪክ የማይሆን ዳቦ እየገመጥን ያለን በልቶ አደሮች ነን፡፡ ነፃታችንን ከባርነት እግር ስርማንበብ ይቀጥሉ…

ስለ ሴቶች

ተከርክሞ የተገረበ፣ ቧልትና ቁምነገር!! “ስለ ሴቶች“ ( ስለ ወንዶች ደግሞ እነሱ ይፃፉ) ከአፈጣጠር እንጀምር፤ በኔ እምነት፣ ሴቶች የተፈጠሩት፣ ወንዶች በተፈጠሩባት ቅፅበት ነው፡፡ እንደ መጥሐፉ ከሆነ፣ ሴት የተፈጠረችው ሁለተኛ ነው፡፡ በደንብ ካየነው ግን እኩል ነው የተፈጠሩት፡፡ ወንድ ሲፈጠር፣ እንትን ነበረው አይደል?ማንበብ ይቀጥሉ…

ለሀገሬ፣ ለሃይማኖቴ፣ ለአላማዬ አልሞትም!!!

ለምን ዓላማ እና ለማን ዓላማ ለመሞት ዝግጁ ናችሁ? ለአላማ መሞት አሪፍ ነገር ነው አይደል? አዎ! አሪፍ ነው ለብዙኀኑ- በግሌ ለኔ አይደለም፡፡ በያዝኩት ነገር ምክንያት ሞት ከመጣብኝ፣ ምላሴን አውጥቼበት ላሽ እላለሁ እንጂ፣ የሞኝ ጀብደኛ ሞት አልሞትም፡፡ በመሰረቱ አላማ የለኝም ቢኖረኝም ሙትልኝማንበብ ይቀጥሉ…

ሞት እኩል ይሆናል ሕይወት

ሞት = ህይወት ‘‘የሞት እንቆቅልሽ የሚመስጠን፣ የማይቀር፤ ነገር ግን የማናውቀው ነገር በመሆኑ ነው’’-(አፍሮጋዳ) የ“አምላክ” ትልቁ ጥበቡ ሞትን መፍጠሩ ነው- ለኔ! እያንዳንዱ ሃይማኖት እግሩን ያቆመው በሞት ላይ ነው። ሞት ባይኖር የሰው ልጅ፣ በአምላክ አማኝ አይሆንም።ሃይማቶች እግር ይከዳቸዋል። …ዘር ካልሞተ/ካልበሰበሰ ፍሬ አይሆንም።ማንበብ ይቀጥሉ…

የማንን ሃሳብ፣ በማን ጭንቅላት እያሰባችሁ ነው?

የማንን ሃሳብ፣ በማን ጭንቅላት እያሰባችሁ ነው? ( ብዙ ጭንቅላቶች ቢኖሩም፣ ብዙ ሀሳበች የሉም) የሰው ልጅ አሳቢ ፍጡር ነው ቢባልም አብዛኛው ግን አይደለም፡፡ ብዙሃኑ ታስቦ ያለቀ አሳብ እራሱ ላይ ጭኖ የሚሄድ መንገደኛ ነው፡፡ ግቡ መሄዱ እንጂ መድረሱ አይደለም፡፡ “ለምን” የሚባል ጥያቄማንበብ ይቀጥሉ…

ሀገሬ ታማለች!

ታማሚ የመሆንሽን እውነት፣ ስታውቂው፣ ሳውቀው ሳይርቀን፣ ለምን ነው፣ ይህ አባይ ቃልሽ እውነቱን የሚደብቀን? ልንገርሽ አይደለ እውነት…. እንዳንቺም ታማሚ የለ በምድር የተስተዋለ አንድነት ቁስል ሆኖበት ልዩነት ደዌ ፀንቶበት፣ መንገዱን ለሞት ያበጀ ፍፃሜን በራ ያወጀ እንዳንቺም ታማሚ የለ፣ በምድር የተስተዋለ፡፡ ግራሽን ለመታማንበብ ይቀጥሉ…

ላኩኝ የማይል ደብዳቤ!

አምላክ ሆይ! ይህንን የምፅፍልህ፣ ከአመት ለማታልፍ ፍቅረኛ በውሸት በኮሹ፤ በቆሸሹ ቃላት ከምቸከችከው ውዳሴ ከንቱ የተሸለ መሆኑን አምኜ ነው፡፡ የእውነት አምላክ ነህና የምትወደው እውነትን ነው፡፡ ስለዚህ እቅጭ እቅጯን እናወጋለን፡፡ ሃሳቤን ለሰዎች ባወጋቸው በአንተ ያምኑ ይመስል፣ ደም ስራቸውን ገትረው፣ ዐይናቸውን አፍጠው ይከራከሩኛል፡፡አንተማንበብ ይቀጥሉ…

ከመሄድሽ ወዲያ…

ከመሄድሽ ወዲያ… በምን አይነት እርጉሚት ቀን እንደሁ እንጃ፣ በምን ኀይል አንደበቴ መታዘዝን እንዳገኘ… “ሂጂልኝ!” አልኩሽ፤ “ሂጂሊኝ፣ ከቤቴ ውጪ! ተይኝ!” አልኩሽ፡፡ ትዝ ይለኛል፣ ዐይኖችሽ ውስጥ የነበረው ግርምት እና ድንጋጤ! መልስ እንኳ አልሰጠሸኝም፡፡ ሄድሽ! ግን…… የዐይን እርግብግቢት ታህል እንኳን ካልቆየች መሄድሽ በኋላ፣ማንበብ ይቀጥሉ…

ኢንጂነሩ!

ምን አባቴ አቀበጠኝ ቀድሞውንስ? ምን ስሆን ያልሆንኩትን አወራሁ? ይሄው ለደቂቃ በተናገርኳት ነገር ለሳምንታት እየተሳቀኩ ነው፡፡ ሰፈር ሰላም ብዬ ከቤቴ ወጣ ብል፣ የሆነ ድምፅ ከኋላዬ “ኢንጂነር” ሲል ያሾፍብኛል- ኢንጂነር! “ሌባ! …ሌባው” ከመባል በላይ ያሳቅቀኛል፡፡ ህፃናት፣አዋቂዎች፣ የሰፈር ውስጥ ተራቢዎች፣ተመርቀው ስራ ያጡ ሰፈርማንበብ ይቀጥሉ…

የወንዶች ዓለም!

እንደ መፀሐፉ፣ እንደ ዘፍጥረት ቃል፣ የሰው ዘር መፈጠር፣ በአዳም ይጀምራል- ከአዳም ይለጥቃል፣ የአዳምን ብቻነት፣ አምላክ አስተዋለ፣ ረዳት እንድትሆን፣ ከገዛ አጥንቱ፣ “ሴት ብፈጥርስ” አለ፡፡ እዚህ ጋ፣ አስተውሉ፤ እግዜር ለሴት ብሎ፣ አፈር አላቦካም፣ ከአዳም ተስተካካይ፣ ጊዜን አልወሰደም፣ ብቻ ከግራ አጥንቱ፣ ወሰደ ፈጠራትማንበብ ይቀጥሉ…