በሃይለስላሴ ዘመን፣ “የሃይለስ ስላሴ የሽልማት ድርጅት ” የሚባለው ተቋም፣ ከሸለማቸው ሰዎች አንዱ አኩራፊው ከበደ ሚካኤል ነበሩ። ጊዜው በ1957 ዓም ሲሆን፣ የሽልማቱ መጠን ደግሞ 7ሺ ብር፣ የወርቅ ኒሻንና ዲፕሎማን ነበር። ታዲያ ከቤ እንደሌላው ሰው ሽልማቱን በአደባባይ ለመውሰድ፣ አሻፈረኝ ብለው ቀሩ። የእምቢታቸው ምክንያት፣ በአዲስ ዘመን ላይ ፅሁፎቻቸው በመተቸታቸው ነበር። አይ ጋሽ ከቤ፣ ስንት ጥበብ ሲገባቸው እቺን ቀላል የሃሳብ ልዩነት ማስተናገጃ መንገድ ግን አልተገለጠችላቸውም ነበር።
በደራሲዎች ዘንድ ካየነው አቤ ጉበኛም መሰል ችግር አለበት።ባለፈው መፅሐፉ የተቹትን ሰዎች በአሁኑ መፅሐፉ መግቢያ እንደ ጠላት ያጥረገርጋቸዋል። ዳኛቸው ወርቁ፣ መፅሐፎቹን ከገበያ ሰብስቦ ቤቱ ያከማቻቸው ልዩነትን ባለመገንዘቡ ነው።
*****
(እህ አብረን ነን? “እሺ እስቲ እንውረድ (ፓ!እቺን ዓርፍተ ነገር ባለስልጣኖች ቢናገሯት እንዴት ታምር ነበር? )
.
.
የልዩነት አፍቃሪ ነኝ! ጥላቻን የሚጠላ፣ “ጠላቴ ” የማያባብል፣ ዛብያ የማይስቆርጥ፣ ሄምሎክ የማያስጠጣ፣ የማያስገርፍ፣ የማያሰቀል፣ የማያስግዝህ ልዩነት ማግኘት ፀጋ ነው!
ሁሉን በአንድ የአስተሳሰብ ጨርቅ መቋጠር የሚፈልጉ ሰዎችን እፈራቸዋለሁ! ዳምጠው ነገር ናቸው! የተፈጥሮ ልዩነትን ጨፍልቀው፣ የተመቻቸው ቀን ሊፈጩህ ይችላሉ!!
ልዩነት ተፈጥሯዊ ቢሆንም፣ የምንለያይባቸው ነገሮች ግን ተፈጥሯዊ አይደሉም!!
ሃይማኖታችን ተፈጥሯዊ አይደለም፤ግን ልዩነታችን ነው (ተፈጥሯዊ ቢሆን አንድ በሆነ ነበር) ብሔራችን ተፈጥሯዊ አይደለም፤ግን ልዩነታችን ነው! የቋንቋችን መለያየት ተፈጥሯዊ አይደለም፤ ግን ልዩነታችን ነው። ለጋሽ ዳምጠው እነኚህ ልዩነቶች አይገቧቸውም። የነሱን ሃይማኖት የማያምን ጠላታቸው። ቋንቋቸውን የማይናገር ፅዪፋቸው። ብሔራቸው ያልሆነ ቢኖር የማይመርጡት ጥላቻቸው ነው። ጋሽ ዳምጤ ፊትም ነበሩ፤ አሁንም አሉ። ሁሉን ዳምጠው ልዩነትን ሁሉ ከራሳቸው “እውነት ” አንፃር ብቻ እየዳመጡ… በየሰርጡ፣ በየአደባባዩ አሉ ( አቤት አይሉም ወይ ጋሽ ዳምጤ?! ነው መዳመጫ እንጂ ማዳመጫ የሎትም? )
.
.
ልዩነት ተፈጥሯዊ ነው ማለት ግን፣ የምንለያይባቸው ነገሮች አይነኬ ናቸው ማለት አይደለም። ጦር እስካልተማዘዝን፣ የጥል ጥንስስ እስካላደረግነው፣ እንደ ህይወት ልምዳችን ለተፈጠሩ ልዩነቶች ሀሳብ ብንሰናዘር ውብ ነገር ነው። በርግጥም የተለያየንባቸው ሺ ደካማ ልዩቶች አሉ።
.
.
ለምሳሌ፣ የቆየ መፅሔት ላይ አንድ ሰውዬ፣ ከሚስቱ ጋር ወሲብ ሲፈፅሙ፣ “አንተ ከላይ ካልሆንክ በቀር አይቻልም፣ ሌላው አይነት አደራረግ የሴተኛ አዳሪ ነው “ብላ ስለከለከለችው ትዳራቸው አደጋ ላይ እንደሆነና መላ የሚሉትን ሰዎች እንዲነግሩት ይማፀናል።
ባልና ሚስት አንድ ናቸው ቢባሉም እንዲህ አይነት አስቂኝ ልዩነቶች ያጋጥማሉ። በርግጥ ሚስትየው ከተለያየ አቅጣጫ ጥቃት እንዲፈፀምባት ስላልፈለገች ይሆናል ☺ ባል ደሞ፣ በፊት በክንፍ… በጀርባ ካላጠቃ የፍቅር ጨዋታ የተጫወተ አይመስለው ይሆናል።
እግዜር ያሳይህ አሁን… አንዲትን ልጅ ወደሃት፣ ነገርዬውን “ከጋብቻ በኋላ ነው የምናደርገው ” ስትልህ እሺ ብለህ፣ በተጋባችሁ ቀን ምሽት ረሀብህን ልታስታግስ አምሮህ፣ ከአምሮትም ዶጊ አምሮህ፣
“ዙሪ… ” ስትላት ይዙርብህና (ሃሃሃ)
“እንዴ አልዞርም፣ እንደሱ ደስ አይልም… ሴተኛ አዳሪ መሰልኩህ? ” ብትልህ…
ምስኪን፣ “ምነው ሞክሬ በገባሁ” ብለህ የመፀፀቻ ጊዜ ሳይኖርህ፣ በተፈቀደው አቅጣጫ ጥቃትህን ስትቀጥል ( አልታወቀህም እንጂ፣ በዚህ ሰአት ያማረህን ስርዓተ መብዶ ( የእንዳለጌታ ከበደ ቃል ናት) ከሌላ ሴት ጋር ለማድረግ ቃል ገብተህ ይሆናል… ከዛ ባንተ ድርጊት ሴቶች ተሰብስበው “ወንዶች ከሃዲዎች ” ሲሉ ባንተ ስራ እኛ መሰደባችን አያሳዝነንም?? ☺)
እስቲ ልብ ካለህ፣ “ልዩነታችን ውበታችን ” በል አሁን? 😉