Tidarfelagi.com

ቅርንጫፉ እንደ ዛፉ

የጋምቤላ ክልል የትምህርት ቢሮን ጨምሮ ዘጠኝ የክልሉ ‹‹ስራ አስፈፃሚዎች›› በሃሰተኛ የትምህርት ማስረጃ ሰበብ ተከስሰው መባረራቸውን ሰማን።
በእውነቱ፤ በዚህ ዜና የሚገባውን ያህል ልደነግጥ ባለመቻሌ አዝኛለሁ።

በስንቱ ልደንግጥ…?

በተለይ በትምህርት ጉዳይ መደንገጥ ያቆምኩት፤ በዛ ዘሞን መንግስት እድሜ ጠገቡን ትምህርት ቤት ‹‹ለልማት›› ማፍረሱን ከሰማሁ በኋላ ነው።
ትምህርት ጥፋት ሆኖ፣ ትምህርት ውድቀት ሆኖ፤ ትምህርት ቤት ለልማት ከፈረሰ ፤ ከዚህ በላይ ምን ሊያስደነግጠኝ ይችላል?
ይህ ስራ ቆዳ ተወደደ ብሎ የእርሻ በሬውን ከሚያርድ ገበሬ ይተናነሳል?
እናም መንግስት እንዲህ በአደባባይ ትምህርት ጥምቡን እንዲጥል ካደረገ በኋላ፣
ትምህርትን ከጥፋት ካስተካከለ በኋላ፣ በሀሰት የትምህርት ማስረጃ ህዝቡን ‹‹ሲመሩ›› የነበሩ ባለስልጣኖቹን ቢከስም ፣ቢያባርርም ከትልቅ ዛፍ ላይ ቅርንጫፍ ቀንጠስ አድርጎ ከመጣል አልፎ አይታየኝም።
ችግሩ መሰረታዊ ነው።
ችግሩ እንደ ትልቅ ዛፍ ስር የሰደደ ነው።
ይልቅ ‹‹ቅርንጫፉ እንደ ዛፉ›› ነውና ዛፉንም መርምሩ።
ልብ ግዙ እና እስቲ ዛፉንም ነቅንቁ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *