ዘመዶች-
ታዛ የሚባለውን ፊልም አይታችሁት ይሆን? ጤዛ አይደለም ታዛ ፡)
ካላያችሁ እዩት። ብዙ አቃቂር የማይወጣለት፣ ከምንጊዜም ምርጥ አስር የአማርኛ ፊልሞች ምድብ ውስጥ ለመመደብ የማይከብድ ውብ ፊልም ነው። ዘሪቱ ነፍስ ናት፣ አማኑኤል ልዩ ነው…እማማ እና አባባ፣ የአመል ግሮሰሪ ቋሚ ተሰላፊዎች ሁሉ ትወናቸው እንከን አልባ ነው። መቼቱ በደርግ የመጨረሻ አመታት ልጆች ለነበርን ከባድ ትዝታን ቆስቋሽ፣ ታሪኩ ፍፁም ኢትዮጵያዊ፣ ዘውጉ ‹‹አንጀት እየበላ የሚያስፈግግ›› ነው።
እስቲ አንድ ቅር የሚል ነገር አውጪ ብትሉኝ የምላችሁ ነገር አንዳንድ ቦታ ሳይመጠን የገባው የማጀቢያ ሙዚቃ ንግግሮችን እንዳንሰማ እስኪከለክል ከልክ በላይ መጮሁ ብቻ ነው። ሌላው እዳው ገብስ፣ ከፊልሙ የማያጎድል ነው።
አርትስ ቴሌቪዥን ምስጋና ይግባውና ከሰሞኑ በልዩ ጥራት ስለጫነው እዚህ አግኝታችሁ ልትደሰቱበት፣ ልታዝኑበት፣ ልትደመሙበት ትችላላሁ።
https://www.youtube.com/watch?v=aYJV2q2K0GM&feature=youtu.be