Tidarfelagi.com

ትብልዬ

የማያልፉት የለም ፣ ያ ሁሉ ታለፈ
ታጋይ የህዝብ ልጅ ፣
ምርጫ በሌለበት ፣ ምርጫ እያሸነፈ
በደሙ በላቡ ፣ ትውልድ አከሸፈ🙄(ርዕሱ አይደለም😂)
።።

መቸም የማያልፉት የለም ያ ሁሉ ታልፎ ያ ሁሉ መሥዋእት ተከፍሎበት የግንቦት 20 በዓል አከባበር በዚህ ደረጃ ቀዝቅዞ ማየት እንባ ይተናነቃል😂ትካዜ ውስጥም ይከታል🙄የታል በሬ ላይ የሚጣለው ድንኳን🙄😂 ለማንኛውም እንኳን ለነፃነት ቀናችን ለግንቦት ሀያ በሰላም አደረሳችሁ ።ዳይ የዛሬ ሁለት አመት ወደተፃፈው ፤ዛሬ ሪሚክስ ወደተደረገው ከሰብልዬ ወደ ትብልዬ
(በላይ በቀለ ወያኔ😂)

።።።



የግንቦት ፍሬ ናቴ ፣ ትግል ያፈራት እጣን
ያሳደገችው ልጅ ፣ ሀክ ሲያደርጋት ስልጣን
ጥላኝ ወዴት ሔደች ፣ አልኩኝ ተማርሬ
ድንኳን በየቦታው ፣ ትጥል ነበር ማሬ፡ ፡
።።።
ምንሽሬ
አንቺ የትግል ፣ ዘመን ጓዴ
ተረሳሽ ወይ
የሳት ዙሪያው ፣ውጊያ ባንዴ
ምንሽሬ ፣አንቺ የልጅነቴ ቀለም
ምነው ዛሬ ፣በየቦታው ድንኳን የለም፡😂
።።።
ላሳደገኝ ትግል ፣ ያውም ፍሬ ሆኜ
አብይ እንዴት ይፍታኝ፣ ካንቺ እስር ድኜ
በጊዜ ተዋከብኩ፣ ቆሜ ከመንገዴ
የኔ ለውጥ ማምጣት ፣ ካንቺ አዳነኝ እንዴ?
“””
ሳዋህድ ከኖርኩት ፣ ቅኔን ከቀን ፀሐይ
ተሽሎ ተገኘ ፣ ኦነግ ዘረፋው ላይ
ለካስ ሰው አይድንም ፣ በተቀኘው ቅኔ
ደግ ባትሆኚ ነው ፣ ደርግን ማመስገኔ😂
ለካስ ሰው አይድንም ፣ በነፃ አውጪ ቁጣ
ደግ ጥሎን ሲሔድ ፣ ደርግ ሆኖ ከመጣ!
“”””
ሀ ብለህ ተው ተኩስ ፣ ሲለኝ ህወሀቴ
ዋእ ብዬ ስተኩስ ፣ ያኔ ነው ጥፋቴ
ቀልሀ ወርቄ ቢሆን ፣ የቅርብ ዘመዴ
ወንድምን በመግደል ፣ ጀግንነት አለ እንዴ?
።።።
ታግላ ሸገር ገባች ፣ ተኩሳ ተኩሳ
ሸበጥና ቁምጣ ፣ አዩዋትማ ለብሳ፡፡
ማር ስትገባ ሸገር ፣ ያንን ቀን አስታውሳ
ታበላኝ ነበረ ፣ በሬ ላይ ደግሳ😂
።።፣
“”አንቺ የግንቦት ፍሬ ፣ ውዴ ነሽ በጣሙን
የስልጣንሽን ልክ ፣ አላውቀውም ጣሙን
አዲስ ፍቅሬ መጣሽ ፣ ባንቺ ስል እፎየኹ
ደርግን ደግ የሚያስብል ፣ ጭካኔሽን አየኹ🙄
።።
ማር ቋፍ ሆና
ማር ሬት ሆና
ማሬ ማሬ
ተቆፃፅራኝ ማሬ፡፡
“””
ማር ማር ብላ ፣ ገባች ሸገር
ሬት ሆነች ፣ በልቤ ሀገር
ቃሊቲ ወይ ቃሌን ክጄ
ነፃ ወጣሁ ፣ ተቀፍድጄ፡፡
“””
ከንግዲማ ፣ ቦንብ አስጥዬ
የሷን ስልጣን ተቀብዬ
በየቦታው ድንኳን ጥዬ
አንቺን ስል ተፈናቅዬ
ትብልዬ
ግንቦት ሀያዬ
ትብላለም
ድንኳንሽ የለም
ትብለፁ
ገፋሽ ወይ ለውፁ
አሆይይ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *