Tidarfelagi.com

ንጉሥ መሆን 2

እንደ ካሊጉላ ዓይነት መንፈስ ላለው
ንጉሥ መሆን ሥራው
አልያም: ደግሞ የ’ለት
እንጀራው ማለት ነው።

ግና ንጉሥ መሆን
ያልፋል ይራመዳል ከዕለት እንጀራነት
ንጉሥ መሆን ያልፋል ከስም ማሥጠርያነት
ይልቅ ያሥፈልጋል አብነት ሊያደርጉት
የዘርዓ ያዕቆብን ቆራጡን ልብ ኣይነት
ፍት’ እንዳይሣሣት
በልጅ ላይ ጨክኖ ፍርድን እሥከመሥጠት።

ያኔ
ይህ ዓይነቱ ንጉሥ
ቀን ከሌት ለሚደክም ቅን ፍርድ እንዲፀና
ፍትህ እንዲቃና
እንኳንሥ የታሪክ መዛግብት ይቅሩና
ኣይረሣውም ስሙን
አዲሥ የሚመጣው የህዝቦች ልቡና።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *