እናቴ ሸርሙጣ ነበረች። …… ሀገር ያወቃት ሸርሙጣ። …… ከማን እንደወለደችኝ አታውቅም። …… ባሏ ነው የሷ ዲቃላ መሆኔን የሚነግረኝ…… እሷም ግን ‘ሂድ ከዚህ ጥፋ! ዲቃላ‘ ትለኛለች ስትሰድበኝ… … የሌላ ሰው ነውር እንደሆንኩ ሁላ
አትገባኝም። …… አንዳንዴ አቅፋኝ ስቅስቅ ብላ ታለቅሳለች። …… ወዲያው መልሳ ለአይኗ እቀፋታለሁ። …‘ዞር በልልኝ‘ ትለኛለች።
ቆንጆ ናት።…… ህልም የመሰለች ቆንጆ… ባሏ ጥንቅቅ ያለ ሱሰኛ ነው። …… ብዙ ያልጠየቅኳቸው… … ያልተመለሱልኝ ጥያቄዎች አሉ። …… ማወቅም አለማወቅም የሚሰጠኝ ሽራፊ ስሜት የለም። ……
እናቴ እንዴት አንድ ዘመድ እንኳን አይኖራትም? የምንኖርበትን ቪላ አወረሱኝ የምትላቸው ቤተቦቿ እንዴት አንዲት የዘር ትራፊ አይኖራቸውም? ለምን በየቀኑ ከተለያየ ወንድ ጋር ትሆናለች? ባሏ ከመስከር ውጪ የሚያደርገው የመልስ ምት እንዴት አይኖርም? …… አላውቅም…… እነሱ ለኔ ግድ እንደሌላቸው ሁሉ እኔም ጉድጓድ ቢገቡ ግድ አልነበረኝም……
በየማታው እሱ ሰክሮ ይገባል… … እሷ ተኳኩላ ትወጣለች። …… ልጥገብ ወይ ልራብ፣ ልደሰት ወይ ልዘን፣ ልክሳ ወይ ልወፍር፣ ልማር ወይ ሜዳ ልዋል፣ ልታመም ወይ ጤነኛ ልሁን…… ግዳቸው አይደለሁም። …… ምናቸውም አልነበርኩም።………… አብሬያቸው ሆኜ የረሱኝ።… …
“እናትህ ሸርሙጣ ናት! ወንድ አትጠግብም።…… ለገንዘብ ብላ አይደለም የምትሸረሙጠው…… ሽርሙጥና ሱስ ሆኖባት ነው። …… ” ይለኛል ይዞ ከመጣው ቢራ እየቀዳልኝ… … ጠዋት ግን ገንዘብ ስትሰጠው አየዋለሁ። …… ከርሱ ጋር በየቀኑ እየሰከርኩ ማደር ልምዴ ሆነ። …… ይቀዳልኛል… … እጠጣለሁ…… አጣጩ እንጂ የማድግ ልጁ አይደለሁምና በየቀኑ የሚግተኝ አልኮል ምን እንደሚጎትትብኝ ግድ የለውም።
ለወጉ በአመቱ መጀመሪያ እንድታስመዘግበኝ ተለማምጫት ት/ቤት እገባለሁ። … አመቱን ሙሉ እመላለሳለሁ… ስንተኛ ክፍል እንደሆንኩ አያውቁም። …… እድሜዬንም ይዘነጉታል። … የትምህርት ቤት ስሜን ሁሉ የማስታውሳቸው እኔ ነኝ።…… የአባቴ ስም የባሏ ስም ነው።
“የማንም ዲቃላ አባት አይደለሁም። አባትህን ሄደህ ፈልግ።” ይለኛል ከሷ ጋር ሲጣላ………
እኔ ለነሱ ‘የለሁም‘።
አስረኛ ክፍል ስደርስ እሱ በጉበት ካንሰር ሞተ። …… እናቴ ድንገት ተቀየረች።
“ርቄ ልሄድ ነው።” አለችኝ አንድ ቀን በጠዋት
የት? ወዴት? ለምን? አላልኳትም። …… ትምህርት ቤት ደርሼ ስመለስ የለችም። …… አልጋዋ ላይ የተወሰነ ገንዘብ እና ደብዳቤ አስቀምጣልኛለች። የፃፈችልኝ… እንዳልፈልጋት…… ትምህርቴን እንድማር…… ጎበዝ ልጅ እንድሆን……ሱስ እንዳቆም…… እና እናት ስላልሆነችልኝ ይቅር እንድላት……
አልከፋኝም። እንደውም ደስ አለኝ።
ክልስ ነኝ። …… አባቴ ምናዊ እንደሆነ አላውቅም። …… እንዴትስ ላውቅ እችል ነበር?
“ይሄኔ እኮ የዘጋ ሀብታም ፈረንጅ ይሆናል አባትህ።” ይሉኛል አብሮአደጎቼ በቀልድ… …
የሚጎፈንነኝ ቀልድ መሆኑ አይገባቸውም። የሚያውቁኝ ሰወች ስለእናቴ ሲያጉረመርሙ እሰማለሁ… … ያስጠላኛል። ያስጠሉኛል። …… ስለቤተሰብ ትስስር ተያያዥ ነገር መስማትም ማየትም አልፈልግም። …… እውነት ግን አባቴ ክዶኝ ነው? ወይስ ጭራሽ መፈጠሬን አያውቅ ይሆን? አላውቅም።…… የራሱ ጉዳይ!! ……
ቤተሰብ ብቻ ሳይሆን ጓደኛም የሌለኝ ሆንኩ። …… ከሱሴ ተጋባሁ። …… ከሱሶቼ ጋር በፍቅር ተቆራኘን።
ከእንጀራ አባቴ ሱስ… … ከእናቴ ሽፍደት… … ከራሴ ቅጥ ያጣ ግድ የለሽነት… … አወጣጥቼ የአሁኑ ኪሩቤል ተሰራ።……
“ኪሩ?…… ኪሩ?” ትከሻዬን እየወዘወዘች ጠራችኝ ። ስምሪት ናት።…… ቡና ልንጠጣ ተቀምጠናል። ……
“ፊትህ እኮ ደም መስሏል። ምን እያሰብክ ነው?” አለችኝ መልሳ
ከዛ ቀን በኋላ ደህና መሆኗን ልጠይቃት አስባለሁ…… ልክ ሳያት እተወዋለሁ። …… ልትጠይቀኝ የምትፈልገው ያላት ይመስለኛል። …… አትጠይቀኝም።… … እንደበፊቱ መጫወት አቃተን። ……
“ለሴት ልጅ ለመጀመሪያ ጊዜ የተለየ ስሜት ሳይሰማኝ አልቀረም።” አልኳት
“ተመስገን ነው። …… እንዴት የተለየች ብትሆን ነው?” አለችኝ ምንም ጉጉት ሳያድርባት… …
“በማላውቀው ምክኒያት እናቴን መሰለችኝ።”
“እናትህን እኮ አትወዳቸውም።” አለችኝ ሰውነቷ እየፈሰሰ እስኪመስለኝ ተኮማትራ
“አዎን አልወዳትም። …… ” የሚሰማኝን መግለፅ ከበደኝ።
‘ግፈኛዋ እናቴን መሰልሽኝ። …… ግን በተለየ ወደድኩሽ።‘ ነው የምላት?… … እንኳን ለርሷ ለራሴ የተደበላለቀ ነገር አለው። …… ለርሷ ላስረዳት ቀርቶ ለራሴም አልገባኝም።
2 Comments
ሌላ ታሪክ ካላችሁ ፃፉልን
ሀይ