አሜሪካ ውስጥ በየቀኑ የማይደረግ አይነት ሰልፍ የለም! በዚህ ሁለት ሳምንት እንኳን ሁለት ሰልፍ አይቻለሁ። ኢራቃዊያን የአሜሪካን የአየር ድብደባ ተቃውመው የወጡትን ሰልፍ በመንገዴ አየሁ …የበርማን መፈንቅለመንግስት አለም ቸል ብሎታል የሚሉ በርማዊያንም ባለፈው ቅዳሜ ተሰልፈው የሆነ ዩኒቨርስቲ በር ላይ ሲጮሁ አየሁ! እዛ ምን እንዳላቸው እንጃ ምናልባት ተማሪዎች ይሆናሉ።
ወደኛ ስንመለስ አሜሪካ ላይ እንደኛ ህዝብ የሚሰለፍ ያለ አይመስለኝም። ትልልቅ መንገዶችን ዘግቶ ከመጉረፍ በረዶ ላይ እስከመንከባለል የኢትዮጵዊያን ሰልፍ በብዛትም በመራርነቱም ጠንከር ይላል። የዛሬ አመት ፍልስጤማዊያን ያዘጋጁት ሰልፍ ነበር ቢበዛ አምሳ ቢሆኑ ነው ታዲያ ጩኸት ምናምን የለም ብዙ ቸኮሌት ይዘው ለመንገደኛው ጣፋጭና ብሶታቸውን የፃፉባት ወረቀት ይሰጣሉ !*አሜሪካዊያን ጣፋጭ ነፍሳቸው ነው!
እና ዋናው ነጥቤ አሜሪካ በዓመት (((እስከሶስት ሽ ))) ሰልፎች ብታስተናግድም (ሁሉም በሚባል ሁኔታ የስደተኛ ሰልፍ) ሚዲያዎች ለአንዱም የተካበደ ሽፋን ሰጥተው አያውቁም ! ከእነዚህ ሰልፎች ኋላ ብዙ ሰቆቃ የሚሊየኖች እልቂትና መፈናቀል የአገሮች መፈራረስ ወዘተ ቢኖርም ሚዲያዎች ከመልእክቱ ይልቅ በሰልፈኞቹ መንገድ መዘጋቱን ነበር የሚዘግቡት ! ትላንት ምን ሆነ ? ሜጋንና ሃሪ ኦፕራ ጋር ኢንተርቪው አደረጉ ! ዲያናን አንገብግቦ የደፋው የእንግሊዝ ጡረተኛ የንጉስ ስርዓት ተቆራጩን ቆረጠብን ዘረኛ የሆነ አመለካከት አሳየን (ሜጋን ጥቁር ስለሆነች ) ወዘተ!
ዓለም ከጥግ እስከጥግ ተነቃነቀ! እንባ ተራጨ ልትሉት ትችላላችሁ! ሚዲያወች ውሎና አዳራቸው ይሄው ሆነ! ልክ የእንግሊዝ ንጉሳዊ ቤተሰብ ክፋት ዛሬ ገና የተሰማ ተዓምር የሆነ ያህል በቃ ሌላ ወሬ የለም! የጥቁሮች ህይወት ይገደናል ሲሉ ጥቁሮችን እንዳላየ ያለፈው ሚዲያ ሁሉ ኡኡ አለ! ኦፕራ ትላንት እንግሊዝ ድረስ ሄዳ ጥርቅም አድርጋ የበላችው ሰርግ በአፍንጫየ ይውጣ እስክትል የሙሽሪት ምሬት ህመሙ ፊቷ ላይ ይታይ ነበር! እንኳን ቤተመንግስታቸው ድረስ ሂደውላቸው በረገጡበት አገር ሁሉ የዘረኝነትና የከፋፋይነት ሰንኮፋቸው ለዘላለም ከማይነቀለው የእንግሊዝ ዘረኛ አገዛዝ ወራሾች ምን ጠብቃ እንደነበር እንጃ!
የሆነ ሁኖ የዓለም ሚዲያም ሆነ የፖለቲካ ሲስተም ከአንተ አገር መፈራረስ የህዝብህ እልቂትና ወዘተ በላይ የእንግሊዝ አሻንጉሊት ነገስታት ቤተሰብ ውስጥ ያለ ውሻ ካለሰዓቱ ከእንቅልፍ መነሳት አንጀቱን ይበለዋል! በዓለም ፊት ዲፕሎማሲ ወሳኝ ነገር ቢሆንም የፈረንጅ ጆሮ ለማግኘት ከመራኮት በላይ አርፈህ አገርህን ገንባ ህዝብህን አቀራርብ ሰው ሁን!! ራስህ ላላከበርከው ማንነት እንኳን ልቡን ካሜራውን የማያውስ ምድር ላይ ነን!!