Tidarfelagi.com

“ከጥላቻ ማህፀን የሚወለድ ሰላም የለም”

Bertrand Russell በ ‘The Proposed Road to Freedom’ ፣ የማርክስን “የኮሚኒስት ማኒፌስቶ” ሃሳብ (የዓለም ሰራተኞች ተባበሩ የሚለውን) ሲተች የሚከተለውን ይላል…
‘ There is no Alchemy by which a universal harmony can be produced out of hatred’
በአጭሩ…ከጥላቻ የሚገነባ ሁሉ ዓቀፋዊ ሰላም የለም ብለን እንፍታው።
ራስል ሃቅ አለው። የቃሉን ሀቅነት በእልፍ ማስረጃዎች ማጣቀስ ይቻላል።
የራስል መከራከሪያ የጥላቻ ስነልቦና የሚጠላውን ሃይል ካሸነፈ በኋላ ሌላ የሚጠላው ወገን ይፈጥራል ነው!
በኢትዮጵያ ውስጥ ያለፈውና “ያላለፈው” ስርዐቶች ጥሩ ምሳሌዎች ናቸው… ድርግ ሃይለስላሴን ጥሎ፣ “ጠላት አታሳጣኝ፣ ብታሳጣኝ እፈጥራለሁ ” በሚል ልቦናው ሺ ጠላት ፈጠረ። ሺ ገደለ ። (የሃይለስላሴ ስርዓት ከጣለ በኋላ፣ የፈጠራቸው ጠላቶች በስርዓቱ ከተፈጠሩ ከውጦች ባይበልጡ ነው? )

ኢህአዴግ ደርግን ጣለ። ጥላቻንም አነሳ። እነሆ ከዛ ጊዜ ጀምሮ፣ “ፀረ ሰላም፣ ጠባቦች፣ ወጣት ጥፋቶች፣ አሸባሪዎች፣ ፀረ ልማቶች… ወዘተ ” የተባሉት በጥላቻ መዝገቡ ሰፍተው ከሚገኙት ጥቂቶቹ ናቸው።

በጥላቻ የተፈጠረ ማህበር፣ በጥላቻ ይቆማል። ከጥላቻ ፍቅር የለም! ከፍቅር ማጣት የሚወለድ ሰላምም እንዲሁ!

የጥላቻ ሌላኛው ቀለም የዘር ጥላቻ ነው…
ራስል ስለ ዘር ጥላቻ ሲያወራ ጉንዳንን በምሳሌነት ይጠቅሳል…
ጉንዳን እንደየትኛውም ማሕበረሰብ ሶሻሊስቲ ቢሆንም ከአጎራባች የጉንዳን ማህበር የመጣን ጉንዳን ግን አጥቅቶ እንደሚገል ይገልፃል
‘Ants are as complete socialistic as any community can possibly be, yet they put to death any ant which stays among them by mistake from neighboring ant-heap”
በሀገሬ ከትሞ የሚታየው አንዱ ባህሪ ጉንዳናዊነት ነው!
Ethnic federalism ለኢትዮጵያ ከሰጣቸው እርግማኖች አንዱ ይህ ጉንዳናዊ ባህሪ ነው። ዛሬም ከክልላቸው ወጥተው ለመስራትየሚቸገሩ ብዙ ሰዎች አሉ፣ የአካባቢውን ቋንቋ ባለመቻላቸው የሚጠሉ ሰዎች አሉ፣ የስራ እድል የሚነፈጉ ሰዎች አሉ፣ “ወደ ሀገራችሁ ሂዱ… “ተብለው የተባረሩ ሰዎች እንደነበሩም ሰምተናል።
የሀገራችን የዘር ፓለቲካ የተመሰረተው በማንነት ላይ ሳይሆን በበታችነት ስሜት ወይ በጥላቻ እንደሆነ ለመረዳት ብዙ ማስለፋቱን እጠራጠራለሁ!
የዚህ ብሔር አባል የመሆንህ መለያ ያንን ብሔር መጥላት ነው የተባለ ይመስል ሁሉ በጥላቼ ቅኝት ሲወዛወዝ ሳይ፣ ሰላም መስፈኑን አይደለም ወደፊት “ሰላም ” መባባላችን እጠራጠራለሁ።

የሰው ልጅ ወዶ ባልፈጠረው ነገር ወዶ መጠላላቱ፣ ትልቁ ሰብዓዊ ቅሽምና መሆኑን ግን አልጠራጥርም።
ጥላች ምንጩ ከየትም ይሁን ከየት መድረሻውም ጥላቻ ነው። ከዱላ የሚወለድ ፍቅር የለም። ከመናቆር የሚወለድ መስማማት የለም።
ዛሬ ጥላቻ እየገፋው የሚመጣው ጦር፣ ሌላ የጥላቻ አባት እንደሚሆን ለመናገር ነብይ መሆን አያሻም!
ባለፈ ታሪክና በታሪክ ሰዎች ጥላቻ ላይ የተመሰረተው የዘር ፖለቲካ፣ የአካባቢያዊነት ዘፈን አስቀያሚ የወደፊቷን ኢትዮጵያ ምስል ማሳያ መስታወት መሆኑም የሚታይ ነው።

ራስል ላይ እንቆይ፣
“… race hatred opens men ‘s to the evil of competition and closes them against the advantages of co-operation … ”

ሰዎች የትም ይቁም የት፣ የየትኛውም ቡድን አባልም ይሁን… በልባቸው ሰሌዳ የተፃፈ ጥላቻ ካልጠፋ እንኳን ዐለማዊና ሀገራዊ ሰላም፣ ውስጣዊ ሰላምም አይጨብጡት ህልም ነው!
.
.
Love! Peace!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *