Tidarfelagi.com

የራስ ሞኮንን ድልድይ ቦኖ ውሃ ታሪክ

በምስሉ ላይ የሚታየው ይህ ከራስ መኮንን ድልድይ አጠገብ የነበረው ቦኖ ውሃ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰራው በፋሽስት ወረራ ዘመን ጥሊያኖች “ውሃ ለህዝብ” በሚለው መመሪያቸው በአዲስ አበባ ከተማ 32 የቦኖ ውሃ ጣቢያወች በአቋቋሙበት ወቅት ነበር ነገር ግን የራስ መኮንን ምስል የያዘ ሀውልት የተገጠመለት በምዕራባውያን አቆጣጣር በ1945 ዓም ድልድዩ ራስ መኮንን ተብሎ ሲመረቅ እግረ መንገዱን ቦኖ ውሃውም ራስ መኮንን ተብሎ ተሰይሞ በአገልግሎት መስክ ለዘመናት ቆየ።

ካስታወሳችሁ በጥንቷ የዶሮ ማነቂያ ሠፈር የነበረችውን ሌላ ቦኖ ውሃ ምስል እና ታሪክ ከእነ አስቀጅዋ ከዚህ ቀደም ለጥፊ ነበር ምንአልባት ካላያችሁት በዚሁ የታሪክ ገጽ ላይ ታገኙታላችሁ። የጥንቷ ቦኖ ውሃ ጣቢያ ብዛት ያለችው ቆንጃጅት ወይም ወጣት ልጅአገረዶች እንስራቸውን እና ማሰሮአቸውን ተሸክምው, ውሃ ለመቅዳት ስለሚሰበሰቡ በዘመኑ የነበሩት ወንዶች ደግሞ እጮኛ ከፈለጉ ነጭ ኩታቸውን ለብሰው በትራቸውን ከትከሻቸው ላይ አውለው, ከቦኖ ውሃው ጣቢያ ቆመው ኮረዶቹን እንስራ እያሸከሙ ይውሉ እንደነበር በታሪክ ተጽፎአል።

የጥንቷ የቦኖ ውሃ ለቄሶች እና ለአዛውንት ነጻ ነበረች, ምን እሱ ብቻ የድሮ ቄሶች ገበያ ከወጡ ጥራጥሪም ሆነ ፍራፍሪ አይገዙም ነበር,…. የዋሆቹ እናቶቻችን ለቄሶቹ ታላቅ ክብር ስለነበራቸው ገና ከሩቅ ሲያዩአቸው ከጉልበታቸው ላይ ወድቀው…እባኮን አባ ይማሩኝ እያሉ ሲማጸኑ… አባም መስቀላቸውን አውጥተው በይ ተነሽና አራት ድንች ከሁለት ራስ ሽንኩርት ጋር አቀብይኝ ምሬሻለሁ ብለው ይመርቆአቸዋል።

አይ ጊዜ….ይደንቃል…. ግን እኔ ባልኖርበት አያቴ አባ መኮንን ኖሮበታል ስለዚህ አይቆጨኝም።

One Comment

  • ዳንኤል ፀጋዬ commented on July 30, 2022 Reply

    ደስ ይላል ደንበኛ እንሑን

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *