Tidarfelagi.com

የባንክ ቤት ታሪክ (ቤተ ወለድ)

በምዕራባውያን አቆጣጠር በ1906 ዓም በአጤ ምንሊክ ትዕዛዝ አብሲኒያ በመባል የሚታወቅ ዘመናዊ ባንክ በአፍሪቃ ምድር ቀድምት ከነበሩት ዘመናዊ ባንኮች አንዱ በመሆን ተቋቁሞ ህብረተሰቡን ማገልገል እንደጀመረ እና በዚህ ዘመን ከኖረው ትውልድ አውሮጳ ቀመስ ከነበሩት ሹማምንት ውስጥ አጤ ምንሊክ እና ራስ መኮንን በኢትዮጲያ ታሪክ የመጀመሪወቹ የሕጋዊ የባንክ ደብተር ያዥ እንደነበሩ የሚገልጽ ጽሁፍ ከዚህ ቀደም በእንግሊዘኛ ቋንቋ ማቅረቤ ይታወሳል።

ዘመናዊ ባንክ ከመጀመሩ በፊት እና ከተጀመረም በኋላ እንዳውም እስካሁን ድረስ የአራጣ አባዳሪ የሚባሉ ብር አበድርው በእጥፍ የሚቀበሉ ግለሰቦች እንዳሉ ሲታወቅ እነዚህ የአራጣ አበዳሪወች የሚተዳደሩት ደግሞ ካበደሩት ገንዝብ ላይ ከሚያገኙት ወለድ በመሆኑ ሌላ ስራ የላቸውም።

የአቢሲኒያ ባንክ እስከ1936 ዓም ድረስ አራት ኪሎ አካባቢ በአገልግሎት ላይ እንዳለች በዚህ አመት በፋሽት ወራሪወች ቁጥጥር ስር በመዋል ከዚህ ጦማር ግርጌ በሚታየው ምስል ገጽታ በአዲስ ታድሳ “Banko di Roma “ ተብላ ተሰይማ እንደገና ህብረተሰቡን ስታገለግል ቆይታ ከፋሽስት ወራራ በኋላ ደግሞ በ1943 ዓም ላይ “State Bank of Ethiopia” በሚለው መጣሪያ ተቀይራ አገልግሎትዋን ቀጠለች።

ከዛም በ1963 ዓም በዚህ በምስሉ ላይ በሚታየው ወደ ዘመናዊ ህንጻ አድራሻዋን ቀይራ የኢትዮጲያ ንግድ ባንክ በሚለው አዲስ ስያሜዋ ከሌሎች እህት ባንኮች ጋር በመተባበር አገልግሎትዋን በሰፊው ስታራምድ ኖራ ዛሬ ካለችበት ደረጃ ደርሳለች። በዚህ አጋጣሚ ጥንት በአገርኛ ባንክ ቤት “ቤተ ወለድ” በሚል መጣሪያ ትታወቅ ነበር።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *