Tidarfelagi.com

የጥንቷ የአባ እንድሪያስ አስኳላ

አውሮጳ ቀመስ ዘመናዊ ተማሪ ቤት (አስኳላ) የተመሰረተው በአጤ ምንሊክ ዘመነ መንግስት እንደነበረ የተለያዩ መረጃወች ቢጠቁሙም ዳሩ ብዕርን ከብራዕና ያቆራኘ ዘመናዊ ትምህርት ግን በኢትዮጲያ ግዛት ውስጥ መስፋፋት የጀመረው ከዘመነ መሳፍንት ስርዓት በፊት እንደነበር የሚገለጹ መረጃወች አሉ።

ታዲያ ይህ በዚህ ምስል ላይ የምትታየው በምዕራባውያን አቆጣጠር በ1898 ዓም ላይ በጅቡቲ በኩል ዘልቀው ወደ ሀረር ምድር በአያሌ ይመላለሱ የነበሩ የፈረንሳይ ቄሶች የከፈቱት “አባ እንድሪያስ” ተብላ ትታወቅ የነበረች አስኳላ ምንም እንኩዋን ከአዲስ አበባ ራቅ ብላ ብትመሰረትም ነገር ግን የመጀመሪያው ዘመናዊ ተብሎ ከተመዘገበው የዳግማዊ ምንሊክ ተማሪ ቤት ቀደም ትላለች።

ለተማሪ ቤቷ መጠሪያ ይሆን ዘንድ ስማቸው የተጠቀሰው አባ እንድሪያስ የተባሉ ፈረንሳዊ ቄስ በተጠቀሰው ዓመተ ምህረት አካባቢ ዘመናዊ ትምህርትን በተመለከተ ለኢትዮጲያ ብዙ ውለታወችን የዋሉ እና ራስ ተፈሪ (ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ) ልጅ በነበሩበት ግዜ የፈረንሳይ ቋንቋ እና የንጉሣዊ አስተዳደር ስነስርዓት ያስተማሮአቸው ትውልድ የዘነጋቸው ታላቅ ሊቅ ነበሩ።

ዛሬ ለስድብነት ስለምንጠቀምበት ነው እንጂ ከቆሎ ተማሪ በፊት የነበረው የጥንቱ ተማሪ “አደርባይ” ይባል ነበር ጥሮ ተጣጥሮ ማደሪያውን የሚያዘጋጅ ሰው ማለት ነው ዛሬ ግን ይህን ቃል ልንጠቀምበት አንችልም ምክንያቱም ስድብ ሆኖአል። አይ ዘመን? ለማንኛውም ይህቺ ጦማር ፊደል አስቆጥረው ብዙወቻችንን ለቁምነገር አብቅተው እናንተ ሂዱ እኔ ደርሼ መጥቻለሁ ብለው ከመንደር ለቀሩት የልጅነቴ የኔታ መምሬ አክሊሉ መታሰቢያ ትሁንልኝ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *