በቅርቡ ከ አዲስ አበባ ወደ ጠረፍ ሲጔጔዝ የነበረ 500 ሺህ ዶላር ኦሮሚያ ክልል ውስጥ መያዙን ተከትሎ……
ለፀረ ሰላም ጉዳይ ከጃዋር የተላከ ነው ፣ አይ ለቡጡቡጥ ከህወሀት ለአብዲ ኢሌ የተላከ ነው እያሉ አንዳንዶች ሲያደነቁሩን ነበር።
ከዛም አልፎ ይህንኑ አጋጣሚ ከ ኢህአዴግ የወቅቱ የውስጥ የፖለቲካ ሽኩቻ ጋር ለማያያዝም ሲጥሩ ተመልክተናል።
እኔ ደግሞ እላለሁ “ራሳችሁን አትፎግሩ…….”
ይሄ ቢዝነስ ነውውውውውውውውው !!!
በ IMF በተለይም Global Financial Integrity (GFI) ተብሎ በሚታወቀው የአሜሪካ ድርጅት ሪፖርት መሰረት ኢትዮጵያችን ባለፉት ዘጠኝ አመታት ብቻ 11.7 ቢልየን USD የህገወጥ ገንዘብ ፍልሰት ገጥሟታል (ጀለሶች ይህ ገንዘብ ማለት ሁለት የ ታላቁ አባይ ግድብን የሚሰራ ገንዘብ ነው 😱😱)
በ 2009 ዓም ብቻ እስከ ሶስት ቢልየን ዶላር ገደማ በህገወጥ መንገድ ከሀገራችን ተሰዷል (ከሰዉ ይልቅ እንዳውም ይህንን የገንዘብ ፍልሰት ቢቆጣጠሩ የሰዉም ይቀንስ ነበር 😃)።
እና
ይሄ ሁላ ገንዘብ በየአመቱ በዚሁ መንገድ ሰተት ብሎ ሲመርሽ እንዳልነበር ዛሬ ላይ 500 ሺ ዋን ብቻ ይዞ ወዮ ወዮ ማለት ሌላ ነው ሲጀመር 500,000 $ የሚያወጣ የውስጥ ፖለቲካ የለንም።😊😊
የ 500,000 ዶላሩ ጉዳይ ስር እየሰደደ የመጣው የ ህገወጥ ገንዘብ ዝውውር ና አጠባ አንዱ ሰበዝ ነው።
ይሄ ንግድ ፈቃድ የማይወጣበት የቢዝነስ ትሬንድ ቢያንስ ቢያንስ ከ 100 የማያንሱ ድርጅቶች(በሌላ ንግድ ፈቃድ የሚሰሩ )እና በሚልየን የሚቆጠሩ ዜጎች የሚተሳሰሩበት ንግድ ነው።
አዳሜ ከዘመድ አዝማድ (በአብዛኛው ከ ህገወጥ ስደተኞች) በ ኢመደበኛ መንገድ የሚላክለትን የውጭ ምንዛሬ ከባንክ የተሻለ ዝርዝር ብር ለሚሰጡት ከላይ ለተጠቀሱት ነጋዴዎች ይሸጠዋል።
ምንም እንኴ ባንክ ሄዶ የመመንዘር እድል ቢኖረውም 1000 USD ቢላክለት በትንሹ የ 4000 ብር ሲያልፍም 5000ብር የተሻለ ትርፍ ወደሚያገኝበት ገበያ ይሄዳል ።
እና ምን ያድርግ …..?
ነጋዴው ደግሞ ዶላሩን የሚገዙት አራት አይነት ደንበኞች አሏቸው …..የነዚህ ደንበኞች አመጣጥ መነሾ ደግሞ በቀጥታ ለጥቁር ገበያ መስፋፋት ምክንያት የሚሆኑትን basic principles ይወክላሉ።
1) ግሽበት (inflation)፣የንግድ ቢሮክራሲ እና የተሻለ ትርፍ;
ወዳጄ የብር የመግዛት አቅሙ በየአመቱ እስከ 10% ድረስ ሲወርድ ምንማለት እንደሆነ ላንተ አይነገርም 5,000,000 ብር አካውንቱ ውስጥ ያስቀመጠ ሰው (አመቱን ሙሉ እን
ደዚህ አይነት ገንዘብ ሳያንቀሳቅስ የሚያስቀምጥ አለ ግን 😊? ) interest እንኳ እየተከፈለው እስከ 250,000 ብር ድረስ ይከስራል ይህ እንግዴህ ብሄራዊ ባንክ ና IMF የተስማሙበት ነው።።
ከሀገራችን ባህላዊ ግብይት የበላይነት አንፃር (የመሬት ዋጋ በአመት ምንያህል ከፍታ እንደሚያሳይ የደላላ ስልክ ላይ ደወል አድርገህ ብትጠይቀው ጥሬ ሀቁን ይዘረግፍልሀል)
ወይም ደግሞ ቢዝነስ ትሬንድ ውስጥ ያለውን ቀለል ያለ የህዳግ ምጣኔ ብታይ (በነገራችን ላይ ትንሹ የህዳግ ምጣኔ 40% አካባቢ ነው ) እናማ ከላይ ያለው የዋህ ሰውየ ባንኩ interest እየከፈለውም በአመት በደምሳሳው ና በትንሹ እስከ ሁለት ሚልየን ብር ድረስ ያጣል።
እና…………….. እናማ………
ዋነኛ ተግዳሮቶችን ; ቢሮክራሲ፣ የምንዛሬ እጥረት፣ የገቢዎችና ጉምሩክ ቅዥብር ፣የገበያ Monopoly፣ የሙስና ኔትወርኩን ና ፉክክሩን ማሸነፍ ቢቻለው ብሩን በአመት በትንንንንሹ ሁለቴ ያገላብጠዋል ( ከላይ ያለውን አንስተኛ የትርፍ ህዳግ ልብ በል ና ባገላበጠው ብዛት አብዛው)
ነገርግን ከላይ ያሉት በቃል የተገለፁ ነገርግን በተግባር እያንዳንዳቸው ልብ የሚያቆሙ፣ ደም የሚያበዙ ፣ የሚያንዘረዝዝዝሩ ና የሚያጥወለውሉ ችግሮች በስፋት ፣ በጥልቀት ና በውስብስብ ደረጃ ባሉብት አገር ውስጥ …..
ቀለል ያለውንና ፀዳ ፣ ነፋ ብሎ የሚሰራውን ቢዝነስ ይመርጣላ አለቄ ደቄቄ….
የገንዘብ አጠባ ስራ
ባቃ ለ አመታት ስትከስርበት የነበረውን ብር ከባንክ አውጥተህ ( ግብር የለ፣ ቢርክራሲ የለ፣ expiry date የለ፣ ጥራትና ምዘና የለ፣ ሞራሉ ከወደቀና የጀዘበ ሰራተኛ ጋር ጭቅጭቅ የለ ፣ ወላ መጋዘን ኪራይ ….ባቃ …
ቡቲክህን ትከፍታለህ አንድ ሶስት ጠብደል ያሉ የቤተሰብ አባላትን አሰልፈህ ከየመንገደኛው ከ 100 ጀምሮ እስከ 10,000 USD በየቀኑ ትገዛልህ….ትሸጣለህ ….
አለቀ ያንን wear ሲያደርግ የነበር 5 ሚልየን ብር በአመቱ መጨረሻ ላይ ትሰልሰውና ክብር ክብርብር ትላልህ !
የ ዶላር ንግዱ ውስጥ በሙሉ ግዜው ለመግባት ድፍረት፣ ወኔ ወይም ጥበቡ የሌለው ደግሞ ትርፉ ቀርቶብኝ ለምን እከስራለሁ ሙድ ያንን 5 ሚልየን ብር አውጥቶ በዶላር ቀይሮ ቁጭ ያደርገዋል። ከዛማ በየ 3 ወሩ እየደወለ እኽ ዕቃ ስንት ገባ ይላል…..ያው አንድ ነገር እርግጠኛ ነው።
………..ይጨምራል እንጂ አይቀንስም።
2-የውጭ ምንዛሬ እጥረት
አስመጪ ነህ
ያው IMF በሚነግረን export/import ratio መሰረት ኢትዮጵያ ውስጥ 5,000,000 ብር ይዘህ ነጋዴ ከሆንክ 70% ዕድልህ አስመጪ የመሆን ነው።።።።።
Here comes the big staff……
የገቢ ወጪ ንግዱ እንደ ኮንዶሚነየም ብድር 30/70 በሆነበት አገር ላይ አስመጪ ሆነህ ዶላሩን ኬታባህ ታመጣለህ?
……………ከዛ ቡቲክ ነዋ 😃 !!
ይህንን ብር ይዘህ የመኪና አስመጪ ትሆናለህ ሁሉንም ወጪ ቀረጡን ጨምሮ አስበህ 25 Corolla መኪኖች ለማዘዝ የሚያስችልህን ብር እንደያዝክ ታውቅና 25 * 5000USD = 125,000 $ ከባንክ ለማስፈቀድ ስትጠይቅ
…………ቅዥቢ ነህ እንዴ ? ትባላለህ እናም አንድ 3 ወር ትታሽና 500 $ ብቻ ይፈቅድልሀል ።
ከዛስ……….
ከዛማ የቀረውን (124,500 $) ከባንክ ምንዛሪው አንፃር በትንሹ በ 4 ብር ልዩነት ከ ዛች ቡቲክ ትገዛለህ.. ያው 124,500*4 ብር= 498,000 ብር ኪሳራ መሆኑ ነው ።
ግን ግድ የለም የሁሉም ነጋዴ ችግር ስለሆነ እንደ ኪሳራ አትቆጥረውም በኤይርፖርት በኩል ደረትህን ነፍተህ ይዘኸው ትወጣለህ።(ምንም እንኳ በባንክ ተፈቅዶ ከተሰጠህ ቢበዛ 5000$ በላይ ከአገር ይዘህ መውጣት ክልክል ቢሆንም ቅሉ)
ወይም
ወይም
ደግሞ አሁን እንደተያዘው አይነት ጠብዳላ ገንዘብ ከሆነ ወደ ሶማልያ ተጭኖ ይላካል ……ከዛም ወደ ዱባይ በአካውንት ትራንስፈር ይደረጋል…….. ( ዱባይ ላይ ሲደርስ ታጠበ ማለት ነው ምክንያቱም የዱባዩ አካውንት የ exporter ወይም ሰርቪስ provider ድርጅት ነው )
ያው ሰውየው በኤይርፖርት ዶላሩ በ ጠረፍ ወጥተው ዱባይ ላይ ይገናኛሉ መኪኖቹንም ሸማምቶ ና ጭኖ ይመለሳል።
አስቂኙ ነገርም ይቀጥላል…..በትክክል 125,000$ የከፈለበትን መኪኖች 500$ ነው የገዛሁዋቸው ብሎ ለጉምሩክ ባለስልጣን declare ያደርጋል። ጉምሩክ የራሱ fixed price data ስላለው በመረጃው መሰረት ያስከፍለዋል።
ግን ግን…..
መዋሸቱንም ፣ ህገወጥ የገንዘብ ዝውውር ውስጥ መሳተፉንም በመረጃ ደግፎ እራሱ እያቀረበ ላሽ ይባላል።
ስለዚህ ስራው በሃላል ይቀጥላል…….😃😃
95% የሚሆነው የመኪና አስመጪ ይህንን የ money laundering method መንገድ ተከትሎ ይሰራል 🤤🤤🤤
3- Insecurity / በሀገሪቷ ላይ እምነት ማጣት
እነ ጋሽ ታምራቶች ደግሞ አሉ …..ሀብትና ገንዘብ አላቸው ነገር ግን በሀገራቸው ላይ መተማመን የሌላቸው ….
ኮሽ ሲል ( እንደ ባለፈው በተለያዩ የአገራችን አካባቢዎች እንደነበረው እይነት አለመረጋጋት ) ይደውላሉ
እቃ/ጥይት ስንት ገባ … ? ይላሉ ከላይ ያለውን ትሬንድ ተከትለው ገንዘቡን ወደ ሚፈልጉት አገር በቀላሉ ያሻግሩታል…..ከዛም እዛው ይቀራል አሊያም ሰላም ሲሆን ታጥቦ ይመለሳል ።
4- ሙስና
ይኸኛው ገዳይ ነው….ከላይ የተጠቀሱት ተዋናዮች ሁላ ወንጀል እየሰሩ ቢሆንም ቅሉ መነሿቸው ግን አሳማኝ ነው ።
ችጋራም የ4000 ብር ደሞዝተኛ የመንግስት ባለስልጣን የ 500 ሚልየን ብር በጀት የሚያንቀሳቅስ መስርያቤት ውስጥ ፈላጭ ቆራጭ ፤ ከፋይ ከልካይ ሆኖ ይመደብና እንደ ግብር ሰብሳቢ ምፅ ምፅ እያለ ከእያንዳንዱ የግዢ ና ኮንትራት ተከፋይ ስሙኒ ስሙኒ (25000 ብር ለማለት ነው😊😊) መሰብሰብ ይጀምራል……
ያው መብያ መጠጫውን ያሟላል፣ ለአመት በዓል በግ በሽ ነው ጎረቤትና አማቾቹ ሳይቀሩ ተጠቃሚ ይሆናሉ…….
በቃ ፌሽታ፣ደስታ፣ረሃ ይሆናል።
ግብድዬ ሶፋ ገዝቶ ጠባቡን ሳሎን ይሞላዋል……(ሳሎኑ ውስጥ የሚረገጥ መሬት ከመጥፋቱ የተነሳ ጩጬዎቹ ከሶፋ ሶፋ መዝለል ይለምዳሉ😃😃)
ከሙስናውም ይዞት ከመጣውም ፀዴ ህይወት ጋር ይላመዳል ፣ፍላጎቱም ይጨምራል። እነሆ ጨዋታውን ከ ምፅ ምፅ ወደ የፐርሰንት ጨዋት ይቀይረዋል። አዎ አሁን ትክክለኛ የቢዝነስ ሰው እንደሆነ ይሰማዋል ፣ ይደራደራል መሳፍንት ይሆናል።
ኮንትራክተሮቹ ኮንትራቱን በጨረታ ቢያሸንፉም እንኴ protection ይፈልጋሉ፣ ስራው ጥራት የለውም ፣ ማስረከቢያ ግዜው አልፏል ….ምናምን እያለ አዛ የሚያደርጋቸው አይፈልጉም …..ለዚህ መፍትሄው ደግሞ ቀላል ነው 2% ግብር ለመሳፍንቶቹ ይከፍላሉ።
ይቺ 2% ድርጅቶች ሳይቀሩ ዋጋ ለማውጣት cost ሲሰሩ የሚጨምሯት ቀላል ነገር ናት።
ዋው የሚያስብለው ከ 500 ሚልየን ብር ውስጥ ካልትሳካ የ300ሚልየኑን ግብር 2% 6 ሚልየን አካባቢ ገቢ ያደርጋል።
ይሄኔ ይደነግጣል…..አሃ ….
ይሄማ ከቦርጭ ያለፈ ምልክት እንደሚያሳይ ይረዳል። እናማ ቤት ልግዛ (በማን ስም ላድርገው ? በወንድሜ ? ሚስት ?…ግራ መጋባት… )
ይሄኔ ነው አንድ ከሱ ቀድሞ መሳፍንት የሆን ጔድኛው መፍትሄውን ሹክ የሚለው…
ዱባይ እኮ ገነት ናት ! ይለዋል።
እናማ አንድ ዱባይ ታትሮ የሚኖር ደላላ አበሻ ያገናኘውና
አንድ 50 ሺ ብር ወጪ አድርጎ ዱባይ ሄዶ አካውንት ይከፍታል….በዛውም በህይወቱ አይቶ የማያቃቸውን ፀዴ ሆቴሎችና የ ባህርዳር መዝናኛዎች ላይ ተንፈላሶ ይመለሳል።
ከዛማ የቅድሙ ዶላር አጣቢ ይጠራል ….ብሩ ይመነዘራል
…..ወደ ሶማሌላንድ ይጔጔዛል…….ከዛም ቀጥታ የዱባዩ አካውንት ውስጥ ዘጭ ይላል። safe mode !!!
አሁን መሳፍንቱ ከበፊቱ በበለጠ ምራቁን ይውጣል፣ ይጣፍጠዋል….እዚህ ሳይክል ውስጥ ቤተኛ ይሆናል።
ከላይ ከተጠቀሱት በሙሉ ይሄኛው ዘግናኝ ጉዳት አለው ከ እያንዳንዱ ዜጋ ኪስ ውስጥ መሰረቁ ሳይበቃ በሌለ የውጭ ምንዛሬ ከአገሪቷ የምንዛሬ ባላንስ ላይ ተጓድሎ እንደ ጠሽ ድያስፖራ በወጣበት ይቀራል….ካስፈለገም እዛው ኢንቨስት ይደረጋል።
የ ቅድሙን ጥናት ስንመለከት ከኢትዮጵያ በአመት ህገወጥ በሆነ መልኩ እስክ 3 ቢልየን የ አሜሪካን ዶላር ድረስ ይወጣል። እንግዲህ ይህ ማለት ከላይ የተጠቀሱት ተዋንያኖች በሙሉ ተደማምረው በአመት ይህንን ገንዘብ ያንቀሳቅሳሉ ማለት ነው። መንግስት ባለበት አገር ይህ ብር ወይ በኤይርፖርት ወይ በጠረፍ ሰተት ብሎ ይወጣል።
ምንምእንኴ ሁሉም ገንዘብ እዛው ባይቀርም የመሳፍንቶቹ ግን የሰው አገር ባንክ ያሞቃል፣ ያዳብራል።
እናማ በየአመቱ ይህ ሁላ ቢልየን ዶላር በተመሳሳይ መልኩ ሲወጣ እንዳልነበር 500 ሺህ ዶላር ያዝኩ ብሎ ያዙኝ ልቀቁኝ ፤ የሽብርተኛ ነው፤ የውስጥ ፖለቲካ ነው፣ ፀረሰላም ሀይል…ብላ ብላ ምናምን እያላችሁ አዛ አታድርጉን ለማለት ነው።
ቢዝነስ ነውውውውውውውውውውውው !!
ቤቃ ይኸው ነው
ይቅር በሉኝ
ተሳስቼ ነው