ይወለዱና በፈረንጅኛ የሸበረቁ
ከ”ኦ ማይ ጋድ” ውጭ ፀሎት አያዉቁ
ይወለድና ምሁር የሚባል
ባህር ተሻግሮ ታሪክ ያርማል
ይወለድና ለዕለት አሳቢ
ሆኖ ይቀራል ኪራይ ሰብሳቢ
ይወለድና ኒዎሊበራሉ
ጠረ-ልማት ነው ካገሩ ሁሉ
ይወለድና እልፍ ሞዛዛ
ግብር አይከፍል ወይ ቦንድ አይገዛ
ይወለድና የEtv አይነቱ
አይታወቅም እውነት ውሸቱ
ይወለድና ሞጭላፋ ሌባ-ካድሬየሚባል
ሀገሩን ሊዘርፍ ኪሷ ይገባል
ይወለድና እውነት ነጋሪ
ሆኖ ይቀራል ቃሊቲ አዳሪ
ይወለድና የጫካ አፍሮ
ዝፈኑ ይላል ሀገሩን ደፍሮ