Tidarfelagi.com

ወንዞች

በሕይወት መንገድ ላይ
አሉ ብዙ ወንዞች
ምንሻገራቸው 
ወንዙ ፈተና ነው
ፈተናው ፈተና
አሉት እልፍ ጭንቆች።

ስንቶች ተሻገሩ፤ ስንቶች ተወሰዱ
ስንቶቹ ሰመጡ
ይኼ ነው ጥያቄው
ይኸው ነው ሚዛኑ
ይኸው ነው ልኬቱ
ሰው ከተፈጠረ
ሙት እስኪባል ድረስ
አፈር እስኪገባ
አሉት ብዙ ወንዞች
ብዙ ጓዝ ጉዝጓዞች
ለአንዳንዱ አራት፤ ለአንዳንዱም ስድስት
ለአንዳንዱም ሰባት
የሚሻገራቸው ተውጦ በስጋት
ሃኬቱም ሃሴቱ
ውድቀትና እድገቱ
የሚተረክለት፤ የሚፎከርለት
ተፈትኖ ሲያልፍ ወይ በድል ሲወጣ
ተመዝኖ ሲጎድል ወይ እኩል ሲመጣ
ስንቴ እንደሰመጠ
ስንቴ እንዳመለጠ
ወንዙ ሲመሰክር፤ ውጤቱ ሲደመር
ይኸው ነው ሚዛኑ
ይኸው ነው ልኬቱ
ኖሮ ኖሮ ሞተ የሚባልለቱ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *