Tidarfelagi.com

(ሕልም)

የሕልም ዓይነት አለ፡ እየጮሁ መጮህ የማይችሉበት፣ እየሮጡ መሮጥ የማይችሉበት፣ እያለቀሱ ዕንባ የማያወጡበት። ሕልምም አለ፡ የማያልቅ የማያልቅ መንገድ የሚጓዙበት……

ሕልምስ አለ የዘለቃ
ባነው እንኳ የሚወቃ
(ዘለቃ አስቀያሚ በመሆኗ)
ሕልምስ አለ የነ አልማዝ
ከወር እወር የሚያፈዝ
(ደደብ ስለሆኑ አልማዞች)

ሕልምስ አለ የመዘዞ
ሁሉ ነገር ጉዞ ጉዞ
(ለቀውላላ ሴቶች)

ሕልሜ እንዲህ ነው።

የሚፈታ ይፍታ፣ ለፈታ አገር ይሰጠዋል።
ያው ያሳደገችኝ ቁርጡሜ ከነኩሷ። ሌላ ምን አለኝ?

እዚያ ተራራ ነው እዛ ተራራ ነው እዚህም እዛም ወዲህም እንደሱ ወዲያም እደሱ ሁሉ ቦታ እንደዚህ እዚያ ኮረብታ ላይ ዋርካ አለ።
እዚህኛውም ወዲያኛውም ወዲህኛውም በፊትጌው በግንባርጌው በጆሮጌው በጀርባጌውም በሁሉም……

ተቀምጬ። በሰፊ ቁምጣ። ኪስ አለው፣ ጣጣ የለው።
ትከሻዬ ላይ ዘንግ፣
ዘንጉ ጫፍ ላይ ቋጠሮ፣
ቋጠሮው፡ ስንቅ፡ ጥሬ ሥጋ/የቀጭኔ ስጋ፣
ከዘንጉ በላይ አሞራ፣
ከአሞራው በላይ ደመና፣
ከደመናው በላይ ሰማይ።
ከሰማይ በላይ ሰማይ፡ ደረጃ ደረጃ ደረጃ ደረጃ ስድስት፣ ሰባት ላጥ። እዛ ስደርስ ባለወርቅ ሸበጥ። ሸበጥ፡ ከፍም የተሰራ። ጥብጣቡም አንጀት፡ የእሳት እራት አንጀት።

ብልህ መልአክ በወንፊት ማር ይነሰንሳል።

ማሩ ኮረብቶች ላይ
ኮረብቶች ላይ ዋርካ
ዋርካውም ላይ ፍሬ አለ
ፍሬውንም አዕዋፋት ይጠቀጥቁና ይዘምራሉ
ከአፎቻቸው ይሄ ይወጣል፡

አጎጤ ናት አጎጤ
የምትነካ ወጠጤ።
አላት አላት ወርቅ ዋንጫ
ፍሬ ጨምቃ ማጠጪያ

ይሔን ሕልም የፈታ ቁርጡሜን ከሰየሟት ደጃዝማች ጋር ይወስዳል።
******
(ይወስዳል መንገድ፤ ያመጣል መንገድ)

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *