‹‹የስንብት ቀለማት ውስጥ ያሉትን ቀለማት በተመለከተ ጥያቄ ቢቀርብም ቀደም ሲል ራሴም እንደማሳሰቢያ ለማስቀመጥ በልቦናዬ የሻትኩት ነጥብ ነው።
በጥልቅ ሂስ ስራ ወይም እዛም ባይደርስ በተራ ግምገማ ድርሰቱ ውስጥ የተጠቀሱት ቀለማት ምን ማለት ናቸው? ምን ይወክላሉ? ብሎ ጥያቄ ማንሳት ትክክል ነው።
በአጭሩ ከዚሁ በድርሰቱ የተጠቀሱት ቀለማት ምንም አይነት ተምሳሌትነት እንደሌላቸው መግለጽ እወዳለሁ።
እነዚህ በባህላችን ሰባቱ ቀለማት የሚባሉትን ዝርዝር አግኝቼ (የተሳካ አጋጣሚ ነው) ትርጉማቸውን ወይ የቆሙለትን ምሳሌ ግን ለማግኘት አልቻልኩም። ከእኔ የንባብ ጥበት ይሁን ወይ የቀለሞቹ ምሳሌ ተብራርቶ አለመጻፍ (በየትኛውም ሰበብ) ዝርዝር ጉዳያቸውን ማግኘት እድሉ አልገጠመኝም። ቀይ ምንን ይወክላል? ሰማያዊስ? ቢጫስ? ወዘተ።
ስለዚህ አንባቢ ተምሳሌትነታቸው ከተሰረዘ ምን ቢፈጠር ነው ቀለሞቹ መጽሀፉን መሸንሸኛ አርዕስት እየሆኑ የገቡት? አገልግሎታቸው ምንድን ነው? ብሎ መጠየቁ አይቀርም። ይሄ ትክክለኛ ጥያቄ ነው።
ቀለሞቹን እንደ ተምሳሌት መጠቀም ባልችልም እንደ ፅንሰሃሳብ ለመጠቀም መጣሬን ግን አላቆምኩም። ማህበራዊና ስነልቡናዊ ትርጉማቸውን ከመሻት ይልቅ እርዳታ ፍለጋ ወደ ሳይንስ መሸሽ (በሆነ መልክ ሽሽት ነው) የሚያዋጣ መሰለኝ። ሳይንስ ስለቀለማት ምን ይላል? ይሄስ እውቀት ለልብወለዱ ምን ግብዓት አለው? ከሽሽቴስ ምን አተርፋለሁ?
ስለ ከለር ወይም ቀለም ከማወቅ ቀድሞ ስለ ብርሃን ማወቅ ግድ ይላል። ስለዚህ ብርሃን ምንድን ነው? የሚለውን ጥያቄ መመለስ ነበረብኝ። በዚህ አጭር ጉዞዬ አይዛክ ኒውተን ስላደረገው ሳይንሳዊ ሙከራ መረጃ አገኘሁ። የዚህ ሰውዬ ፍተሻ ብዙ ቦታ ስላለ (በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መማሪያ መጽሐፍት ውስጥ አይጠፋም) አንባቢ በቀላሉ ሊያገኘውና ሊያመሳክረው ይችላል።
ከዚህ የኒውተን ሙከራ ያገኘሁት ድርሰቱን እንዳዋቅር የሚረዳኝ ግንድ ሀሳብ ነው።
ነጭ ብርሃን (white light) (ይሄ ሁልጊዜ የምናየው) የብዙ ቀለማት ውህደት ውጤት ነው። ይሄን በሳይንሳዊ ሙከራ ለማሳየት አይዛክ ኒውተን ከታች በሚታየው መልክ ሙከራውን አደረገ። (ስዕሉን ይመልከቱ)
አንድ ፕሪዝም (prism) ወስዶ ብርሃን በውስጡ እንዲሄድ አደረገ። ነጩ ብርሃን በመስታወተ ውስጥ ሲያልፍ ስለተበታተነ በውስጡ የያዛቸው የተለያዩ (ለዓይን የሚታዩት) ቀለማት በድርድር (የማርያም መቀነት ወይም ቀስተ ደመና) መታየት ቻሉ። ይሄ የቀለም ተርታ ስፔክትረም ይባላል።
A spectrum (plural spectra or spectrums [1])፡ the word was first used scientifically within the field of optics to describe the rainbow of colors in visible light when separated using a prism.
ሌላው ሀሰሳ እነዚህን ቀለማት መልሶ ወደነበሩበት ነጭ መመለስ የሚቻል እንደሆነ መከታተል ነው። ይቻላል? ይሄን ጥያቄ ያነሳሁበት ምክኒያት በሕጽናዊነት አንድ ልብ ወለድ የሚያልቅ ሳይሆን ‹‹የሚያርፍ›› ነው። በእያንዳንዱ ንዑስ ክፍል ያሉ ‹‹ኦቶኖመስ›› ታሪኮች ‹‹ለበረራ›› የተዘጋጁ ናቸው። በዚህ የመሞገቻ መስመር ስሄድ የምጠይቀው ነጩ ብርሃን ወደ ቀለም ከተበታተነ ተበታትኖ የምናየው የቀለም ድርድር ወደ ነጩ ሊመለስ አይችልም ?
(Isaac Newton also wondered if the colors of the spectrum could be recombined again to make white light……………)
አይዛክ ኒውተን ሁለተኛ ፕሪዝም በመጠቀም የተበታተኑትነ ቀለማት በማሰባሰብ ወደ ነጭ አመጣቸው። (ስዕሉን ተመልከት)
“Recombining the Visible Spectrum………………….. Newton decided to collect the separate colors of light with a second prism. As he had predicted, when the……………colors were added together, the light became white again. Newton’s experiments provided evidence that white light is composed of colors, and each color acts differently inside a prism.
ይሄ ሳይንሳዊ ፍተሸ የስንብት ቀለማት ልብ ወለድ ቅርጽ ነው። እንደ ፕሪዝም ሆነው የሚያገለግሉት ምዕራፎች በስዕሉ ማውጫ (legend) ቁጥር አንድ (1) እ ቁጥር ሁለት (2) ተብለው የተጠቀሱት ናቸው።
(Spectrum has since been applied by analogy to topics outside of optics. Thus, one might talk about the spectrum of political opinion, or the spectrum of activity of a drug, or the autism spectrum. In these uses, values within a spectrum may not be associated with precisely quantifiable numbers or definitions. Such uses imply a broad range of conditions or behaviors grouped together and studied under a single title for ease of discussion)
ልከ የተለያየ የአመለካከት ስፔክትረም ብለን እንደምንናገር የስንብት ቀለማት እንደ ስፔክትረም የተገነባ ነው ማለት እንችላለን። ይሄ ስትራክቸራል ሞዴል እንጂ ጥልቅ ትንታኔ ለማድረግ ሰፊ መንገድ የሚከፍት አይመስለኝም።